Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዓለምለሱዳን ሰላም ያሰፈነው የሥልጣን መጋራት ስምምነት

ለሱዳን ሰላም ያሰፈነው የሥልጣን መጋራት ስምምነት

ቀን:

በሱዳን ለወራት የዘለቀው ሰላማዊ ሠልፍ ግቡን መትቶ፣ የሱዳን ወታደራዊ ሽግግር መንግሥትና የዴሞክራሲ አቀንቃኞቹ የተቃዋሚ ፓርቲዎች ጥምረት ከሥልጣን መጋራት ስምምነት ደረሱ፡፡

ለ30 ዓመታት ሱዳንን የመሩትን የቀድሞው ፕሬዚዳንት ኦማር አልበሽርን ከሥልጣን ለማውረድ ከአምስት ወራት በፊት የተጀመረው ሕዝባዊ ተቃውሞ፣ በሚያዝያ 2011 ዓ.ም. ፕሬዚዳንቱን ከሥልጣን ለማውረድ የጀርባ አጥንት ቢሆንም፣ የአልበሽርን ሥልጣን የተረከበው መከላከያ ኃይሉ ከሕዝቡ ጋር ስምምነትን ማድረግ ተስኖት ነበር፡፡

ሱዳናውያን በሲቪል መመራት አለባቸው በሚሉ ተቃዋሚዎች ሲፈተን የቆየው ወታደራዊ ሽግግር መንግሥቱ፣ ሥልጣኑን ለሲቪል እንዲያጋራ በተደጋጋሚ ውይይት ቢደረግም ከስምምነት መድረስ አልተቻለም ነበር፡፡

- Advertisement -

ይህን ተከትሎ በሱዳን ካርቱም አውራ ጎዳናዎች በተለይም በመከላከያ ቢሮ ፊት ለፊት ለወራት ሳይታክቱ ተቃውሞዋቸውን ከሚገልጹ ተቃዋሚዎች ጋር ግጭትም ተፈጥሮ ነበር፡፡ በግጭቱ የሱዳን መከላከያ ወስዶታል በተባለው ዕርምጃ ቁጥሩ ቢለያይም ከ60 ያላነሱ ሰዎች መገደላቸውም የቅርብ ጊዜ ዜና ነው፡፡

ለሱዳን ሰላም ያሰፈነው የሥልጣን መጋራት ስምምነት

 

መከላከያ ሠራዊቱ ለተቃውሞ በወጡ ሠልፈኞች ላይ የወሰደው ዕርምጃ፣ ከዚህ ቀደም ከነበረው በተለየ መልኩ አገሪቷን ወደ እርስ በርስ ጦርነት እንዳያመራት ሥጋት ጥሎ የነበረ ቢሆንም፣ ዛሬ ላይ ግጭቶች ወደ ሰላም ተቀይረዋል፡፡ ለተቃውሞ ከሥራ በመቅረት የሱዳንን ጎዳናዎች የሚያጨናንቁ ሱዳናውያን ወደ ሥራ ከተዋል፡፡

አብዮተኞች የተዋቃሚ ፓርቲ ጥምረትና ወታደራዊ የሽግግር መንግሥቱ የሥልጣን መጋራት ስምምነት በደረሱበት ሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ደስታቸውን በሰላማዊ ሠልፍ ገልጸው፣ ፊታቸውን ወደ ቀጣዩ ሥራቸው አዙረዋል፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው፣ ከአልበሽር መውረድ በኋላ ሱዳንን ሲመራ የነበረው ወታደራዊ መንግሥትና የተቃዋሚዎች ጥምረት፤ በሱዳን ምርጫ እስኪካሄድ ድረስ የአገሪቷን ሥልጣን ተጋርተው ለመምራት ከስምምነት ደርሰዋል፡፡

ለወራት ያህል በሱዳን የዘለቀውን አመፅ በሰበረው በዚህ ስምምነት፣ ጥምር የወታደርና የሲቪል ካውንስል የሚቋቋም ሲሆን፣ አገሪቷንም ሲቪልና ወታደሩ ክፍል በመፈራረቅ ይመሯታል፡፡

በሱዳን ከሦስት ዓመት ከሦስት ወር በኋላ ምርጫ ይካሄዳል ተብሎም ይጠበቃል፡፡ እነዚህን ጊዜያት ደግሞ 11 አባላት ያሉት ካውንስል በሉዓላዊነት አገሪቱን የሚመራ ይሆናል፡፡ አምስት ከመከላከያ ኃይሉና ስድስት ከሲቪል ማኅበረሰብ አባላት ካውንስል እንዲቋቋምም ከስምምነት ተደርሷል፡፡

ከወር በፊት በዴሞክራሲ አቀንቃኝ ሠልፈኞች ላይ የተወሰደውን ወታደራዊ ዕርምጃና ከዚህ በኋላ የነበሩ ሰብዓዊ ጥሰቶችን ለማጣራት ገለልተኛና ነፃ መርማሪ ቡድን እንዲቋቋም ወታደራዊ ሽግግር መንግሥቱና የሲቪል መሪዎች ተስማምተዋል፡፡

