የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ የቀድሞ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው አሰፋ የት እንደሚገኙ ስላማያውቅና መጥሪያም ለማድረስ ስላልቻለ፣ በጋዜጣ እንዲታወጅለት ፍርድ ቤትን ጠየቀ፡፡ ፖሊስ አቶ ጌታቸውን ፈልጎ ማግኘት አልተቻለም ብሏል፡፡
ስለዚህም ክሳቸው ከ14 ዓመታት በላይ ሊያስቀጣ የሚችል በመሆኑ በሌሉበት መታየት እንደሚችል በማሳወቅ በጋዜጣ እንዲታወጅ ተጠይቋል፡፡ ፍርድ ቤቱም በክሱ ትግራይ ክልል ተባለ እንጂ ትክክለኛ አድራሻቸው የት እንደሆነ ስላልተገለጸ፣ አድራሻው እንዲጠቀስ አሳስቧል፡፡
ፖሊስም ትግራይ ክልል ላሉ የፌዴራል ፖሊስ ባልደረቦች በፋክስ መልዕክት ቢላክም፣ የአቶ ጌታቸውና የሌሎች አራት ተጠርጣሪዎች አድራሻቸው በትክክል ባለመታወቁ መጥሪያ ለማድረስ አልተቻለም ብሏል፡፡
ፍርድ ቤቱም በጉዳዩ ላይ ብይን ለመስጠት ቀጠሮ ሰጥቷል፡፡