Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፌዴሬሽኑና ፖሊስ በፕሪሚየር ሊጉ ፀጥታ ጉዳይ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል

ፌዴሬሽኑና ፖሊስ በፕሪሚየር ሊጉ ፀጥታ ጉዳይ ለመነጋገር ቀጠሮ ይዘዋል

ቀን:

በፀጥታ ችግር በተለይም ከኢትዮጵያ ቡናና ከመቐለ 70 እንደርታ ጨዋታ ጋር በተያያዘ ላልተወሰነ ጊዜ የተቋረጠው የፕሪሚየር ሊጉ መርሐ ግብር፣ መካሄድ እንዲጀምርና ቀሪዎቹ ጨዋታዎችን በተመለከተ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑና ፌዴራል ፖሊስ ለመነጋገር ቀጠሮ መያዛቸው ተሰማ፡፡

የሪፖርተር ምንጮች እንደገለጹት ከሆነ፣ የተቋረጡትን የሊጉን ጨዋታዎች ለማስጀመርና ለፀጥታው ችግር ዕልባት ለመስጠት ረቡዕ ሰኔ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ስብሰባ ለማካሄድ ተዘጋጅተዋል፡፡

በሌላ በኩል የፌዴሬሽን አመራሮች በኢትዮጵያ ቡናና በመቐለ 70 እንደርታ መካከል ሳይካሄድ የተቋረጠውን ቀሪ ጨዋታ ለማከናወን የሚያስችል መግባባት  እንዳልፈጠሩ ታውቋል፡፡

የእግር ኳስ ፌዴሬሽን አመራሮች ለዓመታት ከተከናወኑት መርሐ ግብሮች በተለየ አኳኋን የዘንድሮ የፕሪሚየር ሊግ ውድድሮች በታቀደላቸው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት ለማጠናቀቅ በማቀድ ከወትሮው ቀደም ብለው ለማጠናቀቅ ሲንቀሳቀሱ ቆይተዋል፡፡ ይሁንና በፀጥታ ችግር ሳቢያ ቀሪ ጨዋታዎች በእንጥልጥል የቀሩት፣ ቡናና መቀሌ 70 እንደርታ፣ በአዲስ አበባ ስታዲዮም ሊያካሂዱት ጥቂት ሰዓት እስኪቀረው ድረስ ሲጠበቅ የቆየው ጨዋታ እርስ በርሳቸው በሚጣረሱ ውሳኔዎች ታጅቦ እስካሁን በመቋረጡ ነው፡፡ ይህም በመሆኑ በተያዘው የጊዜ ሰሌዳ መሠረት የሊጉ ውድድር እንዳይጠናቀቅ ተፅዕኖ ማሳደሩ እንደማይቀር እየተነገረ ይገኛል፡፡

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጂራ በበኩላቸው፣ እሳቸውና ምክትላቸው ባልተገኙበት ስብሰባ ላይ በተወሰነው ውሳኔ መሠረት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲቋረጥ የተደረገው የሊጉ ፕሮግራም፣ ዳግም በሚካሄድበትና የፀጥታ ጉዳይ መፍትሔ በሚያገኝበት አግባብ ላይ ከፌዴራል ፖሊስ ጋር ሲነጋገሩ መሰንበታቸው፣ ብሎም ለመጨረሻ ጊዜም ሰኔ 5 ቀን 2011 ዓ.ም. ተነጋግረው ውድድሩን ዳግመኛ ለማስጀመር ማቀዳቸው ታውቋል፡፡

በ27ኛው ሳምንት የፕሪሚየር ሊግ መርሐ ግብር በፀጥታ ችግር እንዲቋረጥ ተደርጎ በገለልተኛ ሜዳና  በዝግ ስታዲዮም አዳማ ከተማ ላይ እንዲከናወን በተወሰነው፣ የሁለቱ ክለቦች ጨዋታ ላይ ኢትዮጵያ ቡና የተቀጣበት አግባብ ‹‹ትክክል ነው›› ‹‹አይደለም›› በማለት በፌዴሬሽኑ አመራሮች መካከል አለመግባባት መፈጠሩ ታውቋል፡፡

የፌዴሬሽኑ አብዛኛው አስፈጻሚ አባላት፣ በሊግ ኮሚቴው አማካይነት የተላለፈውና ክለቦቹ በገለልተኛና በዝግ ስታዲዮም ይጫወቱ የሚለው ውሳኔ ኢትዮጵያ ቡናን የሚጎዳው በመሆኑ ውሳኔው ሊሻር እንደሚገባው፣ የተፈጠረውን የፀጥታ ችግርም የሁለቱም ክለቦች አመራሮችንና ደጋፊዎችን በማነጋገር ሰላም እንዲያወርዱና ጨዋታውም እንዲከናወን ፍላጎት ያላቸው እንዳላቸው ተሰምቷል፡፡

በገለልተኛና በዝግ ስታዲዮም ይጫወቱ የሚለው ውሳኔ ተፈጻሚነት ሊኖረው ይገባል በማለት በሌላ ወገን የሚከራከሩ አመራሮችም በዚሁ አቋማቸው ሳቢያ በፌዴሬሽኑ አመራሮች መካከል አለመግባባት መከሰቱን ምንጮች ለሪፖርተር ተናግረዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...