Saturday, March 2, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊሠናይነት በሕክምና ባለሙያዎች

ሠናይነት በሕክምና ባለሙያዎች

ቀን:

‹‹ከሁለት ዓመት በፊት የጤና መታወክ አጋጥሞኝ ለሕክምና ወደ ቅዱስ ጴጥሮስ ሆስፒታል አቀናሁ፡፡ እንደደረስኩም ተገቢው ምርመራ ተደረገልኝ፡፡ ውጤቱም መድኃኒት የተለማመደ ቲቢ ሆኖ ተረጋገጠ፡፡ ሰውነቴ አልቆ አጥንቴ ብቻ ቆዳ ለብሶ ነበር፡፡ ከበሽታው አስከፊነት የተነሳ የሚጠይቀኝ ወይም የሚያስታምመኝ ዘመድ አዝማድ የለም፡፡ ለሕይወታቸው ሳይሳሱ የሚያክሙኝ፣ የሚያገላብጡኝና የተፀዳዳሁትን የሚያነሱልኝ ሐኪሞች ብቻ ነበሩ፡፡››

ይህን የተናገሩት ከተለማመደው ቲቢ በሕክምና የተፈወሱት አቶ ቅጣው ንጉሤ ናቸው፡፡ ሰኔ 25 ቀን 2011 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ለሁለተኛ ጊዜ በተካሄደው ‹‹የመልካም ዶክተሮች ቀን›› በዓል ላይ አቶ ቅጣው ሕይወታቸውን ለታደጉ ሐኪሞች ባደረጉት የምሥጋና ንግግር የገጠማቸውን የጤና ችግር በሐኪሞች ዕርዳታና እገዛ አልፈው በአሁኑ ጊዜ ከቤተሰቦቻቸው ጋር ለመቀላቀል መብቃታቸውን ገልጸዋል፡፡

ሠናይነት በሕክምና ባለሙያዎች

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እሳቸውን ጨምሮ ወደ 40 የሚጠጉና ተላላፊ በሽታ ካደረባቸው ታካሚዎች መካከል እየተዘዋወሩ የሕክምና ዕርዳታ መስጠት ምን ያህል ሰቅጣጭ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

አቶ አንዋር  አህመድ የተባሉ ሌላው አስተያየት ሰጪ የአራት ልጆች አባት እንደሆኑና ከሁለት ዓመት በፊት የኩላሊት ችግር እንደገጠማቸው አመልክተው፣ ልጆቻቸውን የሚያስተዳድርላቸው፣ የሚያስተምራቸው፣ የሚያሳድግላቸውና የሚያስጠጋቸው ዘመድ አለመኖሩን ካደረባቸው በሽታ ጋር ተዳምሮ ስቃያቸውን እንዳበዛ ተናግረዋል፡፡

እንደ አቶ አንዋር በሐኪሞች ክትትልና ዕርዳታ ከበሽታቸው ተፈውሰውና ከጭንቀታቸው ነፃ ወጥተው ወደ ቤታቸውና ሥራቸው ተመልሰዋል፡፡ ለዚህም ላበቋቸው ሐኪሞች ምሥጋና አቅርበዋል፡፡

የኮሙዩኒኬሽን ባለሙያና ፀሐፊት ወ/ሮ ሕይወት እምሻው ‹‹ብዙ ሰዎች ሐኪም መሆን ይፈልጋሉ፣ ይመኛሉ፡፡ የሚሳካላቸው ጥቂቶች ናቸው፡፡ ምክንያቱም ሐኪሞ መሆን መጀመርያ ከትምህርት ቤት ጀምሮ ጉብዝናን፣ ብርታትን፣ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ መሥራትን፣ ከሞገሱ፣ ከክብሩና  ከማዕረጉ ጋር ከባድ ኃላፊነትን ይዞ የሚመጣ ነው፡፡ ይህንንም የሚወጡት ጥቂት ሰዎች ብቻናቸው፤›› ብለዋል፡፡

ሠናይነት በሕክምና ባለሙያዎች

 እንደ ወ/ሮ ሕይወት፣ ሕፃናት ስታድጉ ምን ለመሆን ትፈልጋላችሁ ተብለው ሲጠየቁ መልሳቸው ‹ሐኪም መሆን› እንደሆነ ነው፡፡ ለዚህም የሚሰጡት ምክንያት እናቴ፣ አባቴ ወይም ዘመዴ ታመው ሐኪም አዳናቸው ሲባል መስማታቸው ነው፡፡ ከዚህ አኳያ ሕፃናት ሐኪም መሆን የሚመኙበት የመጀመርያው ምክንያታቸው ማዳንን ስለሚመኙና ሐኪሞችም ያድናሉ ብለው ስለሚያስቡ ነው፡፡

ደራሲ ኃይለመለኮት መዋዕል፣ ሐኪሞች ወደ ሙያው ሲገቡ የሚፈጽሙት መሐላ ድንበር እንደሌለው፣ የወገን ጦር ከጠላት ጦር ጋር ቢዋጋና ሁለቱም ቆስለው ቢወድቁ ሐኪሞቹ የሕይወት ማዳንን ሥራ የሚሠሩት ለወገን ብቻ ሳይሆን ሁለቱንም መሆኑን፣ ይህም የሐኪሞች  መሐላ ዓለም አቀፍ ይዘት እንዳለው የሚያሳይ  መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ለተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ለምሳሌ ለጋዜጠኛ፣ ገበሬ፣ ሾፌር፣  ለወታደር ተዘፍኗል፡፡ ለሐኪሞች ግን ተዘፍኖ ያውቃል? ብለው ላቀረቡት ጥያቄ ራሳቸው ሲመልሱ ‹‹በእኔ ዕድሜ ተዘፍኖ አላየሁም››  ብለዋል፡፡ ነገር ግን ታክመው ጤና ያገኙ ወይም የዳኑና በሚሊዮን የሚቆጠሩ ነፍሶች ለሐኪሞች በሚሰማና በማይሰማ ቋንቋ እንደሚዘፍኑላቸው አስረድተዋል፡፡

