Sunday, March 26, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትየብሔራዊ አትሌቶች ምርጫና ይሁንታው

የብሔራዊ አትሌቶች ምርጫና ይሁንታው

ቀን:

በኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ለዓመታት እንደ ትልቅ ክፍተት እየቀረበ ሲያወዛግብ የቆየው የብሔራዊ አትሌቶች ምርጫ መፍትሔ ያገኘ ይመስላል፡፡ በመጪው መስከረም መገባደጃ በኳታር ዶሃ የሚካሄደውን 17ኛውን የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ተከትሎ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ለሻምፒዮናው ይመጥናሉ ያላቸውን የማራቶን አትሌቶች ምርጫ አድርጓል፡፡ ይህ ዘገባ እስከ ተጠናቀረበት ከምርጫው ጋር ተያይዞ እንዳለፉት ዓመታት ቅሬታዎች ሲቀርቡ አልተደመጠም፡፡

በባርሴሎና ኦሊምፒክ የረዥም ርቀት ንግሥቷ ኮሎኔል ደራርቱ ቱሉ የሚመራው ብሔራዊ ፌዴሬሽን እስካሁን ባደረጋቸው አኅጉራዊም ሆነ ዓለም አቀፋዊ ውድድሮች ላይ ባደረጋቸው ተሳትፎዎች አትሌቲክሱን አንድ ዕርምጃ ወደፊት የሚያራምዱ ውጤቶችን አስመዝግቧል፡፡ ምናልባትም ይህ ድል ቀጣይነት የሚኖረው ከሆነ በኦሊምፒክም ሆነ በዓለም ሻምፒዮና እያሽቆለቆለ የመጣውን የሜዳሊያ ቁጥር በቀጣዮቹ የኦሊምፒክም ሆነ የዓለም ሻምፒዮናዎች የሚያሻሽልባቸው ዕድሎች እጁ ላይ መሆናቸው ከወዲሁ እየተነገረ ይገኛል፡፡

ከመስከረም 16 እስከ 27፣ 2012 ዓ.ም. በሞቃታማዋ ኳታር ዶሃ ለሚካሄደው የዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያን በማራቶን የሚወክሉ ብሔራዊ አትሌቶች ምርጫ የተደረገው ከነተጠባባቂዎቻቸው ነው፡፡ ከምርጫው ጋር ተያይዞ የፌዴሬሽኑን የአሠራር ግልጽነት ይበልጥ ተዓማኒ የሚያደርገው አትሌቶችን የመረጠበት መሥፈርትና የሚታየውን የሰዓት ልዩነት ከነማብራሪያው ማስቀመጡ ነው፡፡ አይኤኤኤፍ በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚደረጉ የጎዳና ላይ ውድድሮች የሚሰጠው ደረጃ  የወርቅና የብር ብሎ በመለየት ሲሆን፤ በወንዶች የለንደን ማራቶን፣ በሴቶች ደግሞ የበርሊን ማራቶን ቅድሚያውን እንዲይዙ አድርጓል፡፡

የአትሌቶቹ ሰዓት የዓለም አቀፉ ማኅበር በወርቅ ደረጃ ባስቀመጣቸው ማራቶኖች ዘንድሮ ከመስከረም እስከ መጋቢት ባለው ጊዜ ውስጥ ተወዳድረው ባስመዘገቡት ሰዓት ነው፡፡ በዚሁ መሠረት በወንዶች ሙስነት ገረመው በለንደኑ የ2019 ማራቶን ያስመዘገበው 2፡ 02፡ 55 ሰዓት የመጀመሪያ ተመራጭ ሆኗል፡፡ ሙሴ ዋሲሁን በለንደን 2፡ 03፡ 16 እና ሌሊሳ ዲሲሳ በኒዮርክ 2019 ማራቶን 2፡ 05፡ 59 ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን እንዲመረጡ ተደርጓል፡፡ በተጠባባቂነት ደግሞ ሹራ ኪታጣ ለንደን 2019 2፡ 05፡ 01፣  ብርሃኑ ለገሰ ቶኪዮ 2019 2፡ 04፡ 48 እና ታምራት ቶላ ዱባይ 2018 ማራቶን 2፡ 04፡ 06 ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ ይዘው ተመርጠዋል፡፡

በሴቶች ሩቲ አጋ በርሊን 2018 2፡ 18፡ 34 የመጀመሪያ ተመራጭ ሲያደርጋት ወርቅነሽ ደገፉ ዱባይ 2019 2፡ 17፡ 41 እና ሮዛ ደረጀ ዱባይ 2018 2፡ 19፡ 17 ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን ተቀምጠዋል፡፡ በተጠባባቂነት ሹሬ ደምሴ ቶኪዮ 2019 2፡ 21፡ 05 እና ሔለን ቶላ ቶኪዮ 2019 2፡ 21፡ 01 እንዲሆኑ በቅደም ተከተል ተቀምጠዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ለፋይናንስ ዘርፉ ብቃት ያለው የሰው ኃይል የማፍራት የቤት ሥራን የማቃለል ጅማሮ

የአገሪቱ የፋይናንስ ዘርፍ እያደገ ለመሆኑ ከሚቀርቡ ማስረጃዎች ውስጥ  የግል...

የምድር ባቡርን የሚያነቃቃው የመንግሥት ውሳኔ

በኢትዮጵያ ወደብ አልባነት ላይ የተደመረውን የሎጀስቲክስ ችግር ለመፍታት ግዙፍ...

የፓርላማ አባላት ስለሰላም ስምምነቱ አፈጻጸም ግልጽ መረጃ የለንም አሉ

‹‹ሕወሓትን ለፍረጃ አብቅተውት የነበሩ ጉዳዮች በአብዛኛው መልክ ይዘዋል›› ሬድዋን...