Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበኮሌራ ወረርሽኝ 15 ሰዎች ሲሞቱ ከ300 በላይ በበሽታው ተይዘዋል

በኮሌራ ወረርሽኝ 15 ሰዎች ሲሞቱ ከ300 በላይ በበሽታው ተይዘዋል

ቀን:

ከ700 ሺሕ በላይ የመከላከያ ክትባት አገር ውስጥ ገብቷል

በአራት ክልሎችና በአዲስ አበባ ከተማ በኮሌራ ወረርሽኝ 15 ሰዎች ሲሞቱ 390 ሰዎች በወረርሽኝ መያዛቸውን፣ የኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ሳይንስ ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

በተከሰተው የኮሌራ በሽታ በኦሮሚያ ክልል አንድ፣ በአማራ ክልል 14 ሲሞቱ፣ ትግራይና ሶማሌን ጨምሮ 390 ሰዎች በወረርሽኙ መያዛቸውን ኢንስቲትዩቱ አስረድቷል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በየነ ሞገስ (ዶ/ር) ማክሰኞ ግንቦት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ የበሽታውን መንስዔ ለማረጋገጥ ከታካሚዎች ከአማራ ሁለት፣ ከትግራይ ሁለት፣ ከኦሮሚያ አምስት፣ ከአዲስ አበባ ሦስት በድምሩ ከተወሰዱ 12 ናሙናዎች ላይ የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ወረርሽኙን ያስከተለው ‹‹ቪብሮ ኮሌራ›› የተሰኘ ባክቴሪያ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ‹‹የኮሌራ ወረርሽኝ›› በማለት በሰጡት ማብራሪያ፣ ‹‹በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሐረርጌ ዞን በጭሮ ወረዳ 32፣ ኦዳ ቡልቱም ወረዳ 96፣ በበዴሳ ከተማ 10፣ በአጠቃላይ 138 ሰዎች በኮሌራ በሽታው የተያዙ ሲሆን፣ የአንድ ሰው ሕይወት በበሽታው ምክንያት አልፏል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹በአዲስ አበባ ከተማ አቃቂ ቃሊቲ፣ በአዲስ ከተማና በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በአጠቃላይ በ13 ሰዎች የበሽታው ምልክት ታይቶባቸው ሕክምና እየተደረገላቸው ይገኛል፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡

‹‹በአማራ ክልል በዋግ ህምራ ዞን በአበርጌሌ ወረዳ 82፣ በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ 112፣ በበየዳ ወረዳ 3፣ እንዲሁም በአዊ ዞን ጓንጓ ወረዳ አንድ በድምሩ 198 ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን፣ የ14 ሰዎች ሕይወት በበሽታው ምክንያት አልፏል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹በትግራይ ክልል ምሥራቃዊ ዞን ክልተ አውላዕሎ ወረዳ ስምንት ሰዎች፣ በበሽታው ተይዘዋል፡፡ በሶማሌ ክልል በቅሎማይ ወረዳ 33 ሰዎች የአተት ወረርሽን ምልክት ታይቶባቸዋል፤›› ሲሉ አክለዋል፡፡

ይህም በመሆኑ ወረርሽኙ በተከሰተባቸው ወረዳዎች ፈጣን ምላሽ ሰጪ ቡድን በቦታዎቹ ተሰማርቶ ለዚህ አገልግሎት ብቻ ተብሎ በተቋቋሙ ጊዜያዊ የሕክምና ማዕከላት ምላሽ እየሰጡ እንደሚገኙ፣ ከዚህም በተጨማሪ በጎረቤት አገሮች ማለትም በሶማሊያና በኬንያ የተከሰተው የኮሌራ በሽታ ወደ ሶማሌና ኦሮሚያ ክልሎች ሊዛመት ስለሚችል አስፈላጊው ቅድመ ጥንቃቄ መደረጉን ነው ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ የጠቆሙት፡፡

