Thursday, December 1, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ ተቃዋሚ ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው

  [ክቡር ሚኒስትር ከቤት ሊወጡ ሲል ልጃቸውን አገኙት]

  • አንተ ምን ሆነሃል?
  • ምነው ዳዲ?
  • በዚህ ሰዓት ቤት ምን ትሠራለህ?
  • ዋናው ሥራ ቤት አይደል እንዴ ያለው፡፡
  • አልገባኝም?
  • ምኑ ነው ያልገባህ ዳዲ?
  • ትምህርቱን ተውከው እንዴ?
  • የምን ትምህርት ነው?
  • እኔ ጠፋሁ?
  • የእውነቴን እኮ ነው ዳዲ፡፡
  • ተምረህ እኔ የደረስኩበት ደረጃ መድረስ አትፈልግም ማለት ነው?
  • ረሳኸው እንዴ ዳዲ?
  • ምኑን?
  • ሁሉም ዲግሪዎችህ የተገዙ መሆናቸውን ነዋ፡፡
  • አባትህ መሆኔን ረሳኸው እንዴ?
  • እሱንማ እንዴት እረሳለሁ ዳዲ?
  • ታዲያ ምን ዓይነት መልስ ነው የምትሰጠኝ?
  • በቻልከው መጠን እውነቱን ተናገር ትለኛለህ አይደል እንዴ?
  • ለማንኛውም ትምህርት ቤት ለምን አልሄድክም?
  • ምን አደርጋለሁ?
  • ትዕግሥቴን አታስጨርሰኝ፣ ልመታህ ነው፡፡
  • ዳዲ መማታትማ ድሮ ቀረ፣ አሁን ተለውጠናል እያላችሁ አይደል እንዴ?
  • እኮ ለምን አልሄድክም?
  • ዳዲ ትምህርት እንደማያዋጣ ደርሼበታለሁ፡፡
  • ጉድና ጅራት ከወደ ኋላ ነው አሉ፡፡
  • አትመለከትም እንዴ ዳዲ?
  • ምኑን?
  • በየዩኒቨርሲቲዎቹ የሚካሄደውን ነዋ፡፡
  • ምን ተካሄደ?
  • ተማሪዎቹ እኮ ከሚማሩበት የሚደባደቡበት ጊዜ ይበልጣል፡፡
  • እ…
  • በየጊዜው አይደል እንዴ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሞቱ የሚባል ወሬ የምንሰማው፡፡
  • እሱስ እውነትህን ነው፡፡
  • ስለዚህ ዩኒቨርሲቲ ከመግባቴ በፊት የሚቀድም ነገር እንዳለ ገብቶኛል፡፡
  • ምንድነው እሱ?
  • ሰውነቴን መገንባት፡፡
  • ምን?
  • ዳዲ ከትምህርት በፊት መጀመርያ ሰውነቴን ማጠንከር አለብኝ፡፡
  • ለምን?
  • ቢያንስ ዱላ ለመቻል፡፡
  • ነገረኛ ሆነሃል ልበል?
  • በዚያ ላይ ተምረህም ሥራ ስለሌለ መማሩ ምን ይጠቅማል?
  • እ…
  • ያው እናንተም ተምራችሁ ሳይሆን አማራችሁ ነው ሕዝቡን የምትገዙት፡፡
  • ፖለቲከኛ ሆነሃል ልበል?
  • ለማንኛውም አሁን ወደ ትምህርት ቤትህ ግባ፡፡
  • እንዴ ዳዲ እኔ እንዲያውም ለተማሪዎች የሚሆን ጥሩ የቢዝነስ ሐሳብ አለኝ?
  • የምን ሐሳብ?
  • እንደ ነገርኩህ ተማሪዎች ዩኒቨርሲቲ ከመግባቸው በፊት ሰውነታቸውን መገንባት ስላለባቸው ለመክፈት እያሰብኩ ነው፡፡
  • ምንድነው የምትከፍተው?
  • ስፖርት ቤት!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ ተቃዋሚ ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]

  • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት ነህ?
  • እናንተ እያላችሁ ምን እንሆናለን ብለው ነው?
  • ለውጡ እንዴት አየኸው?
  • ክቡር ሚኒስትር ሺሕ ዓመት ንገሡ እያልን ነው፡፡
  • አንተ እውነትም ውሸታም ነህ፡፡
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • ከለውጡ በፊትም የነበረው ሥርዓት ለዘለዓለም ይኑር ትል ነበር፡፡
  • ምን ነካዎ ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት?
  • ለውጡን እኮ የምናደንቀው ወደን አይደለም፡፡
  • ለምንድን ነው የምታደንቁት?
  • የእኛንም አስተሳሰብ ስለቀየረ ነዋ፡፡
  • ይኼኔ ከእኛም በኋላ ለሚመጣው ማሽቃበጥህ አይቀርም፡፡
  • እሱማ መቼ ይቀራል?
  • ለዚህ ነው የማያልፍላችሁ፡፡
  • ኧረ ክቡር ሚኒስትር ለሁለታችንም የሚያሳልፍልን ነገር አለ፡፡
  • ምን?
  • እንደነገርኩዎት ካለፈው ሥርዓት በጣም ተጠቃሚ ነበርኩ፡፡
  • እሱንማ አውቃለሁ፡፡
  • አሁን አንድ ሐሳብ ነበረኝ፡፡
  • የምን ሐሳብ?
  • ያው መንግሥት ለቀጣዩ ምርጫ ከፍተኛ በጀት እንደሚመደብ ይታወቃል፡፡
  • እሺ፡፡
  • ከዚህ ብዙ ነገር መጠቀም እችላለን፡፡
  • ምን ዓይነት ነገር?
  • ያው ከበጀቱ ከፍተኛው የሚመደበው ለፖለቲካ ፓርቲዎች ነው፡፡
  • ስለዚህ?
  • ስለዚህ ክቡር ሚኒስትር እኛ የውሸት የፖለቲካ ድርጅቶችን በመፈልፈል ተጠቃሚ መሆን እንችላለን፡፡
  • እ..
  • ክቡር ሚኒስትር እኔ የፖለቲካ ፓርቲ በማስፈልፈል የታወቅኩኝ ነኝ፡፡
  • እሺ፡፡
  • እርስዎ በሐሳቡ ከተስማሙ እንደ ጫጩት ነው ፓርቲ ማስፈልፈል የምችለው፡፡
  • ወይ ግሩም፡፡
  • በዚያ ላይ የሚፈለፈሉት ፓርቲዎች ደካማ ስለሆኑ የመንግሥትን ሥልጣን ከመነቅነቅ ይልቅ የሚደግፉ ይሆናሉ፡፡
  • ይኼ ጥሩ ሐሳብ ነው፡፡
  • በአንድ ድንጋይ ሁለት ወፍ ነው ስልዎት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ከፓርቲ ፓርቲ ለምን እንደምትዘል አሁን ነው የገባኝ፡፡
  • በሥራው ስለተካንኩበት ምንም አያስቡ፡፡
  • ለመሆኑ የእኔ ጥቅም ምንድን ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር እርስዎ ፓርቲዎቹ ዕውቅና እንዲያገኙ አድርገው በጀት ከተመደበላቸው ምን እንደሚያገኙ ያውቃሉ?
  • ምን አገኛለሁ?
  • ከእያንዳንዱ ፓርቲ በጀት…
  • እ…
  • ግማሹን ይወስዳሉ!

  [ክብር ሚኒስትሩ ከደላላ ወዳጃቸው ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]

  • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት ነው እንቅስቃሴ?
  • እንቅስቃሴው ቀዝቅዟል፡፡
  • ለምን?
  • ይኼው ሕዝቡን የኑሮ ውድነቱ አጉብጦታል፡፡
  • ምን ታደርገዋለህ?
  • በዚያ ላይ ሰሞኑን የመብራት መቆራረጡ ሌላ የራስ ምታት ሆኗል፡፡
  • እንዴት?
  • በቃ ፋብሪካዎች በሙሉ አቅማቸው ማምረት አልቻሉማ?
  • ምን እናድርግ ከተፈጥሮ ጋር አንታገል?
  • አዎ ግን ክቡር ሚኒስትር የመብራት ችግር የኑሮ ውድነቱን አባብሶታል፡፡
  • እሱማ እኛም በመብራት ችግር እየተሰቃየን ነው፡፡
  • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
  • በቃ ከምንሠራበት የማንሠራበት ጊዜ ይበልጣል፡፡
  • ምን ነካዎ ክቡር ሚኒስትር?
  • ምነው?
  • የመንግሥት ሥራ እንዴት በመብራት ምክንያት ይቋረጣል?
  • ምን ታደርገዋለህ?
  • በአፋጣኝ መገዛት አለበት፡፡
  • ምን?
  • ጄኔሬተር፡፡
  • በጀት ይኖራል ብለህ ነው?
  • ይኼማ ለሥራ ከተያዘ በጀት ላይ ነው እንጂ መገዛት ያለበት፡፡
  • እሱስ ልክ ነህ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር ለእናንተ መሥሪያ ቤት ብቻ ሳይሆን፣ ለሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ጄኔሬተር ያስፈልጋል፡፡
  • እ…
  • ክቡር ሚኒስትር ይኼ እኮ በእጃችን ላይ ያለ ወርቅ ማለት ነው፡፡
  • እንዴት?
  • ለሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤት ጄኔሬተር መሸጥ ከቻልን፣ በአጭር ጊዜ የራሳችንን የኃይል ማመንጫ መገንባት እንችላለን፡፡
  • መቼም አባ መላ ነህ፡፡
  • ክቡር ሚኒስትር በአፋጣኝ ወደ ትግበራ መግባት አለብን፡፡
  • ምን ይደረግ ታዲያ?
  • ያለ ጨረታ ግዥው ይሰጠኛ፡፡
  • እ…
  • እኛም የአስመጪ ፈቃድ እናውጣ፡፡
  • የምን ፈቃድ?
  • የጄኔሬተር አስመጪ!

