Friday, June 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየከተማ አስተዳደሩ ዕግድ የተጣለባቸውን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለይቶ እንዲያሳውቅ ታዘዘ

የከተማ አስተዳደሩ ዕግድ የተጣለባቸውን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለይቶ እንዲያሳውቅ ታዘዘ

ቀን:

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ቁጠባ ቤቶች ልማት ኢንተርፕራይዝ፣ ዕግድ የተጣለባቸውን የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ለይቶ እንዲያሳውቅ በፍርድ ቤት ታዘዘ፡፡

ትዕዛዙን የሰጠው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ስምንተኛ ፍትሐ ብሔር ችሎት ነው፡፡ ኢንተርፕራይዙ ባለሦስት፣ ባለሁለትና ባለአንድ መኝታ የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች በየትኞቹ ሳይትና ብሎክ እንደሚገኙና የተሰጣቸውን የቤት ቁጥር ጭምር ለይቶ እንዲያሳውቅ ተነግሮታል፡፡ ኢንተርፕራይዙ ትዕዛዙን ፈጽሞ የሚቀርበው ሐሙስ ሐምሌ 18 ቀን 2011 ዓ.ም. ነው፡፡

የ40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ዕግድ የተጣለባቸው በምዝገባ ወቅት መቶ በመቶ ክፍያ የፈጸሙ በርካታ ተመዝጋቢዎች ቅድሚያ የዕድሉ ባለቤቶች እንደሚሆኑ ተነግሯቸው ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ውል ከፈጸሙ በኋላ፣ የካቲት 27 ቀን 2011 ዓ.ም. የከተማ አስተዳደሩ ከ18 ሺሕ በላይ የሚሆኑ 40/60 የጋራ መኖሪያ ቤቶችን፣ ከ40 በመቶ በላይ የቆጠቡ ሁሉ በዕጣው በማካተቱና በማውጣቱ ምክንያት ክስ በመመሥረቱ መሆኑ ይታወሳል፡፡

ፍርድ ቤቱ መጀመርያ ክስ ባቀረቡት 98 ሰዎች አቤቱታ መሠረት ሁሉንም ዕጣ የወጣባቸውን የጋራ መኖሪያ ቤቶችና በቀጣይ የሚወጡትም ጭምር ዕግድ የጣለ ቢሆንም፣ ቆይቶ ክስ ባቀረቡት ልክ ብቻ በማገድ የሌሎችን ቤቶች ዕግድ ማንሳቱ ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ጊዜ መቶ በመቶ መክፈላቸውን በመግለጽ ለፍርድ ቤት ክስ ያቀረቡ ተመዝጋቢዎች ቁጥር 700 መድረሱ እየተነገረ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...