ቅዳሜ ሰኔ 15 ቀን በባህር ዳርና በአዲስ አበባ ከተሞች በሰዓታት ልዩነት በአማራ ክልል ከፍተኛ የመንግሥት ባልሥልጣናት፣ እንዲሁም በአገር መከላከያ ሠራዊት ከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ላይ የተፈጸመው ግድያ ምክንያት በመላ አገሪቱ ሐዘንና ድንጋጤ ተፈጥሯል፡፡ የመንግሥት ባለሥልጣናቱም ሆኑ የወታደራዊ መኮንኖቹ ድንገተኛ ሕልፈት ከታወቀ በኋላ በርካታ መላምቶች እየተሰሙ ቢሆንም፣ የምርመራ ውጤቱ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ በመንግሥት በኩል ተገልጿል፡፡ ለሟቾች ረቡዕ ሰኔ 19 ቀን 2011 ዓ.ም. በባህር ዳርና በትግራይ ክልል ከፍተኛ የቀብር ሥነ ሥርዓት ይከናወናል፡፡