በግንቦት ሁለተኛ ሳምንት የተከበረውን የዓለም የቴሌኮሙዩኒኬሽን ቀን አጋጣሚ፣ የኢትዮጵያ ቴሌኮሙዩኒኬሽን ባለሥልጣን የመጀመሪያው ዋና ሥራ አስኪያጅ የሚዘክር ዘጋቢ ሲዲ ግንቦት 17 ቀን 2011 ዓ.ም. ከጠዋቱ 2፡30 ሰዓት በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቴአትር ይመረቃል፡፡ ተወዳጅ የሚዲያና የኮሙዩኒኬሽን ማዕከል እንዳስታወቀው፣ የመጀመርያው ሥራ አስኪያጅ ስለነበሩት ኢንጂነር በትሩ አድማሴ ሕይወት የሚተርከውና በጋዜጠኛ እዝራ እጅጉ የተዘጋጀው ዘጋቢ 107 ደቂቃ ይፈጃል፡፡ በድምፅ በተቀነባበረው ዶክመንታሪ ውስጥ የ89 ዓመቱ አረጋዊ ባለታሪክ ራሳቸው ቃለ መጠይቅ የሰጡበት ሲሆን፣ የቅርብ ሰዎቻቸውም አስተያየት ተካቶበታል፡፡