Friday, July 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ይድረስ ለሪፖርተርእሑድ ግንቦት 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ባወጣነው ዕትም ማረሚያ

እሑድ ግንቦት 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ባወጣነው ዕትም ማረሚያ

ቀን:

እሑድ ግንቦት 25 ቀን 2011 ዓ.ም. ባወጣነው ዕትም ‹‹ኢንሳ በፖለቲካ ሪፎርም ሳቢያ የለቀቁ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ወሳኝ መረጃ እንዳፈተለኩበት ገለጸ›› በሚል ርዕስ በፊት ገጽ ላይ ዜና መውጣቱ ይታወሳል፡፡ ነገር ግን በዚህ ዘገባ ዝግጅት ወቅት በተለይም ቴክኒካዊ የሆኑ እውነቶች ወደ አገርኛ ቋንቋ መመለስ ሒደት ላይ አንዳንድ ግድፈቶች መፈጠራቸውን አስተውለናል፡፡ በዚህ መሠረት አንባቢያን በተለይ በዜናው ርዕስና የመጀመርያ አንቀጽ ላይ የሰፈረውን ጨምሮ፣ አንዳንድ አገላለጾች ተስተካክለው እንዲያነቡልን በትህትና እንጠይቃለን፡፡

በዚህ መሠረት የዜናው ርዕስ ‹‹ኢንሳ ሚስጥራዊ ቋቶቹ ተሰብረው መረጃ አፈትልከዋል መባሉን አስተባበለ›› በሚል ተስተካክሎ እንዲነበብ እየጠየቅን፣ የቀዳሚ አንቀጹ ደግሞ ‹‹የኢትዮጵያ የሳይበር የማስበቅ ኃላፊነት የተጣለበት የመረጃ መረብ ደኅንነት ኤጀንሲ (ኢንሳ) ባለፈው አንድ ዓመት ውስጥ በተከሰተው የፖለቲካ ለውጥ ሳቢያ በተቋሙ ይሠሩ የነበሩ ኃላፊዎችና ሠራተኞች ከሥራቸው ያለ ቅድመ ማስጠንቀቂያ መልቀቃቸውን ቢያምንም፣ ከሰሞኑ የወጡ ወሳኝ መረጃዎች በብርበራ አፈትልከዋል የሚሉ ዘገባዎችን ግን አስተባብሏል፤›› በሚል ተስተካክለው እንዲነበቡ እንጠይቃለን፡፡ ከዚህ ባለፈ በሁለተኛው አንቀጽም፣ ‹‹ቁጥራቸው ያልተገለጹ የኤጀንሲው ኃላፊዎችና ሠራተኞች መልቀቃቸው የራሱ የሆነ ጫና እንዳሳደረበት ያመኑት ተጠባባቂ የኮሙዩኒኬሽን ኃላፊው አቶ ሰለሞን ተስፋዬ፣ በቀጣይ ወራት ተቋሙ የሪፎርም ዕርምጃዎችን እየወሰደ እንዳለ አክለው ገልጸዋል፤›› በሚል ተተክቶ ይነበብ፡፡

በመጨረሻም በዘገባው ላይ ‹‹ወሳኝ ሚና›› እና ‹‹ወሳኝ መረጃ›› የሚሉት አገላለጾች፣ ‹‹ሚና›› እና ‹‹መረጃ›› ተብሎ ብቻ እንዲነበብ እየገለጽን ለተፈጠረው ስህተት ይቅርታ እንጠይቃለን፡፡

የዝግጅት ክፍሉ

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የሰብዓዊ መብት ጉዳይና የመንግሥት አቋም

ሰኔ ወር አጋማሽ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) ከፍተኛ የሰብዓዊ...

ከሰሜኑ ጦርነት አገግሞ በሁለት እግሩ ለመቆምና ወደ ባንክነት ለመሸጋገር የተለመው ደደቢት ማክሮ ፋይናንስ

በኢትዮጵያ የፋይናንስ ኢንዱስትሪ ውስጥ በቀዳሚነት ስማቸው ከሚጠቀሱት ውስጥ ደደቢት...