ፐርች (Perch) ከሚባሉት የአሳ ዝርያዎች ውስጥ ዛፍ ላይ የሚወጡ ዝርያዎች አሉ፡፡ እነዚህ አሳዎች በቁመት ከ7 እስከ 20 ሳ.ሜ. ሲደርሱ አነስተኛ መጠን አላቸው፡፡ በስንጥባቸው ሽፋን ላይ የሚገኘውን ተንቀሳቃሽ ሹል የአካል ክፍልን በመዘርጋት መሬት ሲቆነጥጡ ጭራና የፊት ክንፈ-አሳ (እግርን የተካው) በመጠቀም ደግሞ በኃይል ወደፊት ይገፋሉ፡፡ የእነዚህ አሳዎች ስንጥብ ለተወሰነ ጊዜ በአየር ላይ እንዲተነፍሱ ሆኖ የተሻሻለ ሳንባ መሰል አካል ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ውኃ አካባቢ የሚገኝ ዛፍ ላይ መውጣት ችለዋል፡፡
- ማንይንገረው ሸንቁጥ ‹‹ባለአከርካሪዎች›› (2004)