Monday, June 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናሲጠበቅ የነበረው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

ሲጠበቅ የነበረው የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲ ምዝገባ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

ቀን:

የፖለቲካ ፓርቲዎች በንግድናኢንዱስትሪ መሰማራት ይከለከላሉ

በውጭ አገር ለሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መምረጥ የሚችሉበት ልዩ ሥርዓት ይዘረጋል

ለፓርላማ በዕጩነት የሚቀርብ ግለሰብ ከምርጫ ክልሉስት ሺሕ የድጋፍ ፊርማ ማቅረብ አለበት

በዕጩነት የቀረበ የመንግሥት ሠራተኛ የምርጫው ሒደት እስከሚጠናቀቅ ያለ ደመወዝ ከሥራ ገበታው መልቀቅ ይኖርበታል

2012 ዓ.ም. ይካሄዳል ተብሎ የሚጠበቀውን አገር አቀፍ ምርጫ ከምንጊዜውም በላይ ነፃና ፍትሐዊ ለማድረግ መንግሥት ቃል በገባውና ምኅዳሩን ለመፍጠር አስፈላጊ ነው የተባለው የምርጫ ማሻሻያ ተጠናቆ ረቂቁ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሐሙስ ሰኔ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. ቀረበ፡፡

ረቂቁ በርካታ ማሻሻያዎችን ያካተተ ሲሆን፣ ከእነዚህም መካከል ላለፉት ዓመታት አወዛጋቢ ሆኖ የቆየው የገዥው ፓርቲ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች በሥራቸው የሚያስተዳድሯቸው የንግድ ድርጅቶችና ኢንዱስትሪዎችን ጉዳይ እልባት ሊሰጥ የሚችል ድንጋጌ ይዟል፡፡

ረቂቅ አዋጁ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የተፈቀዱ የገንዘብ ምንጮችን ዘርዝሯል፡፡ እነዚህም ከአባላት የሚሰበሰብ የአባልነት መዋጮ፣ ምርጫ ቦርድ አጥንቶ በሚያስቀምጠው ጣሪያ መሠረት በኢትዮጵያውያን ግለሰቦች ወይም ኢትዮጵያውያን በሚቆጣጠሯቸው ኩባንያዎች የሚደረግ ስጦታ ወይም ዕርዳታ፣ ከመንግሥት ከሚሰጠው ድጋፍና ዕርዳታ የገንዘብ አቅምን ለማጎልበት የሚያግዙ የገቢ ማስገኛ ዝግጅቶች በማዘጋጀት ከሚገኝ ገቢ ብቻ መሆኑን በግልጽ አስፍሯል፡፡

የተከለከሉ የገቢ ምንጮችን በተመለከተ ማንኛውም ሕጋዊ ሰውነት ያገኘ የፖለቲካ ፓርቲ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ መንገድ፣ በንግድና ኢንዱስትሪ ሥራዎች መሰማራት እንደማይችል የሚገልጽ ድንጋጌካቷል፡፡ ከተገለጹት በተጨማሪ ማንኛውም ፓርቲ ካልታወቀ ምንጭ ወይም ሙሉ በሙሉ፣ ወይ በከፊል የመንግሥት ከሆኑ የልማት ድርጅቶች የሚቀርብ ስጦታ ወይምርዳታ መቀበል እንደማይችል ረቂቁ ይከለክላል፡፡

በተጨማሪም አንድን ጉዳይ ወደፊት ለማስፈጸም ተገቢ ያልሆነ ጥቅም ለማግኘት ወይም ከሕግ ውጭ ጥቅም ለማግኘት ከሚያልም ማንኛውም አካል የሚሰጥ ስጦታ፣ ወይምርዳታ መቀበል እንደማይቻል ረቂቁ ይገልጻል፡፡

ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ የተከለከለ ስጦታ ወይም ዕርዳታ በማንኛውም መንገድ የተቀበለ እንደሆነ፣ ስጦታውን ወይምርዳታውን በተቀበለ 21 ቀናት ውስጥ ከተያያዥ መረጃዎች ጋር ለቦርዱ ገቢ ማድረግ ይጠበቅበታል፡፡

ማንኛውም የፖለቲካ ፓርቲ በዚህ አዋጅ ከተፈቀደለት ውጪገንዘብ፣ንብረት፣ በስጦታ፣ በዳረጎት፣ በውርስ፣ በንግድና ኢንዱስትሪ ሥራ ወይም በማናቸውም መንገድ ተቀብሎ ቢገኝ፣ ያገኘው የገንዘብ ጥቅም ሦስት እጥፍ እንደሚቀጣና ከምዝገባ እንደሚሰረዝ ረቂቁ ይደነግጋል፡፡

ዕድሜው 18 ዓመት በላይ የሆነ ኢትዮጵያዊ በመራጭነት መሳተፍ የሚችል ሲሆን፣ በውጭገር በመኖራቸው ወይም በሌላ ምክንያት በአካባቢያቸው መምረጥ ለማይችሉ ዜጎች፣ በምርጫ የሚሳተፉበት ልዩ ሥርዓት ምርጫ ቦርድ ሊዘረጋ እንደሚችልና ዝርዝር አፈጻጸሙ ቦርዱ በሚያወጣው መመርያ እንደሚወሰን ያመለክታል፡፡

