Tuesday, April 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትየስፖርት ባለሙያዎች ለስፖርቱ ውድቀት ተጠያቂ ነን ሲሉ ራሳቸውን ወቀሱ

የስፖርት ባለሙያዎች ለስፖርቱ ውድቀት ተጠያቂ ነን ሲሉ ራሳቸውን ወቀሱ

ቀን:

አገር አቀፍ የስፖርት ሣይንስ ሙያ ማኅበር መስርተዋል

በስፖርቱ የሙያ ዘርፍ ተሰማርተው በማገልገል ላይ የሚገኙ የስፖርት ሣይንስ ምሁራን፣ የሙያ ማኅበር ሳይኖራቸው በተበታተነ አኳኋን ስፖርቱ ላይ የነበራቸው ሙያዊ ተሳትፎ ውጤታማ ሳይሆን መቆየቱ ባለሙያዎቹን ተጠያቂ እንደሚያደርጋቸው በመግለጽ ራሳቸው ላይ ወቀሳ አቀረቡ፡፡ አገር አቀፍ የሙያ ማኅበር ለማቋቋም የተዋቀረው ጊዜዊ ኮሚቴ ረቡዕ ሰኔ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ሆቴል ስለዚሁ ጉዳይ መግለጫ  ሰጥቷል፡፡

አገር አቀፉን የስፖርት ሣይንስ የሙያ የማኅበር መመሥረቻ ሰነድ ከማዘጋጀት ጀምሮ የተለያዩ ቅድመ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች የተዋቀረው ጊዜያዊ ኮሚቴ፣ በጋዜጣዊ መግለጫው ዕለት፣ ‹‹ማኅበሩ ቅዳሜ ሰኔ 15 ቀን 2011 ዓ.ም. በዚሁ በኢትዮጵያ ሆቴል ይመሠረታል፤›› ብሏል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በአገሪቱ ሁሉም ስፖርቶች በውጤት ደረጃ ሊጠቀስ የሚችል ስኬት አለማሳየታቸው፣ በተለይም ሣይንሱን በቅጡ የሚገነዘቡ በአካዳሜውና በተግባር ዘርፉን የሚያገለግሉ ባለሙያዎች፣ ዘመኑን በሚመጥን መልኩ በአንድነት መንቀሳቀስ ተስኗቸው እንደቆዩ የጊዜያዊ ኮሚቴው ሰብሳቢ አቶ ቢልልኝ መቆያ ተናግረዋል፡፡

‹‹የተበታተነ አቅም ለአገሪቱ ስፖርት ብቻም ሳይሆን፣ ለራሱ ለሙያተኛውም ዋስትና አይሆንም፡፡ ጥናቶች እንደሚያስረዱት፣ በአሁኑ ወቅት በአገሪቱ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥ ገብተው በስፖርት ሣይንስ የሠለጠኑ ከ10,000 በላይ ባለሙያዎች አሉ፡፡ ይኼ ሁሉ ባለሙያ ባለበት አገር ውስጥ ስፖርቱ በሚፈለገው ደረጃ ማደግ አልቻለም፤›› ያሉት አቶ ዋለለኝ፣ ስፖርቱ ሊያድግ ይቅርና ቀደም ሲል የነበሩ ጠንካራ ጎኖቹን ማስጠበቅ እንደተሳነው ገልጸዋል፡፡ ‹‹ለዚህ ደግሞ ሣይንሱን እናውቃለን ብለን የምናገለግል ሁላችንም ተጠያቂዎች ነን፤›› በማለት ከአሁን በኋላ ግን እስካሁን የነበረው አኳኋን ሊቀጥል እንደማይገባ፣ ይልቁንም በማኅበር ተደራጅተው የአባላቱን መብትም ሆነ በስፖርቱ መስክ የሚኖራቸውን የባለቤትነት ድርሻ በመያዝ መንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

በአብዛኛው ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ውስጥ የስፖርት ሳይንስ ትምህርት በመሰጠቱ በየዓመቱ በርካታ ቁጥር ያለው የስፖርት ሣይንስ ባለሙያ እየተፈጠረ እንደሚገኝ የጠቀሱት አቶ ዋለልኝ፣ የአባላቱን መብት በማስከበር ረገድ፣ የስፖርት ሣይንስ ባለሙያዎች በዘርፉ መሪ ተዋንያን መሆን አለመቻላቸው፣ በዚህም ሳቢያ አብዛኛው ባለሙያ የድርሻውን በአግባቡ ሳይወጣ ለመቆየት መገደዱ ብሎም ባለሙያዎቹ እንደ ዕውቀታቸው ልክ በልዩ ልዩ ተቋማት ውስጥ ገቢውን ሙያዊ ግልጋሎት ማበርከት ሳይችሉ መቆየታቸውን በመዘርዘር የተናጠል ጉዞ ከሙያተኛውም በላይ ስፖርቱን ሲጎዳው እንደቆየ ተናግረዋል፡፡

ማኅበሩ ከተቋቋመ በኋላ በአገሪቱ ከሚገኙ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማትና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ጋር ጠንካራ ግንኙነት በመፍጠር ከስፖርት ዘርፍ ሥርዓተ ትምህርት ቀረፃ ጀምሮ በማናቸውም ሙያው በሚጠይቀው የማማከርና መሰል ሁነቶች ላይ ድርሻ እንዲኖረው እንደሚደረግም ሰብሳቢው አክለዋል፡፡

የማኅበሩን አባላት በሚመለከት ሰብሳቢው ሲናገሩ፣ ‹‹ከስፖርቱ ጋር ተያያዥነት ያላቸው ሙያተኞች በሙሉ አባል ይሆናሉ፤›› ብለዋል፡፡ ነገር ግን ፈቃዱን ከሚሰጠው ከመንግሥት አካል ጋር ስለ ጉዳዩ ውይይት ተደርጎ ከስምምነት የተደረሰው ‹‹የማኅበሩ አባል መሆን የሚችሉት በትምህርት ደረጃቸው ቢያንስ ዲፕሎማ ያላቸው ናቸው፤›› ቢልም የማኅበሩ ፍላጎትም ሆነ መሆን የሚገባው አሠራር ግን ከስፖርቱ ጋር ግንኙነት ያላቸውና ከስፖርት ሚዲያው ጭምር በአባልነት ቢካተቱ ተገቢ እንደሚሆን እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...