የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዚዳንት ቀዳሚ ሙፍቲ ሐጂ ዑመር እድሪስ፣ የረመዳን የጾም ወር መጠናቀቁን ተከትሎ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ፡፡ ሕዝበ ሙስሊሙ የ1440 ዓመተ ሒጅራ ዒድ አልፈጥርን በጋራ ተሰባስቦ በመስገድ፣ በመተሳሰብና በመተዛዘን እንዲያከብር ጥሪ ያቀረቡት ፕሬዚዳንቱ፣ ከዒድ ሶላት ስግደት በኋላ በመጠያየቅ፣ ያላቸው ለሌላቸው በመስጠት አብሮነቱን እንዲያሳይ አሳስበዋል።