Thursday, May 30, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህልአዲሱ የድንጋይ መሣርያ ግኝት በአፋር ኮል ዶራ

አዲሱ የድንጋይ መሣርያ ግኝት በአፋር ኮል ዶራ

ቀን:

ላለፉት ሦስት አሠርታት በነበረው የአርኪኦሎጂ መረጃ መሠረት የሰው ልጅ ሲስተማቲክ በሆነ መልኩ የድንጋይ መሣርያን ለመጀመርያ ጊዜ ሠርቶ መጠቀም የጀመረው 2.58 እና 2.55 ሚሊዮን ዓመታት ገደማ በፊት እንደነበር ጥናቶች ያሳያሉ::

ይሁንና በቅርቡ በአሜሪካውያንና በኢትዮጵያውያን አርኪዮሎጂስቶች የተካሄደ አሰሳና ቁፋሮ እንደሚያመላክተው የሰው ልጅ ዝርያ የድንጋይ መሣርያን ለመጀመርያ ጊዜ ሠርቶ መጠቀም የጀመረበት ጊዜ ከዚህ በፊት ከነበረው መረጃ 50,000 እና 100,000 ዓመት ሊቀድም እንደሚችልአፋር ሌዲ ገራሩ ልዩ ስሙ በኮል ዶራ በተባለ አዲስ የጥናት ቦታ የተገኙ የጥንት የድንጋይ መሣርያዎች ያስረዳሉ::

መሰንበቻውን የቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን 2.6 ሚሊዮን ዓመታት ያስቆጠረ የድንጋይ መሣርያ በአፋር መገኘቱን ይፋ አድርጓል፡፡

- Advertisement -

የባለሥልጣኑ አዲሱ ዋና ዳይሬክተር ሙሉጌታ ፍሥሐ (ዶ/ር) በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት፣ ከዚህ በፊት ሦስት ነጥብ ሦስት ሚሊየን ዓመት ያስቆጠረ የድንጋይ መሣሪያ በኬንያ የተገኘ ቢሆንም የሰው ልጅ ይጠቀምባቸው እንደነበር ማረጋገጫ አልነበረም።

ጥንታዊ የድንጋይ መሣሪያ ለማግኘት በሚደረገው ጥናት ኢትዮጵያውያን ባለሙያዎች በመሳተፋቸው የዕውቀት ሽግግር ሲደረግ ቆይታል ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ፣ ኢትዮጵያ የሰው ዘር አመጣጥን በተመለከተ በአይነትም በብዛትም በርካታ ቅሪተ አካል የተገኙባት በመሆኗ፣ እንዲሁም ከዚህ በፊትም ሌላ የድንጋይ መሣሪያ በመገኘቱ ለሳይንስ የምታበረክተውን አስተዋፅኦ የሚያሳይ ነው ብለዋል።

አራት ዓመት ገደማ በፊት 2.78 ሚሊዮን ዓመታትን ያስቆጠረ የሆሞEarliest Homoዝርያ ቅሪተ አካል በዚህ የድንጋይ መሣርያ በተገኘበት አካባቢ መገኘቱ ይታወቃል። ይህ የድንጋይ መሣርያ በተገኘበት አካባቢ ጂኦሎጂካል ጥናት ሲያካሂዱ የነበሩት /ር ክሪስ ካምፒሳኖ አርኪዮሎጂካል ቅርሶቹንአጋጣሚ እንዴት እንዳገኟቸው የገለጹትን ቅርስ ጥናትና ጥበቃ ባለሥልጣን በማኅበራዊ ገጹ እንዲህ ገልጾታል፡-

በመጀመርያ ሰርፌስ ላይ ብዙ የድንጋይ መሣርያዎችን ተመለከትን። ከየትኛው የአፈር ደለል/ክምችት እንደመጡ ግን አላወቅንም ነበር። በኋላ ግን ወደ ሆነች ትንሽ ክሊፍ (ገደላማ) ቀረብ ስል የድንጋይ መሣርያዎችን አየሁና ከየትኛው የአፈር ደለል/ክምችት እንደመጡ በሚገባ ተረዳሁኝ። ይኼንን ለአርኪዮሎጂስቶች ስነግራቸውም መጥተው እስኪያዩ ድረስ ሊያምኑኝ አልቻሉም ነበር፡፡’’

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር 2012 ጀምሮ የአርኪዮሎጂ ቡድን በዚህ በኮል ዶራ በተባለው ሥፍራ ላይ ቁፋሮ እያደረገ ቆይቷል፡፡ በእነዚህ ዓመታት ውስጥ በተደረገ የመስክ ሥራም የተለያዩ የድንጋይ መሣርያዎችንና የተለያዩ የእንስሳት ቅሪተ አካላትን በቁፋሮ ማግኘት ተችሏል። የአካባቢውን ሥነ ምኅዳር የሚያጠኑት ፕሮፌሰር ከይ ሪድ እንደሚሉት ከእነዚህ የድንጋይ መሣርያዎች ጋር የተገኙት የእንስሳት ቅሪቶች በሌዲ ገራሩ ሊዓዶይታEarliest Homoየተገኘበት ሆኖ ከበኮል ዶራ አምስት ኪሎ ሜትር ርቀት የሚገኝ ነው። ይኼም የድንጋይ መሣርያዎቹንና የሆሞ ቅሪተ ኣካል ግንኙነትን ያሳያል። በዚህም መሠረት እነዚህን የድንጋይ መሣርያዎች ይሠሩ ከነበሩት የሰው ልጅ ዝርያዎች መካከል በዚሁ አካባቢ ይኖር የነበረው የሆሞ ዝርያ አንዱ ሊሆን እንደሚችል ይታመናል።

በቅርብ ዓመታት የተካሄዱ የመስክ ጥናቶች ጠቅሰው መግለጫውን የሰጡት የጥናቱ አስተባባሪ ዴቪድ ብራውን (ዶ/ር) እንደገለጹት ከሆነ የድንጋይ መሣርያን የሚጠቀመው የሰው ልጅ ብቻ ሳይሆን የችምፓንዚና የመንኪ ዝርያዎችም የተለያዩ ሥራዎችን ለማከናወን ንጋይ የተሠሩ መሣርያዎችን ይጠቀሙ ነበር። በዚህ ፋር በኩል ዶራ በተባለው ሥፍራ ላይ የተገኙት የጥንት የድንጋይ መሣርያዎች ግን ችምፓንዚና የመንኪ ዝርያዎች ከሚሠሯቸው ጋር ሲነፃፀሩ በአሠራር ጥበባቸው፣ ቅርጽ፣ ቴክኖሎጂና አጠቃላይ ገጽታቸው የተለዩ ሆነው ተገኝተዋል ይላል ጥናቱ።

 የሰው ልጅና የቅርብ ዘመዶቹ በአካባቢያቸው የሚገኙትን የተለያዩ ሪሶርሶችን ለመጠቀም የድንጋይ መሣርያን ይጠቀሙ እንደነበሩ የሚያሳዩ በርካታ መረጃዎች እንደመኖራቸው አንፃር በአፍሪካ ይኖሩ የነበሩት የሰው ልጅ ዝርያዎች ለየት ያለ የድንጋይ መሣርያዎች አጠቃቀምን ማስተር ሳያደርጉ እንዳልቀሩ በጆርጅ ዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ የአርኪዮሎጂ መምህር / ዴቪድ ብራውን ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...