የፖለቲካ ፓርቲጩዎች በሥራ ላይ ባለው መሠረት ማሟላት ከሚጠበቅባቸው መሥፈርቶች በተጨማሪ እያንዳንዱ ዕጩ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሚወዳደር ከሆነ፣ በሚወዳደርበት የምርጫ ክልል ከሚኖሩ መራጮችስት ሺሕ የድጋፍ ፊርማ፣ ለክልል ምክር ቤት የሚወዳደር ከሆነ አንድ ሺሕ አምስት መቶ የድጋፍ ፊርማ ማቅረብ እንደሚኖርበት ረቂቁ ያመለክታል፡፡

በሌላ በኩል በምርጫ የሚወዳደሩ የመንግሥት ሠራተኞች በዕጩነት ከተመዘገቡበት ጊዜ ጀምሮ የምርጫው ሒደት እስከሚጠናቀቅ በጊዜያዊነት ከሥራ ገበታቸው መልቀቅ የሚኖርባቸው ሲሆን፣ በዚህ ምክንያት በጊዜያዊነት የለቀቀ ዕጩ ምርጫው እስኪጠናቀቅ ባለው ጊዜ ውስጥ የሚከፈለው ደመወዝና ጥቅማ ጥቅም እንደማይኖርና በማንኛውም የቀጣሪው የመንግሥት መሥሪያ ቤት ንብረት መገልገል እንደማይፈቀድለት ረቂቁ ይገልጻል፡፡

በተጨማሪም ዳኞች፣ ወታደሮች፣ ፖሊሶችና ሌሎች የፀጥታይሎች፣ የደኅንነትራተኞችና የምርጫ ቦርድራተኞችግል ወይም የፖለቲካ ፓርቲ ተወዳዳሪ ሆነው ከቀረቡ የያዙትን የመንግሥት ሥራ መልቀቅ እንደሚገደዱ ረቂቁ ያመለክታል፡፡

አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲ ስለመመሥረት በተቀመጠው የድንጋጌው ክፍል ደግሞ አንድ የፖለቲካ ፓርቲ በአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲነት የሚመሠረተው፣ 10,000 መሥራች አባላት ሲኖሩት ነው፡፡ ከመሥራች አባላቱ ውስጥም ከአርባ በመቶ የማይበልጡት የአንድልል መደበኛ ነዋሪዎች መሆን እንደሚጠበቅባቸው፣ የተቀሩት መሥራች አባላት ደግሞ በኢትዮጵያ ከሚገኙት ሌሎች ክልሎች ውስጥ ቢያንስ በአራቱ ክልሎች መደበኛ ነዋሪዎች ሊሆኑ እንደሚገባ ያመለክታል፡፡

ከላይ በተመለከተው መሠረት ፓርቲው የሚያቀርበውን የመሥራች አባላት መረጃ ትክክለኛነት ለማረጋገጥ አጠራጣሪ ሁኔታ ሲያጋጥም፣ ቦርዱ መሥራች አባላቱ በሚኖሩበት አካባቢ የነዋሪነት ማረጋገጫ የመስጠት ሥልጣን ካለው አካል ጋር በመተባበር ሊያጣራ እንደሚችል፣ የማጭበርበር ተግባር መፈጸሙ ከተረጋገጠ ፓርቲው ለሦስትመታት በፖለቲካ ፓርቲነት ከመመዝገብ እንደሚከለከል ወይም እንደሚሰረዝ ይገልጻል፡፡ እንዲሁም ከማጭበርበር ተግባሩ ጋር ግንኙነት ያለው ማንኛውም የፓርቲ መሪ፣ ኃላፊና ግለሰብ በፓርቲ መሪነት ወይም አባልነት ከመሳተፍ እንደሚታገድ ይገልጻል፡፡

ረቂቅ አዋጁ የተወካዮች ምክር ቤት ሊዘጋ የቀናትድሜ ሲቀረው መቅረቡ ተገቢ አለመሆኑን አንዳንድ የምክር ቤቱ አባላት ተናግረዋል፡፡ቂቁ ለዝርዘርይታ ለሕግ፣ ፍትሕና ዴሞክራሲ ጉዳዮች ኮሚቴ ተመርቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አስጨናቂው የኑሮ ውድነት ወዴት እያመራ ነው?

ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የኑሮ ውድነት እንደ አገር ከባድ ፈተና...

‹‹ወላድ ላማቸውን አርደው ከደኸዩት ወንድማማቾች›› ሁሉም ይማር

በንጉሥ ወዳጅነው   የዕለቱን ጽሑፍ በአንድ አንጋፋ አባት ወግ ልጀምር፡፡ ‹‹የአንድ...

የመጋቢቱ ለውጥና ፈተናዎቹ

በታደሰ ሻንቆ ሀ) ችኩሎችና ገታሮች፣ መፈናቀልና ሞትን ያነገሡበት ጊዜ እላይ ...

ጥራት ያለው አገልግሎት መስጠት የሚያስችል ሥርዓት ሳይዘረጉ አገልግሎት ለመስጠት መነሳት ስህተት ነው!

በተለያዩ የመንግሥትና የግል ተቋማት ውስጥ ተገልጋዮች በከፈሉት ልክ የሚፈልጉትን...