Saturday, December 2, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህል‹‹ግጥም በ…ኛ›› በአምስት ቋንቋዎች ይካሄዳል

‹‹ግጥም በ…ኛ›› በአምስት ቋንቋዎች ይካሄዳል

ቀን:

‹‹ግጥም በ…ኛ›› በአምስት ቋንቋዎች ይካሄዳል

‹‹ቋንቋ ይበልጥ ያቀራርባል›› በሚል መሪ ሐሳብ የጀርመን ባህል ማዕከል ያዘጋጀው የግጥም መድረክ፣ በአምስት ቋንቋዎች ሐምሌ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ቴአትርና ባህል አዳራሽ በ11 ሰዓት ይካሄዳል፡፡ ማዕከሉ በላከው መግለጫ እንዳስታወቀው፣ በ‹‹ግጥም በ…ኛ›› የተሰኘው የግጥም ምሽት የሚቀርቡት ግጥሞች እስካሁን ከተለመደው ውጪ በተለያዩ የአገር ውስጥ ቋንቋዎች ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ጋሞኛ፣ ጌዲኦኛ፣ ትግርኛ፣ ጉራጊኛ፣ አፋርኛ ወዘተ ይገኙባቸዋል፡፡ ግጥሞቹ መድረክ ላይ የሚቀርቡት በእነዚህ ቋንቋዎች ቢሆንም፣ ቋንቋውን መናገር ለማይችሉት ታዳምያን የግጥሙ ትርጉም ወይም ደግሞ ጠቅላላ ሐሳቡ ወደ አማርኛ ተተርጉሞ በጽሑፍ ይቀርባል፡፡

******

    የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለመታደግ ያለመው ኮንሰርት

በአዲስ አበባ ያሉ የጎዳና ተዳዳሪዎችን በዘላቂነት ለማቋቋምና ተከታታይ ድጋፍ ለማድረግ ‹‹ያገባኛልይመለከተኛል›› በሚል መሪ ቃል የገቢ ማሰባሰቢያ ኮንሰርት ነሐሴ 4 ቀን 2011 .ም. በሚሌኒየም አዳራሽ ሊካሄድ ነው።

ዝግጅቱን የአዲስ አበባ ከተማ ማኅበራዊ ትረስት ፈንድና የኢትዮጵያ ኢቫንጀሊካል ሊደርስ ፌሎሺፕ በጋራ በመሆን የሚያዘጋጁት እንደሆነ የከተማዋ የሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ቢሮ አስታውቋል፡፡

በዕለቱ የመዝሙር ኮንሰርት ከማካሄድ ባለፈ የማኅበራዊ ትረስት ፈንድ በዋነኛነት ዜጎችን ለመርዳት 6400 በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ድጋፍና በሌሎች የገቢ ማሳባሰቢያ መንገዶች እስከ 100 ሚሊየን ብር የሚደርስ ገቢ እንደሚሰበስብ ይጠበቃል ብሏል መግለጫው፡፡

የጎዳና ተዳዳሪዎችን ለማቋቋም ከአራት ወራት በፊት ወደ ሥራ የገባው የአዲስ አበባ ማኅበራዊ ትረስት ፈንድ ከተለያዩ ምንጮች ድጋፎቹን በማሰባሰብ ወገኖቹን መልሶ ለማቋቋም እየሠራ መሆኑም ተገልጿል

 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...