Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናፍቅረኛውን ገድሎ ሁለት እጆቿንና ጭንቅላቷን ይዞ የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ውሎ ተከሰሰ

ፍቅረኛውን ገድሎ ሁለት እጆቿንና ጭንቅላቷን ይዞ የተሰወረው ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ውሎ ተከሰሰ

ቀን:

መስከረም 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ከሌሊቱ በግምት 10፡00 ሰዓት አካባቢ በተከራየው ቤት ውስጥ ፍቅረኛውን ከገደለ በኋላ፣ ሁለት እጆቿንና ጭንቅላቷን ይዞ ተሰውሮ የነበረው ተጠርጣሪ በቁጥርጥር ሥር ውሎ ክስ ተመሠረተበት፡፡

ተከሳሹ በቅፅል ስሙ አናቶሊ ኪሮስ እንደሚባልና እውነተኛ ስሙ ከድር ሽፈራው ሐሰን መሆኑን በክሱ የገለጸው ከሳሽ ዓቃቤ ሕግ፣ ድርጊቱ የተፈጸመው በቦሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 14 ልዩ ቦታው ገርጂ ወፍጮ ቤት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ መሆኑን፣ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 20ኛ ወንጀል ችሎት ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡

ዓቃቤ ሕግ በክሱ እንዳብራራው፣ ተከሳሹ የፍቅር ጓደኛው ከሆነችው ሟች ራሔል አስመላሽ ጋር አብረው ለማደር ወደ ተከራየው ቤት ይሄዳሉ፡፡ መኖሪያ ቤቱ ከደረሱ በኋላ ምክንያቱ ለጊዜው ባልታወቀ መነሻ፣ በቤቱ ውስጥ በነበሩ ሁለት ስለቶች አንገቷን ሙሉ በሙሉ፣ ሁለቱን እጆቿን ከትከሸዋ ጀምሮ፣ እንዲሁም ሁለቱንም እግሮቿን ከታፋዋ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ በመቁረጥና ከሰውነቷ በማለያየት ሕይወቷ እንዲያልፍ ማድረጉን ዓቃቤ ሕግ ገልጿል፡፡

ተከሳሹ ሟችን ከቆራረጠ በኋላ ሁለት እግሮቿን በኩርቱ ፌስታልና በማዳበሪያ ጠቅልሎ ጥቁር ሻንጣ ውስጥ፣ ቀሪ ሰውነቷን በሌላ ኩርቱ ፌስታል በማድረግ፣ እንዲሁም ጭንቅላቷንና ሁለቱን እጆቿን በሌላ በፌስታል ጠቅልሎ በጥቁር ሻንጣ ውስጥ አድርጎ ላዳ ታክሲ በመኮናተር ወደ አቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ልዩ ቦታው አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ጀርባ መውሰዱን፣ ዓቃቤ ሕግ በክሱ አብራርቷል፡፡

ተከሳሽ በተጠቀሰው ቦታ እንደ ደረሰ ከታክሲው በመውረድ ሌሎቹን ሻንጣዎች መንገድ አጠገብ ከጣለ በኋላ፣ ሁለቱን እጆቿንና ጭንቅላቷ ያለበትን ቦርሳ ይዞ መሰወሩንም ዓቃቤ ሕግ በክሱ አስረድቷል፡፡ መንገድ ላይ የተጣለው የሟች አካል በአካባቢው ሰዎች ጥቆማ የተገኘ ቢሆንም፣ ለጊዜው ተጠርጣሪው ገዳይ ይዞ ከተሰወረው የሟች እጅና ጭንቅላት ጋር ለተወሰነ ጊዜ ቢቆይም፣ በቅርቡ በቁጥጥር ሥር መዋሉ ታውቋል፡፡

በመሆኑም ተጠርጣሪ ገዳይ በወንጀል ሕግ አንቀጽ 539 (1ሀ) ሥር የተመለከተው ድንጋጌ በመተላለፍ ድርጊቱን መፈጸሙን፣ ይኼም በሕክምና የተረጋገጠ መሆኑን ጠቁሟል፡፡ ግለሰቡ ጨካኝነቱን፣ ነውረኛነቱንና አደገኛነቱን በሚያሳይ ሁኔታ በፈጸመው ከባድ የሰው መግደል ወንጀል ክስ እንደመሠረተበትም ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ ያቀረበው ክስ ያስረዳል፡፡

ክሱ በችሎት ግንቦት 26 ቀን 2011 .ም. ለተከሳሹ ከተነበበለት በኋላ ድርጊቱን አለመፈጸሙን፣ ነገር ግን መከሰሱን እንደማይቃወም በመግለጽ የእምነት ክህደት ቃሉን ሰጥቷል፡፡ ተከሳሽ ድርጊቱን በመካዱ ዓቃቤ ሕግ እንደ ክሱ ያስረዱልኛል ብሎ የቆጠራቸውን ምስክሮች ለማሰማት ቀጠሮ ተሰጥቶታል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...