የአንድ መቶ ሠላሳ ሦስት ዓመት ዕድሜዋን ለመዘከር ከአራት ወር ያነሰ ጊዜ የሚቀራት አዲስ አበባ ከተማ፣ በየዐረፍተ ዘመኑ በሕንፃ ግንባታ ዘርፍ ለውጥ በማሳየት ላይ ትገኛለች፡፡ ከነዚህ ዐበይት ሕንፃዎች መካከል መዲናዪቱ በ1962 ዓ.ም. የነበራትን ገጽታ ከአፍሪካ አዳራሽ (ኢሲኤ)፣ እንዲሁም ዘንድሮ ላይ ኢትዮጵያ ሆቴል አካባቢ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እያስገነባ ያለው ሰማይ ጠቀስ ፎቅ በዓይነተኛ መገለጫነት ይጠቀሳሉ፡