Sunday, February 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበአዲስ አበባ የኮሌራ ክትባት ተጀመረበአዲስ አበባ የኮሌራ ክትባት ተጀመረ

በአዲስ አበባ የኮሌራ ክትባት ተጀመረበአዲስ አበባ የኮሌራ ክትባት ተጀመረ

ቀን:

17,000 ሰዎች ይከተባሉ

የኢቦላ ወረርሽኝ እንዳይገባ ቅድመ ዝግጀት እየተደረገ ነው

በአዲስ አበባ ለኮሌራ ወረርሽኝ ተጋላጭነት ላላቸው 17,000 ያህል ሰዎች ወረርሽኙን ለመከላከል የሚያስችል ክትባት መስጠት ተጀመረ፡፡ የኢቦላ ወረርሽኝም ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎች በመከናወን ላይ መሆኑን የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የኢንስቲትዩቱ ምክትል ዋና ዳይሬክተር በየነ ሞገሥ (ዶ/ር) እንደገለጹት፣ በመጀመርያው ዙር በሚካሄደው የክትባት ዘመቻ፣ ፌዴራል ማረሚያ ቤቶች፣ አዳሪ ትምህርት ቤቶች፣ አረጋውያንና የአዕምሮ ሕሙማን እንዲሁም በጎዳና ሕፃናት ማዕከላት ለሚገኙ የኅብረተሰብ ክፍሎችና በዚህ ሥራ ላይ ብቻ የተሰማሩ የጤና ባለሙያዎች የሚከተቡ ይሆናል፡፡

ተጋላጭ የሆኑ የኅብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት ክትባቱ የሚቀጥል መሆኑን አመልክተው፣ ክትባቱን ለሚሰጡ ባለሙያዎችም ትናንት ሥልጠና መሰጠቱን አስረድተዋል፡፡

እንደ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ገልጻ፣ በኢትዮጵያ በኮሌራ ወረርሽን የተያዙ ሰዎች ቁጥር 614 ደርሷል፡፡ ከእነዚህም መካከል በኦሮሚያ ክልል በምዕራብ ሐረርጌ ዞን በጭሮ ወረዳ 74፣ በኦዳ ቡልቱም ወረዳ 128፣ በሜኤሶ ወረዳ 34፣ ገመቺስ ወረዳ ዘጠኝ፣ እንዲሁም በበዴሳ ከተማ 42 በፊንፊኔ ዙሪያ የኦሮሚያ ልዩ ዞን በሰንዳፋ ከተማ ስድስት እንዲሁም በበርኽ ወረዳ አንድ፣ በአጠቃላይ 294 ሰዎች በበሽታው የተያዙ ሲሆን፣ እስካሁን የሁለት ሰዎች ሕይወት በበሽታው ምክንያት አልፏል፡፡

በአዲስ አበባ በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ 22፣ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ 17፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ስድስት፣ በልደታ ክፍለ ከተማ አምስት፣ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ አንድ፣ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ ከተማ ስምንት፣ በጉለሌ ክፍለ ከተማ ሁለት፣ በቦሌ ክፍለ ከተማ አንድ፣ እንዲሁም በአራዳ ክፍለ ከተማ ስድስት፣ በአጠቃላይ 70 ሰዎች የበሽታው ምልክት ታይቶባቸው ሕክምና ተደርጎላቸው ወደ መደበኛ ሕይወታቸው ተመልሰዋል፡፡ በአዲስ አበባ በለይቶ ማቆያ የተኛ ታካሚም ሆነ በወረርሽኙ የሞተ ሰው እንደሌለ ተናግረዋል፡፡

በድሬዳዋ አስተዳደር አንድ ሰው በበሽታው እንደተያዘ፣ ውጤቱም በላብራቶሪ ተመርምሮ ቪብሮ ኮሌራ መሆኑ እንደተረጋገጠና ሰውየውም የድሬዳዋ ነዋሪ ሳይሆን ከምዕራብ ሐረርጌ የመጣ ሰው እንደሆነ ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ አመልክተዋል፡፡