‹‹በአጠቃላይ በሽታውን ቶሎ ለመቆጣጠር መድኃኒቶችና የሕክምና ግብዓቶች፣ በሁሉም ክልሎች የሚገኙ የኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲ መጋዘኖች እንዲከማች ተደርጓል፡፡ በተጨማሪም ለዚህ በሽታ ምላሽ ለመስጠት የሚያስችል የሰው ኃይል እንዲሠለጥን እየተደረገ ይገኛል፤›› ብለዋል፡፡

የመከላከያ ክትባቱ የሚሰጠውም ወረርሽኙ በተከሰቱባቸው ክልሎች ከፍተኛ ተጋላጭነት ያላቸውን የኅብረተሰብ ክፍሎች በመለየት መሆኑን ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጸው፣ ከእነዚህም መካከል የጎዳና ተዳዳሪዎች፣ የሕግ ታራሚዎችና በአንድ በተወሰነ ሥፍራ የተሰባሰቡ ሰዎች ክትባቱን እንደሚያገኙ አስረድተዋል፡፡

በአገሪቱ ሁሉም ቦታዎች የቅኝት ሥራዎችን ተጠናክሮ እንደሚቀጥል፣ በሁሉም ክልሎች የወረርሽኙ መከሰቱን ወይም አለመከሰቱን ዕለታዊ ሪፖርት በየደረጃው ባሉ መዋቅሮች ከክልሎች እንደሚሰበሰብ፣ አስፈላጊ የሕክምና ግብዓቶችና መድኃኒቶች፣ የውኃ ማከሚያ ኬሚካሎች፣ ድንኳኖችና የመከላከል ሥራውን የሚያግዙ ሌሎች ግብዓቶች እንዲጠቀሙ ለኅብረተሰቡ የማንቂያና የማስገንዘቢያ ተግባራት ይከናወናል ብለዋል፡፡

 እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ማብራሪያ፣ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውከት (አተት) በተለያዩ ምክንያቶች ለሚከሰቱ በሽታዎች ምልክት ሊሆን ይችላል፡፡ ኮሌራ ግን አተትን ከሚያመጡ ባክቴሪያዎች አንዱ በመሆኑ በወረርሽኙ መልክ ሊከሰት ይችላል፡፡

ከበሽታው ዋና ዋና መንስዔዎች መካከል አንዱና ግንባር ቀደሙ የንፁህ መጠጥ ውኃ አቅርቦት ዕጦት ሲሆን፣ የግልና የአካባቢን ንፅህና አለመጠበቅ፣ ውኃን አፍልቶ ወይም አክሞ አለመጠጣት፣ ጎርፍና ድርቅ ከመንስዔዎቹ መካከል ይጠቀሳሉ፡፡

ኢንስቲትዩቱ አጥብቆ እንዳሳሰበው፣ የኮሌራ ወረርሽኝ በቀላሉ ሊዛመትና ከፍተኛ ጉዳት ሊያስከትል ስለሚችል ሕዝቡ የመፀዳጃ ቤት በአግባቡ መጠቀም፣ የመመገቢያ፣ የመጠጫና የውኃ ማስቀመጫ ቁሳቁሶችን በንፁህ ውኃ በማጠብና ከድኖ በማስቀመጥ ከዝንቦችና ከበካይ ነገሮች መጠበቅ ይገባዋል፡፡

ከተለያዩ ሥፍራዎች የሚገኝ ለአገልግሎት የሚውል ውኃን በውኃ ማከሚያ መድኃኒቶች በማከም ወይም በማፍላት መጠቀም እንደሚገባ፣ በምግብ ዝግጅት ሒደት ከመመገብ በፊት ከመፀዳጃ ቤት መልስ እጅን በሳሙና መታጠብ እንደሚገባም ኢንስቲትዩቱ ሳያስታውስ አላለፈም።

ወረርሽኙ እንዳይስፋፋ የሚከታተል በአገር አቀፍ ደረጃ በጤና ሚኒስትሩ ዶ/ር አሚን አሚር፣ እንዲሁም በአዲስ አበባ ከተማ ደግሞ በምክትል ከንቲባ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) የሚመሩ ግብረ ኃይሎች መቋቋማቸውን፣ አደረጃጀታቸውም በክልል፣ በዞንና በወረዳ ደረጃ እንደሚዋቀርም ተገልጿል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...