Sunday, June 23, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ኢትዮጵያዊው የኮሜሳ ባንክ ፕሬዚዳንት የዓመቱ የባንክ ባለሙያ የተሰኘውንና እንደ ኦስካር የሚታየውን ሽልማት ተቀዳጁ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

የምሥራቅና የደቡባዊ አፍሪካ የጋራ ገበያ (ኮሜሳ) ባንክ እየተባለ የሚታወቀው የንግድና የልማት ባንክ ፕሬዚዳንትና ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን እያገለገሉ የሚገኙት አቶ አድማሱ ታደሰ፣ የአፍሪካ የዓመቱ የባንክ ባለሙያ የተሰኘውን የአፍሪካ ልማት ባንክ ሽልማት ተቀዳጅተዋል፡፡

በኢኳቶሪያን ጊኒ፣ ማላቡ ከተማ በተካሄደው የአፍሪካ ልማት ባንክ ዓመታዊ አቶ አድማሱ ብቻም ሳይሆኑ፣ የሚመሩት ባንክም የዓመቱ ምርጥ ባንክ የተሰኘበትን ሽልማት ያገኘ ሲሆን፣ ለሞዛምቢክ የተፈጥሮ ጋዝ ፕሮጀክት በሰጠው ብድር፣ ክሬዲት አግሪኮል ከተሰኘው ባንክ ጋር በጋር እንዲሁም ለኬንያ ባስገኘው የ1.25 ቢሊዮን ዶላር የውጭ የቦንድ ብድር (ሶቨሪን ቦንድ) ሁለት ሽልማቶች አግኝቷል፡፡

ሞዛምቢክ የስምንት ቢሊዮን ዶላር ፈሳሽ የተፈጥሮ ጋዝ ማምረቻ ፕሮጀክት ይፋ አድርጋለች፡፡ ለዚህ ፕሮጀክት ከሚያስፈልገው ፋይናንስ ውስጥ ከ92 ሚሊዮን ዶላር በላይ የሚሆነውን አቶ አድማሱ የሚመሩት የንግድና የልማት ባንክ ለማቅረብ ተስማምቷል፡፡ 

እ.ኤ.አ. በ2012 አንድ ቢሊዮን ዶላር የነበረው የንግድና የልማት ባንክ፣ በአሁኑ ወቅት ከስድስት ቢሊዮን ዶላር ካፒታል ማስመዝገብ የቻለ ሲሆን፣ የተበላሸ የብድር መጠኑም ከሦስት በመቶ በታች በመሆኑም ጭምር ጤናማና በልማት ባንኮች ከሚታየው የበለጠ ዘመናዊነትን መላበስ የቻለ ባንክ እየተባለ የሚሞከሸው ይህ የኮሜሳ ባንክ፣ እያሳየ ላለው ውጤታማነት በዋናነት የሚጠቀሱት አቶ አድማሱ ናቸው፡፡ 

አቶ አድማሱ በፋይናንስ ኢንዱስትሪው መስክ በአፍሪካ ስመጥር ከሚባሉ ባለሙያዎች ተርታ የሚመደቡ ኢትዮጵያዊ ሲሆኑ፣ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ተቋማት ውስጥ በልዩ ልዩ የኃላፊነት መደቦች ማገልገላቸውንም ግለ ማኅደራቸው ያሳያል፡፡

በአገር ቤትም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ሐበሻ ሲሚንቶ፣ ጋቴፕሮ የብረት ውጤቶች ማምረቻ፣ እንይና ሌሎችም ኩባንያዎች ከባንኩ በየጊዜው ብድር ማግኘት የቻሉት በአብዛኛው አቶ አድማሱ ባንኩን ማስተዳደር ከጀመሩ ወዲህ ሲሆን፣ በኢትዮጵያ በርካታ መስኮች በአንድ ጊዜ እስከ አንድ ቢሊዮን ዶላር ብድር ለማቅረብ የሚቻልባቸው ፕሮጀክቶች እንዳሉ በአንድ ወቅት ከሪፖርተር ጋር ባደረጉት ቆይታ መናገራቸው ይታወሳል፡፡

የፋሽን አልባሳት አምራችና የወጣት ዲዛይነሮች መፍለቂያ እየሆነ ከመጣው አፍሪካን ሞዛይክ መሥራችና የቀድሞዋ ዓለም አቀፍ ሞዴሊስት የአና ጌታነህ የትዳር አጋር የሆኑት አቶ አድማሱ፣ ከባለቤታቸው ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ሕፃናት ፈንድ የተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት ውስጥም ተሳትፎ ያደርጋሉ፡፡ በአብዛኛው የባለቤታቸው የአና ጌታነህ ጥንስስ የሆነው ይህ የበጎ አድርጎት ተቋም ወላጆቻቸውን ያጡና የተቸገሩ በሺዎች የሚቆጠሩ ሕፃናትን በመንከባከብና በማስተማር ይታወቃል፡፡   

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች