በአዲስ አበባ ልደታ ክፍለ ከተማ ወረዳ 3 ልዩ ስሙ ኮካ በሚባለው አካባቢ ከ200 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የተገነባው የአሚን አጠቃላይ ሆስፒታል ሕንፃ በጤና ሚኒስትር አሚር አማን (ዶ/ር) ሰኔ 30 ቀን 2011 ዓ.ም. ተመርቋል፡፡ ግንባታው አምስት ዓመት የፈጀው የሆስፒታሉ ሕንፃ 80 አልጋዎች ያሉት ሲሆን የድንገተኛና ፅኑ ሕሙማን፣ የውስጥ ደዌ፣ የማህፀንና ፅንስ፣ የሕፃናት፣ የዓይንና የጥርስ፣ የልብ፣ የመተንፈሻ አካላትና መሰል ሕክምናዎችን እንደሚሰጥ፣ እንዲሁም በዘመናዊ ቴክኖሎጂ መደራጀቱን የሆስፒታሉ ባለቤት ዶ/ር መሀመድ ሽኩር በምረቃው ላይ ገልፀዋል። ሆስፒታሉ ለ200 ሰዎች የሥራ ዕድል ፈጥሯል። ፎቶዎቹ የምረቃውን ገጽታ በከፊል ያሳያሉ፡፡
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -
ፌርማታ ፅሁፎች
ትኩስ ፅሁፎች
- Advertisement -
- Advertisement -