Saturday, June 15, 2024

ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ዳያስፖራ ደወለላቸው

[ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ባለሀብት ስልክ ደወለላቸው]

 • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዴት ነህ?
 • ለምን በግልጽ አታምኑም?
 • ምርጫው እንደሚራዘም ነው?
 • ልታራዝሙት ነው እንዴ?
 • በዚህ ሁኔታ ይካሄዳል ብለህ ነው?
 • ለነገሩ መጀመርያም መቼ ተመርጣችሁ መጣችሁ?
 • ምን ማለት ነው?
 • ሕዝቡ በትክክል መርጦ አይደለማ ወደ ሥልጣን የመጣችሁት፡፡
 • እንዳትሳሳት፡፡
 • ምኑን ክቡር ሚኒስትር?
 • ሕዝቡ በትክክል ነው የመረጠን፡፡
 • እ. . .
 • ሕዝቡ ችግራችንን ነገረን፣ እኛም አስተካከልን፣ ከዚያም መቶ ፐርሰንት አሸነፍን፡፡
 • ከእርስዎ ይኼን በመስማቴ በጣም ነው ያሳዘነኝ፡፡
 • ምኑ ነው የሚያሳዝነው?
 • ተለውጠናል ስትሉ እኮ ዲስኩራችሁም አብሮ የተለወጠ መስሎኝ ነበር፡፡
 • እ. . .
 • ሕዝብ ነው የመረጠን ስትሉ ትንሽ አታፍሩም?
 • ምኑ ነው የሚያሳፍረው?
 • ክቡር ሚኒስትር ሕዝቡ በትክክለኛ ምርጫ እንዳልመረጣችሁ ታውቃላችሁ፡፡
 • ምን እያልክ ነው?
 • ተመርጣችሁ ሳይሆን በጡንቻችሁ ነው ሥልጣን ላይ ያላችሁት፡፡
 • ለነገሩ ከአንተ ምን ይጠበቃል?
 • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
 • የቀድሞው ሥርዓት ናፋቂ ነሃ፡፡
 • በእርግጥ አሁን የቀድሞው ሥርዓት ሊናፍቀኝ ነው፡፡
 • መቼ አጣሁት እኔ?
 • ምኑን?
 • በቀድሞው ሥርዓት ተጠቃሚ ነበርካ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ እዚህ የደረስኩት በሥራ እንጂ ለሥርዓት በማጨብጨብ አይደለም፡፡
 • ካልሆነ ታዲያ ይኼኛውን ሥርዓት ለምን ትቃወማለህ?
 • ለዚያ እኮ ነው ለምን በግልጽ አታምኑም ብዬ የጠየቅኩዎት?
 • ምኑን ነው የምናምነው?
 • አገር ማስተዳደር እንዳቃታችሁ ነዋ፡፡
 • ምን ማለት ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር በየጊዜው ከድጡ ወደ ማጡ እየሄድን ነው እኮ?
 • የዘመናት ችግር በአጭር ጊዜ ሊቀረፍ አይችልም፡፡
 • ይኼ ነጠላ ዜማችሁን መቼ ነው የምታቆሙት?
 • ምን?
 • ቢያንስ ለሕዝቡ ሌላ ነጠላ ዜማ ይዛችሁ ቅረቡ፡፡
 • ምን ይላል ይኼ?
 • ክቡር ሚኒስትር ሁሉ ነገር እየባሰበት ስለሆነ በጊዜ ፈር ብታስይዙት መልካም ነው፡፡
 • ነግሬሃለሁ እኮ አንተ የለውጡ አደናቃፊ ነህ፡፡
 • እውነቱን ልንገርዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • የምን እውነት?
 • የለውጡ አደናቃፊ ማን እንደሆነ ነዋ፡፡
 • ማን ነው?
 • መንግሥት!

[ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ደላላ ስልክ ይደውልላቸዋል]

 • ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ማን ልበል?
 • ስልኬን አልያዙትም እንዴ?
 • ማን ነህ አንተ?
 • ባለፈው ተገናኝተን ምሣ በልተን ነበር፡፡
 • አላወቅኩህም ማን ልበል?
 • ባለጊዜው ደላላ ነኝ፡፡
 • እንዴት ነህ እባክህ?
 • እልም ብለው ጠፉ እኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እያወቅከው የእኛን ነገር ቢዚ ስለሆንኩ እኮ ነው፡፡
 • ቢዚ ከመሆን ዌልዚ መሆን እኮ ነው የሚያዋጣው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ካልሠሩ እንዴት ዌልዚ መሆን ይቻላል ብለህ ነው?
 • ለዚያ እኮ ነበር አብረን እንሥራ ያልኩዎት፡፡
 • እ. . .
 • ክቡር ሚኒስትር መንቃት አለብዎት፡፡
 • እንዴት?
 • ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል አይደል እንዴ የሚባለው?
 • ተረቱ ተቀይሯል እያሉ ነው፡፡
 • በምን?
 • ሲሾም ያልሠራ ሲሻር ይቆጨዋል በሚል ነዋ፡፡
 • ውሸት ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እ. . .
 • እሱ ሚዲያ ላይ ለፕሮፓጋንዳ የሚወራ ነው፡፡
 • ነው ብለህ ነው?
 • ስነግርዎት ክቡር ሚኒስትር፣ በአደገኛው ዘርፈው በአደገኛው ወደስኮር እኮ ነው አካሄዱ፡፡
 • ለነገሩ አንተ ታውቀዋለህ፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ይኼ ጊዜ ሳያልፈን እንጠቀምበት፡፡
 • እንዴት?
 • እኔ በቀድሞው ሥርዓት ተራ ደላላ ነበርኩኝ፡፡
 • እሺ፡፡
 • በወቅቱ የነበሩት የባለጊዜው ደላሎች ከዜሮ ተነስተው አሁን ባለሀብት ሆነዋል፡፡
 • እ. . .
 • ስለዚህ ክቡር ሚኒስትር አሠራሩን በሚገባ አውቀዋለሁ፡፡
 • ምንድነው አሠራሩ?
 • ለምሳሌ በቀረጥ ነፃ ዕድል ብዙ መሥራት እንችላለን፡፡
 • እንዴት? እንዴት?
 • በቃ ዋናው ሥራ ያለው እሱ ላይ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እስኪ አስረዳኝ?
 • እኔ በዚህ ዕድል መጠቀም የሚፈልጉ ባለሀብቶችን አመጣለሁ፡፡
 • እሺ፡፡
 • እርስዎ ደግሞ የቀረጥ ነፃ ዕድሉን ያመቻቻሉ፡፡
 • ከዚያ ምን እንጠቀማለን?
 • ባለሀብቱ ለእኛ ኮሚሽን ይሰጣል፡፡
 • በጣም ጥሩ፡፡
 • ስለዚህ ክቡር ሚኒስትር በዚህ የቀረጥ ነፃ ዕድል እኛም ነፃ እንወጣለን፡፡
 • ከምን?
 • ከድህነት!

[ክቡር ሚኒስትሩ ለአንድ የባንክ ፕሬዚዳንት ስልክ ይደውላሉ]

 • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዴት ይዞሃል?
 • ምንም አንል፡፡
 • ሥራ እንዴት ነው?
 • እናንተም ዝም አላችሁ እኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምኑን?
 • ኢኮኖሚውን ነዋ፡፡
 • ይኸው ዶላር ተለቀቀላችሁ አይደል እንዴ?
 • እየቀለዱ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • የምን ቀልድ ነው?
 • መቶ ሚሊዮን ዶላሯን እኮ ለ16 ነው የምንካፈላት፡፡
 • ቢሆንስ ታዲያ?
 • ስለዚህ እያንዳንዳችን የሚደርሰንን በጣት የሚቆጠሩ ባለሀብቶች ነው የሚወስዱት፡፡
 • ሁሉም መቼም ችግር ነው የሚያወራው?
 • ምን ይደረግ ክቡር ሚኒስትር?
 • ትንሽ እንኳን ማመስገን ልመዱ እንጂ?
 • በአሁን ጊዜ ማን የሚያመሠግን ሥራ ይሠራል ብለው ነው?
 • ለነገሩ እናንተም ፖለቲከኛ ሆናችኋል፡፡
 • ኧረ ምን በወጣን ክቡር ሚኒስትር?
 • ከዚህ በላይ ምን ትፈልጋላችሁ፡፡
 • ኧረ እኛ ነጋዴዎች ብቻ ነን፡፡
 • አልመሰለኝም፡፡
 • ምን ነካዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • እኔም እናንተ ምን ነካችሁ ብዬ እኮ ነው የደወልኩት፡፡
 • ፖለቲካና ባንክን ምን አገናኘው?
 • የእኔም ጥያቄ እሱ ነው፡፡
 • ግራ እያጋቡኝ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ለመሆኑ ለውጡን ትደግፋላችሁ?
 • ለውጥ ማን ይጠላል ብለው ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ታዲያ እንደዚህ የለውጡ ተቃዋሚዎች የሆናችሁት ለምንድነው?
 • ሌላ ሰው ጋ የደወሉ መስልዎት ነው?
 • ኧረ በትክክል ለአንተ ነው የደወልኩት፡፡
 • እኔ እኮ የባንክ ፕሬዚዳንት ነኝ ብዬ ነዋ፡፡
 • በሚገባ አውቃለሁ፡፡
 • ስለፖለቲካ ሲያወሩኝ ግራ ተጋብቼ እኮ ነው፡፡
 • ለምን ግራ ትጋባለህ?
 • ሥራዬ ቢዝነስ ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እንግዲያው አርፈህ ሥራህን ሥራ፡፡
 • እ. . .
 • እኛን ማስተቸትህንም አቁም፡፡
 • ምንም አልገባኝም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • በድራማ አታሰድበን፡፡
 • የምን ድራማ?
 • የቴሌቪዥን ድራማው ነዋ፡፡
 • እ. . .
 • የለውጡ ደጋፊ ከሆናችሁ በአስቸኳይ አቋርጡት፡፡
 • ምኑን?
 • ስፖንሰርሽፑን!

[ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ዳያስፖራ ደወለላቸው]

 • አዝኛለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • በምኑ?
 • በጣም ነው የቀለዳችሁብን፡፡
 • ማን ላይ?
 • ሁላችንም ላይ፡፡
 • እንዴት?
 • በወሬያችሁ አስደስታችሁን በተግባራችሁ አስለቀሳችሁና፡፡
 • ምን አድርገን?
 • እንደዚያ ሆ ብለን ደግፈን አሁን ማጠፊያው አጠረን፡፡
 • አልገባኝም?
 • ተረቱን ተገበራችሁብን እኮ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • የትኛውን ተረት?
 • በሬ ሆይ ሳሩን አየህና ገደሉን ሳታይ የሚለውን ነዋ፡፡
 • ምን እያልክ ነው?
 • በጣፋጭ አንደበታችሁ ልባችንን ሰረቃችሁና በተግባራችሁ ሁሉ ነገራችንን ዘረፋችሁና፡፡
 • ዘለፋውን በልክ አድርገዋ፡፡
 • ምን ላድርግ ክቡር ሚኒስትር?
 • ምን ይደረግ ነው የምትለው?
 • ለውጥ አለ ስትሉ አምነናችሁ ነበር፡፡
 • የለም እያልክ ነው?
 • እሱማ አለ፡፡
 • ታዲያ ምንድነው የምትለው?
 • ለውጡ የንጉሥ ብቻ ነዋ፡፡
 • እኔ ጠፋሁ?
 • ክቡር ሚኒስትር ወሬያችሁ እስካሁን መሬት አልወረደም፡፡
 • እ. . .
 • መሬት ከወረደ ይቆሽሻል ብላችሁ ፈርታችሁ ነው እንዴ አየር ላይ ያለ ወሬ የምትመግቡን?
 • ምን ይላል ይኼ?
 • ክቡር ሚኒስትር ሕዝቡ ሰልችቶታል፡፡
 • ምንድነው የሰለቸው?
 • ውሸት፡፡
 • እ. . .
 • ውሸት መሮናል፡፡
 • እንከባበር እንጂ፡፡
 • እ. . .
 • ረሳኸው እንዴ ማንነቴን?
 • ምን እያሉ ነው?
 • እኔ እኮ ክቡር ሚኒስትር ነኝ፡፡
 • ለእኔ ማን እንደሆኑ ያውቃሉ?
 • ማን ነኝ?
 • የውሸት ሚኒስትር!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...

የ‹‹ክብር ዶክትሬት›› ዲግሪ ጉዳይ

በንጉሥ ወዳጅነው ‹‹የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ግልጽ የሆነ መመርያ እስኪወጣ ድረስ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን ቅሬታውንም አልሰማሁም። እንዴት? አልሰማሁማ? የምን ቅሬታ ቀርቦባቸው ነው? ሰሞኑን ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ውድና ቅንጡ አውሮፕላን ተከራይተዋል የሚል ቅሬታ...