በትግራይ ክልል በምሥራቃዊ ዞን ክልተአውላዕሎ ወረዳ፣ አዲግራት ከተማ እንዲሁም በመቀለ ዙሪያ ሰሜንና አዲሃቂ ክፍለ ከተሞች፣ በአጠቃላይ 18 ሰዎች በበሽታው ተይዘዋል፡፡

ወረርሽኙ በተከሰተባቸው ክልሎች በበሽታው የተያዙ ሰዎችን ለይቶ ለማከም የሚያስችሉ በአጠቃላይ 18 ለይቶ የማከሚያ ማዕከላት የተቋቋሙ ሲሆን፣ ከእነዚህም ዘጠኙ በኦሮሚያ ይገኛሉ፡፡ ማዕከላቱ በኦዳቡልቱም 1፣ በጪሮ 4፣ በሰንዳፋ ከተማ 1 እና በሜኤሶ 3፣ በአዲስ አበባ 2 (ድል ፍሬ አንድና አዲስ ከተማ 1)፣ በትግራይ ክልል 1 (በመቀሌ አዲሃቂ 1) እንዲሁም በአማራ ክልል 6 (አበርጌሌ ወረዳ 3፣ ዓባይ ማዶ ህርዳ 1 እና ጠለምት 2 ናቸው፡፡

ከምክትል ዋና ዳይሬክተሩ ማብራሪያ ለመረዳት እንደተቻለው፣ ከኢትዮጵያ የእስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት (መጅሊስ) ጋር የኮሌራ በሽታ መከላከል ስለሚቻልባቸው መንገዶች፣ በተለይም የእምነቱ ተከታዮች ማድረግ ስለሚገባቸው ጥንቃቄ ውይይት ተደርጓል፡፡ በመጅሊሲ በኩል በየመስጊዱ በጎ ፈቃደኞችን መድበው እንደሚሠሩ መግባባት ላይ ተደርሷል፡፡ እንዲሁም ከአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ጋር ውይይት ተካሂዶ በትምህርት ቤቶች የግንዛቤ ማስጨበጫ ፕሮግራም እንዲጀመር ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

‹‹በኬንያ በኬሮቾ ካውኒቲ አንድ ሰው በኢቦላ ቫይረስ በሽታ የተጠረጠረ ሲሆን፣ ውጤቱም ኔጌቲቭ መሆኑ ተረጋግጧል፡፡ ይሁንና ጉዳዩን በጥብቅ እየተከታተልነው እንገኛለን፡፡ ወረርሽኑ ወደ አገራችን እንዳይገባ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወንን እንገኛለን፡፡ ከቅድመ ዝግጅት ሥራዎች መካከልም በቦሌ ዓለም አቀፍ የአውሮፕላን ጣቢያ የተጓዦችን የሙቀት መጠን የልየታ ሥራ እየተከናወነ መገኘቱ ተጠቃሽ ነው፤›› ብለዋል፡፡  

በአውሮፕላን ማረፊያ ጣቢያውም በበሽታው የተያዙ መንገደኞች ቢያጋጥሙ ለይቶ ለማከም የሚያስችል ቦታ እንደተዘጋጀ፣ ከዚህም በተጨማሪ በቦሌ ጨፌ የኢቦላ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል እንደተቋቋመ፣ ሕክምናውን መስጠት የሚችሉ ባለሙያዎችም በተለያዩ ጊዜያት እየሠለጠኑ እንደሚገኙ ነው የተናገሩት፡፡

በሌላ መልኩ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ መንገደኞች ከገቡበት ዕለት ጀምሮ ለ21 ቀናት ባረፉበት ቦታዎች የሕክምና ክትትል እየተደረገ ይገኛል፡፡ ከሜይ 8 ቀን 2018 ጀምሮ ከ15 ሺሕ በላይ ከዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የመጡ መንገደኞች ላይ የልየታ ሥራ የተከናወነ ሲሆን፣ ከእነዚህም ውስጥ 1,882 መንገደኞች ላይ ለ21 ቀናት ክትትል ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ወቅት 214 መንገደኞች ባረፉበት ቦታ ሆነው ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል፡፡

