ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር)፣ በ‹‹ገበታ ለሸገር›› የገቢ ማሰባሰቢያ መድረክ ላይ ከተናገሩት የተወሰደ፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ለታዳሚዎቹ ባደረጉት ንግግር ስለአቧራና አሻራ በሰጡት ማብራሪያ፣ በትውልድ ጉዞ ውስጥ በሁለቱም ጎራ የተሠለፉ ሰዎች እንደነበሩ ወደፊትም እንደሚኖሩ አስታውሰዋል፡፡
ግንቦት 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በታላቁ ቤተ መንግሥት፣ የዳግማዊ ምኒልክ ግብር ቤት ውስጥ የተዘጋጀው የእራት ሥነ ሥርዓት፣ የአዲስ አበባን ወንዞችና ዳርቻዎች፣ እንዲሁም ተያያዥ መናፈሻዎችን ለማልማት በጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋ የተደረገው ፕሮጀክት ለመደገፍ ያለመ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረክ ነው፡፡