Friday, September 22, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊጄኔራል አብርሃ ወልደ ማርያም (ኳርተር) (1953-2011)

ጄኔራል አብርሃ ወልደ ማርያም (ኳርተር) (1953-2011)

ቀን:

ባደረባቸው ሕመም ምክንያት በታይላንድ ሕክምና ሲከታተሉ የነበሩት ጄኔራል አብርሃ ወልደ ማርያም (ኳርታር)፣ ዓርብ ሰኔ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ከዚህ ዓለም በሞት ተለዩ፡፡

በቀድሞው ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለ ማርያም አመራር ወቅት የሙሉ ጄኔራልነት ማዕረግ ያገኙት ጄኔራል አብርሃ፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ሥልጣኑን ከጨበጡ በኋላ በጡረታ መገለላቸው ይታወሳል፡፡

ጄኔራሉ በሕወሓት/ኢሕአዴግ የትጥቅ ትግል በተዋጊነትና አዋጊ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን፣ የአገር መከላከያ ሠራዊት እንደገና ሲደራጅ የደቡብ ምሥራቅ ዕዝ ዋና አዛዥና በአገር መከላከያ ሚኒስቴር የዘመቻ መምርያ ኃላፊ ሆነው ሠርተዋል፡፡

በተጨማሪም በሰላም ማስከበር ተልዕኮ በሩዋንዳ በሻለቃ ጦር ምክትል አዛዥነት ማገልገላቸውን የሕይወት ታሪካቸው ያመለክታል፡፡

በትግራይ ክልል ማዕከላዊ ዞን እንደባፃህማ ወረዳ ነሐሴ 21 ቀን 1953 ዓ.ም. መወለዳቸው የተገለጸው ጄኔራል አብርሃ፣ በ58 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡ ባለትዳርና የሁለት ወንዶችና የሁለት ሴቶች አባት የነበሩት ጄኔራል አብርሃ አስከሬናቸው እሑድ ሰኔ 23 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ቦሌ ዓለም አቀፍ ኤርፖርት አቀባበል ከተደረገለት በኋላ፣ ወደ ትውልድ ሥፍራቸው እንደሚሸኝ ታውቋል፡፡

የቀብር ሥነ ሥርዓታቸው በቤተሰቦቻቸውና በመንግሥት ከተወሰነ በኋላ በአገር መከላከያ ሠራዊት የቀብር ሥነ ሥርዓት መሠረት እንደሚፈጸም፣ ይህንንም በተመለከተ ለሕዝብ ይፋ እንደሚደረግ የአገር መከላከያ ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የዓለም አቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ኮሚሽን ሪፖርት ምን ይዟል?

ለአሜሪካ ድምፅ አማርኛ ዝግጅት የስልክ አስተያየት የሰጡ አንድ የደንበጫ...

መንግሥት በአማራ ክልል ለወደሙ የአበባ እርሻዎች ድጋፍ እንዲያደርግ ተጠየቀ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በአማራ ክልል የተፈጠረው ግጭትና አለመረጋጋት በቢዝነስ...

አምናና ዘንድሮ!

እነሆ መስከረም ጠብቶ በአዲስ መንፈስ ተሞልተን መንገድ ጀምረናል። ‹‹አዲስ...