‹‹ሞደርኒስት አርት ኢን ኢትዮጵያ›› በተሰኘውና በኤልሳቤጥ ወልደ ጊዮርጊስ (ዶ/ር) ተጽፎ፣ በኦሃዩ ዩኒቨርሲቲ ፕሬስ እ.ኤ.አ. በ2019 የታተመው መጽሐፍ ማስተዋወቂያ ዝግጅት ሐሙስ፣ ሐምሌ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ከቀኑ በ10 ሰዓት በአለ የሥነ ጥበብና ዲዛይን ትምህርት ቤት ይካሄዳል። በዝግጅቱ ላይ ዶ/ር ኤልሳቤጥ ስለመጽሐፉ አጠር ያለ ዳሰሳ የሚያቀርቡ ሲሆን፣ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ሂሳዊ የማስተዋወቂያ ምልከታቸውን ያጋራሉ። በተጨማሪም በመጽሐፉ የተካተቱ የተወሰኑ የሥነ ጥበብ ሥራዎች ዓውደ ርዕይ፣ ግጥሞችና የጃዝ ሙዚቃዎች ይቀርባሉ።