Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ክስ የተመሠረተባቸው የተፋጠነ ፍትሕ ልናገኝ ይገባል አሉ

የሶማሌ ክልል የቀድሞ ፕሬዚዳንትን ጨምሮ ክስ የተመሠረተባቸው የተፋጠነ ፍትሕ ልናገኝ ይገባል አሉ

ቀን:

ተጨማሪ የተያዙ ተከሳሾች በክሱ የተካተተው ስም የእነሱ አለመሆኑን ተናገሩ

በሶማሌ ክልል ከሐምሌ 26 እስከ 30 ቀን 2010 ዓ.ም. ድረስ በጅግጅጋ ከተማና ሌሎች የወረዳ ከተሞች ተከስቶ በነበረው ረብሻና ሁከት በደረሰው ጉዳት፣ ከአሥር ወራት በፊት በእስር ላይ የሚገኙትና ክስ የተመሠረተባቸው የክልሉ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እነ አቶ አብዲ መሐመድ (አብዲ ኢሌ) የተፋጠነ ፍትሕ ሊያገኙ እንደሚገባ ለፍርድ ቤቱ አመለከቱ፡፡

አቶ አብዲ መሐመድ፣ ወ/ሮ ረሂማ መሐመድ፣ አቶ አብዱራዛቅ ሳኒ፣ ኮሚሽነር ፈሪሃን ጣሂርን ጨምሮ ከስምንት በላይ ተከሳሾች ሰኔ 3 ቀን 2011 ዓ.ም. በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አራተኛ ወንጀል ችሎት የቀረቡ ሲሆን፣ ችሎቱ በዋናነት ቀጠሮ ይዞ የነበረው በቁጥጥር ሥር ያልዋሉ ተከሳሾችን የፌዴራል ፖሊስ ከክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ክትትል በማድረግ መቅረባቸውን ለመጠባበቅ ነበር፡፡

በመሆኑም ስምንት ተጠርጣሪ ተከሳሾች በቁጥጥር ሥር ውለው መቅረባቸውን ዓቃቤ ሕግ ለፍርድ ቤቱ አሳውቋል፡፡ ነገር ግን ተይዘው የቀረቡት ተከሳሾች፣ በክስ መዝገቡ በተያዘው ስም ሲጠሩ መኖራቸውን ከማረጋገጥ ይልቅ ዝምታን መርጠዋል፡፡ ምክንያታቸውን ሲጠየቁ ስማቸው እንዳልሆነ ተናግረዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግ ግን ተከሳሾቹ ራሳቸው መሆናቸውን ጠቁሞ፣ በአሁኑ ወቅት ስማቸውን እያስቀየሩና አዲስ መታወቂያ እያቀረቡ መሆኑን በማስረዳት በክሱ ላይ በተቀመጠው ስማቸው ወይም ራሳቸው በሚያስመዘግቡት ስም ክርክሩ እንዲቀጥል ለፍርድ ቤቱ አመልክቷል፡፡

የተከሳሾች ጠበቆች በበኩላቸው ባቀረቡት መቃወሚያ ዓቃቤ ሕግ ተከሳሾች መሆናቸውን ጠቅሶ ያቀረበ ቢሆንም፣ በስም ማረጋገጥ አልቻለም፡፡ ፆታው ወንድ ነው የተባለ ተከሳሽ ተይዞ ሲቀርብ ሴት ሆና በተገኘችበት ሁኔታ፣ ዓቃቤ ሕግ እየሠራ ነው ማለት እንደማይቻልም አክለዋል፡፡ ድርጊቱም የተከሳሾችን መብት የሚጎዳ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከሳሽ በየቀጠሮው ሁለትና ሦስት ሰዎችን እያቀረበ ባለበት ሒደት የታሰሩ ተከሳሾች መብት እየተጣሰ መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ የክርክሩን ተገማችነትም ግምት ውስጥ የሚያስገባ መሆኑንም አክለዋል፡፡ ተከሳሾቹ ከምርመራ ወቅት ጀምሮ ከአሥር ወራት በላይ ተፈልገው ሊገኙ ስላልቻሉ፣ በእስር ላይ ያሉ ተከሳሾች የተፋጠነ ፍትሕ የማግኘት መብታቸው ጥያቄ ውስጥ መግባቱንም ተናግረዋል፡፡ ዓቃቤ ሕግም ሆነ ፖሊስ ሥራቸውን በትጋት መሥራት ሲገባቸው፣ ባለመሥራታቸው በእስር ላይ ያሉ ተከሳሾች የመዳኘት ሕገ መንግሥታዊ መብታቸው ሊጠበቅላቸው እንዳልቻለ ጠቁመዋል፡፡

በተከሳሾቹ ጠበቆች የቀረበው መቃወሚያ ተገቢነት የሌለው መሆኑን በመጥቀስ ዓቃቤ ሕግ ምላሽ ሰጥቷል፡፡ በዕለቱ ያቀረባቸው ስምንት ሰዎች ተከሳሾች መሆናቸውን ጠቁሞ፣ ፖሊስ ከፍተኛ ጥረት እያደረገ መሆኑንና ዓቃቤ ሕግም ፍርድ ቤቱ የሰጠውን ትዕዛዝ ተከትሎ አስፈላጊውን ጥረት እያደረገ ቢሆንም፣ ያልተያዙ ተከሳሾች ግን ስማቸውን የመቀየርና በፍርድ ቤት የመካድ አባዜ ውስጥ መሆናቸውን አስረድቷል፡፡ መንግሥት ሠርቶ በሰጣቸው ቤት አድራሻ ሊገኙ ያልቻሉ ስድስት ተከሳሾች፣ በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው ትዕዛዝ እንዲሰጥለትና ቀሪዎቹን አፈላልጎ ለማቅረብ ተጨማሪ ጊዜ እንዲሰጠው ጠይቋል፡፡

የግራ ቀኙን ክርክር የሰማው ፍርድ ቤት በችሎት ቀርበው ማንነታቸው በተረጋገጠውና በክሱ ላይ በተጠቀሰው ስም መካከል ልዩነት መኖሩን ማረጋገጡን ጠቁሞ፣ በቀጣይ ቀጠሮ መታወቂያ ይዘው እንዲቀርቡ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ ዓቃቤ ሕግም አጣርቶ ማረጋገጫ እንዲያቀርብ ትዕዛዝ ሰጥቷል፡፡ በአጠቃላይ በዕለቱ የቀረቡ ተከሳሾችን በሚመለከት የተሰጠውን ትዕዛዝ ሐሙስ ሰኔ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ታይቶ፣ ባልቀረቡት ተከሳሾች ላይ ማለትም በጋዜጣ ጥሪ እንዲደረግላቸው በተጠየቀውና ተጨማሪ ጊዜ በተጠየቀባቸው ላይ ትዕዛዝ እንደሚሰጥ አስታውቋል፡፡         

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...