   [ክቡር ሚኒስትሩ አንድ የመንግሥት ኃላፊ ዘንድ ስልክ ደወሉ]

  • አቤት ክቡር ሚኒስትር?
  • ሥራ መሥራት አልቻልንም እኮ፡፡
  • ለምን ክቡር ሚኒስትር?
  • ይኼው የመብራት መቆራረጡ ሥራችን ላይ ጫና እያሳደረ ነው፡፡
  • እሱማ የአገር ችግር እኮ ነው፡፡
  • ታዲያ መብራት የለም ተብሎ የመንግሥት ሥራ ይቆማል እንዴ?
  • ምን ይደረግ ታዲያ?
  • ለሁሉም የመንግሥት መሥሪያ ቤቶች ጄኔሬተር ይገዛ፡፡
  • ችግሩ እኮ ጊዜያዊ ነው፡፡
  • ጊዜያዊስ ቢሆን?
  • ያው የግዥው ፕሮሰስ እስኪጠናቀቅ ድረስ ችግሩ ይፈታል ብዬ ነዋ፡፡
  • እንደ አያያዙማ ችግሩ ቀጣይ ይመስለኛል፡፡
  • ምን ማድረግ ይቻላል ክቡር ሚኒስትር?
  • ስነግርህ ለሁሉም መሥሪያ ቤት ጄኔሬተር ይገዛ፡፡
  • በጀት ከየት መጣል?
  • ይኼ እኮ ራሱ የሥራ ማስኬጃ በጀት ነው፡፡
  • ምን እያሉ ነው?
  • በቃ በአስቸኳይ ግዥው ይፈጸም፡፡
  • ያለ ጨረታ ክቡር ሚኒስትር?
  • ሥራችን እየተስተጓጎለ ነው እያልኩህ ጨረታ ምናምን ትለኛለህ?
  • ክቡር ሚኒስትር ያለ ጨረታ የሚፈጸም ግዥ ያስጠይቀናል እኮ?
  • ማን ነው የሚጠይቀን?
  • የሚመለከተው አካል ነዋ፡፡
  • እባክህ ከአንድ ሰሞን የሚዲያ ጫጫታ አያልፍም፡፡
  • ምን እያሉኝ ነው ታዲያ?
  • ይገዛ!

   [ለክቡር ሚኒስትሩ ስልክ ተደወለላቸው]

  • ማን ልበል?
  • ፈልገንዎ ነበር ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • በምን ጉዳይ?
  • በጄኔሬተር ግዥው፡፡
  • እ…
  • ለጥያቄ ስለምፈልግዎት ቢሮ ይምጡ፡፡
  • ከየት ነው
  • ከፖሊስ!

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  አዋሽ ባንክ ለሁሉም ኅብረተሰብ የብድር አገልግሎት የሚያስገኙ ሁለት ክሬዲት ካርዶች ይፋ አደረገ

  አዋሽ ባንክ ለሁሉም የኅብረተሰብ ክፍሎች በዘመናዊ መንገድ ብድር ማስገኘት...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  የክልሎችን አንደኛ ደረጃ ትምህርት መማሪያ መጻሕፍት ለማሳተም 29 ቢሊዮን ብር ያስፈልጋል ተባለ

  ለብሔራዊ ፈተና የሚያገለግሉ አንድ ሚሊዮን ታብሌቶች በአገር ውስጥ ሊመረቱ...

  በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ከ30 በመቶ በላይ የሚሆኑት መምህራን አያስፈልጉም ተባለ

  የትምህርት ሚኒስቴር አካሄዱኩት ባለው የዳሰሳ ጥናት፣ በበርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...

  የጉድለታችን ብዛቱ!

  ከፒያሳ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። ጎዳናውን ትውስታ እየናጠው ሁለትና...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር! ቀድሜ ቀጠሮ እንዲያዝልኝ ስጠይቅ እንደገለጽኩት በተቋሙ ሠራተኛ ተወክዬ ነው የመጣሁት። እንዴ? አንተ የእኛ ተቋም ባልደረባ አይደለህም...

  [የተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደውለው መንግሥት በሙሰኞች ላይ ለመውሰድ ስላሰበው የሕግ ዕርምጃ ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  ሄሎ… ማን ልበል? ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስጥልኝ… ማን ልበል? የእርስዎ ትይዩ ነኝ፡፡  አቤት? ያው ፓርቲዬን ወክዬ የፍትሕ ሚኒስትሩ ትይዩ ነኝ ማለቴ ነው፡፡ ኦ... ገባኝ… ገባኝ...  ትንሽ ግራ አገባሁዎት አይደል? ትይዩ...

   [ክቡር ሚኒስትሩ እራት እየበሉ መንግሥትን በሚተቹ ጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ የተመለከተ መረጃ እየቀረበላቸው ነው]

  ለጋዜጠኞቹ መንግሥትን እንዲተቹ መረጃ የሚሰጧቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ እነሱ አይደሉም፡፡ እና የትኞቹ ናቸው? እዚሁ ከተማችን የሚገኙ ምዕራባውያን ናቸው። እንዴት ነው መረጃውን የሚያቀብሏቸው? እራት እያበሉ ነው። ምን? አዎ፣ እራት ግብዣ ይጠሯቸውና መተቸት...