የሌሎች ዘፈኖች ተሰምቶ ወዲያው እንደሚያልቅ  የሐኪሞቹ ዘፈን ግን ሁልጊዜ በየዕለቱ ‹‹ዕድሜ ይስጣችሁ!›› እየተባሉ የሚመረቁና የሚወደሱ ከመሆናቸውም በላይ ሕይወት ለማዳን ቀዳሚ እንደሆኑ አመልክተዋል፡፡

በዓለም ላይ ሰዓት የማይገድበው፣ ከተጀመረ የማይቋረጥ፣ ከተፈለገም የሚታደርበት ሥራ የሐኪሞች ሥራ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ድካማቸው እጅግ ከፍተኛና በአጠቃላይ ከእግዚአብሔር በታች የነፍስ ወኪሎች ናቸው፡፡ በአንጻሩ ግን የልፋታቸውን ያህል እንደማይከፈላቸው ደራሲው ተናግሯል፡፡

የቅድስት ሥላሴ መንፈሳዊ ዩኒቨርሲቲ የአካዴሚክ ምክትል ዲን ቀሲስ መዝገቡ ካሳ (ዶ/ር)፣ ሐኪሞች በአዕምሮ፣ በአካልና በመንፈስ ጤነኛ ካልሆኑ ሰዎችን ሊያክሙ አይችሉም፡፡ ራስን መውደድ የሚለው አመለካከት ከሐኪሞች ጋር አብሮ እንደማይሄድና ራስን አሳልፎ የሚሰጥ ሙያ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

የሕክምና ሙያ ከአምላክ ጋር የሚገናኝበት መንገድ እንዳለው ቄስ መዝገቡ ጠቁመው፣ ሰው ውስጣዊ ገበናውን ያለምንም ሃፍረት ለሐኪሙ ገላልጦ የሚያሳየው ያድነኛል፣ አለበለዚያም ስቃዬ በሐኪሙ ይፈታል የሚል ልባዊ እምነት ስላለው መሆኑን አስረድተዋል፡፡

የፕሮቴስታንት እምነት ሰባኪና አስተማሪ ፓስተር ዮናታን አክሊሉ ‹‹ትንሽ ልጅ ሆኜ ሐኪም ሲባል በጣም ሀብታም ነበር የሚመስለኝ፡፡ ነፍስ እያወኩና እያደኩ ስመጣ የሚከፍሉትን ዋጋና የሚኖሩትን አይቼ ለአገር አገልግሎት ከሚሰጥ ይልቅ፣ ጨውና ዘይት ደብቆ ኅብረተሰቡ በችግር ውስጥ ሲዘፈቅ በውድ ዋጋ የሚሸጥ ደህና እየኖረ መሆኑን ተገንዝቤያለሁ፤››  ብለዋል፡፡

ይህም ሆኖ ግን ሐኪሞች የበለጠ የሚያስደስታቸውና የሚያረካቸው ለሰው ልጅ በሚሰጡት ሕይወት፣ ወይም ባለቀ ደቂቃ ሕይወት ለማትረፍ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውጤታማ ሆኖ ሲያገኙት መሆኑን ሳይገልጹ አላለፉም፡፡

የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበር የቢዝነስና ዴቨሎፕመንት ፕሮግራም ሥራ አስኪያጅ አቶ ጌትነት ካባ፣ የኢትዮጵያ ሐኪሞች ቀን በየዓመቱ ሰኔ 25 ቀን እንዲከበር የተወሰነው በማኅበሩ 54ኛው ጉባዔ ላይ መሆኑን፣ ሰኔ 25 እንዲሆን የተደረገበት ምክንያት በአገሪቱ የመጀመርያዎች ሐኪሞች በዚህ ዕለት ስለተመረቁ መሆኑን አክለዋል፡፡

ይህም በዓል ሲከበር የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ እንደሆነና በዚህም ዝግጅት አዳዲስ ሐኪሞች የሚበረታቱበት፣ ከከፍተኛ ሐኪሞች ጋር የሚተዋወቁበት፣ ልምድም የሚቀስሙበትና ታክመው የዳኑ ሰዎች ለሐኪሞቻቸው ምሥጋና የሚያቀርቡበት ነው፡፡ ወደፊት ግን በማኅበረሰቡ ዘንድ እየተለመደና እየተጠናከረ ሲመጣ ለዕውቅ ሐኪሞች ዕውቅና የሚቸርበት፣ ሁሉም ሐኪሞች ትንሽ ዘና ብለው የሚውሉበት፣ እንዲሁም የማኅበራዊ አገልግሎቶች የሚከናወኑበትና የዕውቀትና የቴክኖሎጂ ሽግግር የሚከናወንበትን ፕሮግራም ያካተተ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሕክምና ኮሌጅ የአካዴሚክና ጥናት ምክትል ፕሮቮስት ሲሳይ ይርጉ (ዶ/ር) የሕክምና ተማሪዎች ወደ ሥራው ዓለም ሲቀላቀሉ የኅብረተሰቡ አገልጋይ ሆነው እንዲወጡ ለማድረግ የሚያስችል ሥራ እየተሠራ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት የስብሰባ አዳራሽ የተካሄደውን ይህንኑ ፕሮግራም በመተባበር ያዘጋጁት የኢትዮጵያ ሕክምና ማኅበርና የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሕክምና ኮሌጅ ናቸው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...