የችኩንጉኒያ ወረርሽኝ በሶማሌ ክልል ቀብሪ ዳሃር ከተማ 115 ሰዎች ላይ ተከስቷል፡፡ በተጨማሪም በአካባቢ ከሚገኘው የመከላከያ ካምፕ 25 ታማሚዎች መኖራቸው ተረጋግጧል፡፡ በአጠቃላይ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 140 ነው፡፡ ወረርሽኙን ለመቆጣጠር እንዲቻል በአካባቢው ለበሽታው መስፋፋት አጋላጭ የሆኑ ቦታዎች የመድኃኒት ርጭት መካሄድ ጀምረዋል፡፡

ይሁንና ማንኛውም በበሽታው የተያዘ ሰው በቶሎ ወደ ሕክምና ተቋም በመሄድ የሕክምና አገልግሎት ማግኘት የሚችል ሲሆን፣ በተጨማሪም ማኅበረሰቡ ራሱን ከበሽታው ለመከላከል አጎበር እንዲጠቀም፣ እንዲሁም ለትንኞች መራቢያ አመቺ የሆኑ ሁኔታዎችን እንዲያስወግድ ኢንስቲትዩቱ አሳስቧል፡፡

የወባ በሽታ በወረርሽኝ መልክ በአገሪቱ በተለያዩ ክልሎች እየታየ ሲሆን፣ በተለይም በደቡብ ክልል በወላይታ ዞን በስድስት ወረዳዎች (በዳሞ ጋሌ፣ በቦሌሶሴሬ፣ በቦሎሶ ቦምቤ፣ ኪነዶ ኮይሻ፣ ዳሞቴ ሶሬና ዳጉና ፉነጎ) እንዲሁም በአማራ ክልል በባህር ዳር ዙሪያና ደራ ወረዳዎች ተከስቷል፡፡ ኅብረተሰቡ ለትንኝ መራቢያ አመቺ የሆኑ የታቆሩ ውኃዎችን በማፋሰስ እንዲሁም የአልጋ አጎበር በመጠቀም ራሱን ከወባ ትንኝ ንክሻ እንዲከላከል ዶ/ር በየነ አሳስበዋል፡፡

የኩፍኝ በሽታ በአፋር ክልል በአሳይታ ወረዳ የተከሰተ ሲሆን፣ በወረርሽኙ 256 ሰዎች ተይዘዋል፡፡ ይሁንና ወረርሽኙን አስቀድሞ ለመከላከል እንዲቻል ክትባት በወረዳው ተሰጥቷል፡፡ በአሁን ወቅት 26 የሚሆኑ ሕሙማን በአሳይታ ሆስፒታል ሕክምና እየተደረገላቸው መሆኑን አክለዋል፡፡

የጊኒዎርም በሽታ በጋምቤላ ክልል በጎግ ወረዳ በአራት ዝንጀሮዎች ላይ የተገኘ በመሆኑ ኢንስቲትዩቱ ከእንስሳት ወደ ሰው እንዳይተላለፍ ትኩረት ሰጥቶ እየሠራ ነው፡፡ ከዚህም ጋር በተያያዘ በአካባቢው የሚገኙ ማኅበረሰቦች ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ አመልክተዋል፡፡

ከክረምቱ ጋር ተያይዞ በተለይም በጎርፍ ምክንያት ውኃዎች መበከል ሊጋጥማቸው ይችላል፡፡ በመሆኑም ኅብረተሰቡ ለመጠጥ የሚጠቀመው ውኃ በውኃ ማከሚያ ኬሚካሎች በማከም ወይም አፍልቶ እንዲጠቀም እንዲሁም ወቅቱ የዝናብ በመሆኑ ለወባ ትንኝ መራባት አመቺ ስለሆነ ኅብረተሰቡ ጥንቃቄ እንዲያደርግ ዶ/ር በየነ አሳስበዋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...