አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች
- 5 የተቀቀለ እንቁላል
- 2 የቡና ስኒ (200 ግራም) በሙቅ ውኃ ለግማሽ ሰዓት የተዘፈዘፈ የምስር ክክ
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (300 ግራም) የደቀቀ ቀይ ሽንኩርት
- 3 የሾርባ ማንኪያ አዋዜ
- 2 የሾርባ ማንኪያ ርጥብ ቅመም
- 1 የሾርባ ማንኪያ ምጥን ሽሮ
- ግማሽ የሻይ ማንኪያ ምጥን ሽንኩርት
- 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) ዘይት
- 1 እግር ርጥብ በሶብላ
- 1 የሻይ ማንኪያ መከለሻ
- 1 የሻይ ማንኪያ ጨው
- 6 የሾርባ ማንኪያ (100 ሚሊ ሊትር) በጠጅ ወይም በውኃ የተበጠበጠ ርጥብ ቅመም
አዘገጃጀት
1. ቀይ ሽንኩርቱን በውኃ ብቻ ማቁላላት፤
2. ምጥን ሽንኩርቱን ጨምሮ ማቁላላት፤
3. ውኃው ሲመጥ ትንሽ ውኃ እያደረጉ ማማሰል፤
4. ዘይት መጨመር፤
5. ዘይቱና ሽንኩርቱ ብቻ እስኪቀር ማማሰል፤
6. አዋዜ ጨምሮ ማሸት፤
7. ውኃው ሲመጥ አዋዜው እንዳያር ሙቅ ውኃ ጠብ እያደረጉ ማማሰል፤
8. ርጥብ ቅመም ጨምሮ ትንሽ ማንተክተክ፤
9. ምስሩን ጨምሮ ማብሰልና ሽሮውን ጨምሮ ማንተክተክ፤
10. ምስሩ ሲበስል በጠጅ ወይም በውኃ የተበጠበጠውን ርጥብ ቅመም መጨመር፤
11. መከለሻና ጨውን አስተካክሎ በሶብላ ጨምሮ ማውጣት፤
12. እንቁላሉን በሹካ ወጋ፣ ወጋ አድርጐ መጨመርና ለገበታ ማቅረብ፡፡
(ደብረወርቅ አባተ፤ የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት፣ 2002)