የወታደራዊ ሽግግር መንግሥት ምክትል መሪ ጄኔራል መሐመድ ሀምዳን ዳጋሎ የሽግግር ካውንስሉ አሳታፊ እንደሚሆን ተናግረዋል፡፡

‹‹ሁሉም የፖለቲካ ኃይሎች፣ ታጣቂዎች እንዲሁም ከወጣት እስከ አዛውንት ሴትና ወንድ ሳይለይ ለውጥ ለማምጣት ለተሳተፋችሁ ሁሉ ስምምነቱ አሳታፊና ማንንም ያላገለለ ነው፤›› ብለዋል፡፡

የተቃዋሚ ቡድኖች ስብስብ የሆነው ፎርስስ ፎር ፍሪደም ኤንድ ቼንጅ (ኤፍኤፍሲ) መሪ ኦማር አልዲጋር፣ የሽግግር መንግሥት ለመመሥረት የተደረሰው ስምምነት የአዲስ ዘመን መጀመርያ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ዓርብ ሰኔ 28 ቀን 2011 ዓ.ም. የተደረሰው ስምምነት፣ ‹‹የአብዮታችን ማሸነፍ የተረጋገጠበትና ድላችን ያንፀባረቀበት›› ነው ሲል ደግሞ የሱዳን ፕሮፌሽናል አሶስየሽን (ኤስፒኤ) በመግለጫው አመልክቷል፡፡

በስምምነቱ መሠረት መከላከያ ኃይሉ ሉዓላዊውን ካውንስል ለ21 ወራት የሚመራ ሲሆን፣ ቀጣዮቹን 18 ወራት የሲቪል ማኅበረሰቡ ይመራል፡፡ ኤፍኤፍሲ የሚኒስትሮች ምክር ቤት አባላትን ይሰይማል፣ ሕግ አውጭው ካውንስል ደግሞ ሚኒስትሮች ከተሰየሙና ካቢኔ ከተቋቋመ በኋላ የሚቋቋም ይሆናል፡፡

እንደ ስምምነቱ፣ የአፍሪካ ኅብረት ዳኞች ያሉበት የሕግ ባለሙያዎች ኮሚቴ የሚቋቋም ሲሆን፣ ይህም የተደረሰውን ስምምነት በ48 ሰዓታት ውስጥ ማጠቃለል ይጠበቅበታል፡፡

የመጀመርያ ደረጃ በተባለው ስምምነት፣ መከላከያ ኃይሉ ከሲቪል ጋር በጥምረት የሚሠራ በመሆኑ፤ የአብዮቱ መሳካት የሚረጋገጠው ከሦስት ዓመት በኋላ ምርጫ ተካሂዶ የሱዳን መንግሥት ሙሉ ለሙሉ በሲቪል ሲተካ መሆኑን የተቃዋሚዎች መሪ ካሊድ ኦማር ተናግረዋል፡፡

‹‹ኤፍኤፍሲ ብቀላ አይፈልግም›› በማለትም፣ ዓላማቸው አሳታፊ የሆነ ብሔራዊ ዕርቅ ማውረድ እንደሆነም አክለዋል፡፡

አፍሪካ ኅብረትና ኢትዮጵያ በሱዳን የተከሰተውን ቀውስ ለማርገብ የጀመሩት ጥረት ባለፈው ዓርብ የተሳካው ከሁለት ቀናት ውይይት በኋላ ነበር፡፡

በሰኔ መጀመርያ ላይ ወታደራዊ ዕርምጃ መወሰዱን ተከትሎ፣ በሱዳን ጎዳናዎች ለተቃውሞ የሚወጡ ሰዎች ቁጥር ቢቀንስም፣ ከስምምነቱ በኋላ ደስታቸውን ለመግለጽ የወጡ ሱዳናውያን በርካታ እንደነበሩ አልጀዚራ አስፍሯል፡፡

ደስታቸውን ለመግለጽ የወጡትም፣ ወታደራዊ ሽግግር መንግሥቱ የገባውን ስምምነት ተፈጻሚ እንዲያደርግ ግፊት መደረግ እንዳለበት ተናግረዋል፡፡

ወታደራዊ ሽግግር መንግሥቱ (ቲኤምሲ) ለተደረሰው ስምምነት ዋስትና መስጠት አለበት የሚሉት ተቃዋሚዎች፣ መከላከያው ከዚህ ቀደም የገባውን ቃል ሲያጥፍ እንደነበር በማስታወስ አዲሱ ስምምነት የዚህ ሰለባ እንዳይሆን ጥንቃቄ ያስፈልጋል ብለዋል፡፡ ስምምነቱ ጥሩ ጅማሮ ነው፣ ሆኖም ይህ ተተግብሮ ማየት እንፈልጋለን ሲሉም አክለዋል፡፡

የዓረብ ስፕሪንግ ዓይነት አዝማሚያ ነበረው የሚባለውና ሱዳንን ለእርስ በርስ ጦርነት ዳርጎ ቀጣናውንም ያመሳቅላል የተባለው የሱዳን አብዮት፣ ከአምስት ወራት ቀውስ በኋላ መስመር ይዟል፡፡

ኢትዮጵያና አፍሪካ ኅብረት ባደረጉት ጥረት፣ ሱዳን ወደ ሰላም ጎራ ተቀላቅላለች፡፡ በሥልጣን መጋራት ስምምነት የተገኘውን ሰላምም አስመልክቶ፣ የቲኤምሲ ደጋፊ የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ሚኒስትር አንዋር ጋራጋሽ የደስታ መልዕክት በትዊተራቸው አስተላልፈዋል፡፡ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝም እንዲሁ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...