Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበመርህ መመራትና መደማመጥ የናፈቀው እግር ኳሱ በነሲብ ውሳኔዎች ታምሷል

በመርህ መመራትና መደማመጥ የናፈቀው እግር ኳሱ በነሲብ ውሳኔዎች ታምሷል

ቀን:

የእግር ኳሱ ሰሞነኛ ትኩሳት ዘርፉን የሚመራውን አካል አጣብቂኝ ውስጥ ከቶታል፡፡ በሁለት ክለቦች መካከል ሊካሄድ የነበረው ጨዋታ ‹‹የፀጥታ ሥጋት አለ›› በመባሉ ምክንያት በተደጋጋሚ ተቋርጧል፡፡

ይሁንና ውሳኔዎች በተደጋጋሚ ሲሻሩና ሲከለሱ መክረማቸው የስፖርቱን አመራር አካላት ጥያቄ ላይ ጥሏቸዋል፡፡ አመራሩ በሁለት ክለቦች ጉዳይ ላይ በአንድ ሳምንት ውስጥ ከስድስት ጊዜ በላይ ተሰብስቧል፡፡

የእግር ኳስ ስፖርት እንዲህ ያሉ ያልታሰቡና ከቁጥጥር ውጪ የሆኑ የፀጥታና  ሌሎችም አሳሳቢ ጉዳዮች ላይ ቆፍጣናና የማያወላዳ፣ ለየትኛውም ወገን ያላደላ ውሳኔ ማሳለፍ የሚሳነው፣ ሲወስንም ርትዕ ያጠረውና ተገዥነት የጎደለው ሆኖ በመታየቱ በክለቦቹ ጠንካራ ጩኸት እዚህም እዚያም ሲዋልል ከርሟል፡፡ ይህም ተቋማዊ ገጽታው ላይ ተዓማኒነቱና መዋቅሩ ሁሉ ዳግም መፈተሸ እንደሚያስፈልገው የሰሞኑ ድራማዊ ክስተት ምስክር እንደሚሆን የሚገልጹ አሉ፡፡

ከተቋሙ ውጭ ያሉ ግፊቶችን በተለይም እንደ ፀጥታ ተቋማት ያሉት አስቸኳይና አሳሳቢ ጉዳይ በገጠማቸው ወቅት ጣልቃ የሚገቡበት መንገድ ግብታዊ መሆኑም ጥያቄ አጭሯል፡፡ በፀጥታ ጉዳይ ጨዋታዎች መቋረጣቸው ያስከተለው ተፅዕኖ በአንድ ወገን የሚታይ ሆኖ፣ ይህንኑ በፀጋ ተቀብለው ሲጠባበቁ ዱብ ዕዳ ውሳኔዎች የሚተላለፍባቸው ክለቦች፣ ይህንኑ ሲሞግቱም እንደ ተቋም አብሮ ከመነጋገርና ከመግባባት ይልቅ የአንድ አቅጣጫ ውሳኔዎች አንዴ ሲተላለፉ መልሰው ሲቀለበሱና ዳግም ሲተላለፉ የእልህና የግብታዊነት እንጂ፣ የመርህና የሥርዓት ግንኙነት አልመስል ያላቸው የስፖርቱ ታዛቢዎች ግራ መጋባቸውን ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡

በአሁን ወቅት የሚታየው የተቋሙ ቁመና፣ በእግር ኳሱ ሽፋን ጫፍ የደረሰው ዘረኝነት ሲታከልበት፣ ነገሮች ወዳልተፈለገ አቅጣጫ እንዳያመሩ ሥጋት ያደረባቸው እንዲበረክቱ ምክንያት መሆኑ አልቀረም፡፡

የብሔራዊ እግር ኳስ ፌዴሬሽኑ አመራሮች ሊጉን በበላይነት ለማስተዳደር በጠቅላላ ጉባዔ የተሰጣቸውን ኃላፊነት በመርህ፣ በደንብና በመከባበር ላይ ተመሥርተው፣ ውሳኔዎቻቸውንም ከማሠለፋቸው በፊት፣ በጋራ የወጡ ደንቦችና መመርያዎችን ዓይተው፣ ተነጋግረውና ተደማምጠው መወሰን እየተሳናቸው በምትኩ ጎራ ለይተው ለሚፈጥሩት ንትርክና እሰጥ አገባ ሌላ ዳኛ ማስፈለጉ በተቋሙም ሆነ በሊጉ የወደፊት ዕጣ ፈንታ ላይ ሥጋት ፈጥሯል፡፡

ለዚህ ሁሉ መነሻው የኢትዮጵያ ቡናና የመቐሌ 70 እንደርታ የ27ኛ ሳምንት የፕሪምየር ሊጉ ጨዋታ በፀጥታ ሥጋት ሳቢያ በተያዘለት መርሐ ግብር አለመከናወኑን ተከትሎ የተፈጠረው አለመግባባት ነው፡፡ የተቋረጠው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ከነበረው የፀጥታ ሥጋት በመነሳት እንዴት ይከናወን በሚለው ላይ ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ያሳለፋቸው ውሳኔዎች ግብታዊና የዜጎችን ሰላማዊና ማኅበራዊ ግንኙነት ወዳልተፈለገ አቅጣጫ የወሰዱ መሆናቸው ችግሩን ከድጡ ወደ ማጡ አድርጎት ሰንብቷል፡፡

አንድ ጊዜ በዝግና በገለልተኛ፣ ሌላ ጊዜ በዝግ ሜዳ ይህም ተቀባይነት ሲያጣ ደግሞ በምሽት እየተሰበሰቡ ለንጋት አጥቢያ ውሳኔ በማሳለፍ ተመልካች በሚገኝበትና በሌለበት ይካሄድ የሚሉ አጨቃጫቂና ከስምምነት መድረስ ያላስቻሉ ዕርምጃዎች በመወሰዳቸው፣ የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ ‹‹ይደረጋል፣ አይደረግም›› በሚለው ላይ ቁርጡን መናገር ቢቸግርም፣ ማክሰኞ ሰኔ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ስታዲዮም ተመልካች በተገኘበት እንዲከናወን መባሉ ተሰምቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...