Tuesday, July 23, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልስምንት አገርኛ ቋንቋዎችን ያስተናገደው የግጥም ምሽት

ስምንት አገርኛ ቋንቋዎችን ያስተናገደው የግጥም ምሽት

ቀን:

‹‹ግጥም ይበልጥ ያቀራርባል!›› በሚል መሪ ቃል በስምንት የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የተዘጋጀው የግጥም ምሽት በአዲስ አበባ ማዘጋጃ ቤት ቲያትርና ባህል አዳራሽ ውስጥ ነሐሴ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. ተካሂዷል፡፡

የጀርመን የባህል ማዕከል ባዘጋጀው ግጥማዊ መሰናዶ ላይ የተለያዩ ገጣምያን በጉራጊኛ፣ ሲዳምኛ፣ ዎላይትኛ፣ ጋሞኛ፣ አፋርኛ፣ ኦሮምኛና ትግርኛ ቋንቋዎች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ያተኮሩ ግጥሞቻቸውን አቅርበዋል፡፡  

በተለያዩ አካባቢዎች በሚነገሩ ቋንቋዎች ገጣሚያን ስለአገር፣ ስለፍቅር፣ ስለሐዘን፣ ስለትዝታ፣ እንዴት ይገልጻሉ የሚለው ለማየት የግጥም ምሽቱ ምቹ መድረክ ነው ያሉት የጀርመን ባህል ማዕከል የመረጃና የቤተ መጻሕፍት ኃላፊ አቶ ዮናስ ታረቀኝ ናቸው፡፡

በምሳሌነትም በአማርኛ የሴት ልጅ ውበትን ለመግለጽ ‹‹አንገቷ መቃ›› ሲባል በጋሞኛ ‹‹አንገቷ ቅልስልስ እንደ ቅል›› በማለት ውበት እንደሚገለጽ፣ የሴት ልጅ የወገብ ቅጥነት ለመግለጽ ደግሞ ‹‹ወገቧ እንደ ቅል›› እያሉ እንደሚያነፃፅሩ አስረድተዋል፡፡

የግጥም ምሽቱ የረዥም ጊዜ ዕቅድ እንደሆነና ከተለያዩ ቦታዎች ለመጡ ገጣሚያን መድረክ ለመፍጠር ያለመ መሆኑን፣ መድረኩ የሀገርን ባህል ለማስተዋወቅም የሚረዳ መሆኑን አውስተዋል፡፡

ግጥሞቹ በተለያዩ የአገር ውስጥ ቋንቋዎች ቢቀርቡም (ቋንቋውን ለማይሰሙ) ታዳሚያን በአማርኛ ተተርጉመው ቀርበዋል፡፡

ከቀረቡት ግጥሞች መካከል አንዱ የአቶ አድማሱ ቱማቶ ቱንታ ወይም ‹‹ጥርስ ምን ቸገረው!›› (Achchawu ay metoo!) የተሰኘው ነው፡፡

‹‹Ashoy xuugettishin suuttaykka penttihin,

Guuggee laatettiini ayfee afuxxishin,

Ganjjee mullugishin maraccee danddayin,

Doonay luullumishin bollay kayyottishin,

Achchay ay metootii garssabaa ay erii,

Miiccawu miicci zaarees keettaawawu ay

maaddii?››

የግጥሙ ትርጉም የሚከተለው ነው፡፡

‹‹ልቡ ሲቃጠል ደሙ እየፈላ፤

አንጎሉ ሲበጠበጥ ነገር እየበላ፤

ጨጓራው ሲላጥ አንጀቱ እየተከነ፤

ጥርስ ግን ይስቃል ምንም እንዳልሆነ፤

ምን ቸገረው ጥርስ ለሳቀው ይስቃል፤

የውስጡን በሽታ ኧረ ማንያውቃል፤

‹‹ግጥም በ…ኛ›› በሚል ፕሮግራም ላይ ከተሳተፉት ገጣሚዎች መካከል በአፋርኛ ያቀረቡት አቶ ዓሊ አብደላ መድረኩ ባለብዙ ብሔር ብሔረሰቦች አገር በሆነችው ኢትዮጵያ የተጻፉ ግጥሞችን ማበረታታት ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

‹‹ስማዕ ዘወደይ›› (ዘውዴ ሆይ ስማኝ) በሚል ርዕስ በትግርኛ የቀረበው ግጥም የሙሉ ጎዲፋይ ገብረ ኢየሱስ ነው

‹‹እኔን ዝቅ አድርጌ…አንተን ግን አክብሬ፤

ከላይ አስቀመጥኩህ…ንጉሥ አደረግኩህ፤

የበላዩን ከታች…ታማኝ ከእውነተኛ፤

ታማሚ ጤነኛ…እንድትለይበት፤

ብዬ ነው እኮ እኔ…ራሴን የሰጠሁህ፤ እንድትቀመጥበት፡፡

የሰውነቴ ንጉሥ፣ በሆነው ራሴ ላይ ተቀምጠህ በሥልጣን፤

የአካላቴን እሮሮ በደንብ ካልሰማኸኝ፤

ስወድቅ ዝም ካለከኝ፤

ዘውዴ ሆይ ስማኝ እውነቱን ልንገርህ፤

ከተቀመጥክበት ከራሴ ላይ ወድቀህ ትፈጠፈጣለህ!››

በወላይታ ዩኒቨርሲቲ የቋንቋ መምህሩ አቶ አድማሱ ቱማቶ ቱንታ መድረኩ መፈጠሩ ቋንቋዎችን ለማሳደግና ልምድ ለመለዋወጥ እንደሚጠቅም ገልጸዋል፡፡ አክለውም እንደሌሎቹ ቋንቋዎች ሁሉ በወላይትኛ የተለያዩ አባባሎች፣ እንቆቅልሽ፣ ተረት፣ ምሳሌያዊ ንግግር እንደሚናገሩ ለማሳየት የግጥም ምሽት መድረክ ምቹ እንደሆነ፣ ለወደፊትም መንግሥት መሰል መድረኮችን ፈጥሮ ቋንቋዎችንና ባህሎችንም ለማሳደግ መሥራት ተገቢ እንደሆነ አውስተዋል፡፡ 

‹‹ናፈቀችኝ››

ልተኛ! አትተኛም!

ልቀመጥ! አትቀመጥ!

ልሥራ! አትሥራ!

ልጫወት! አትጫወት!

ብላኝ

ተቅበዝባዥ አድርጋኝ፡፡

እኔን ግን ግራ አጋብታኝ፤

ናፈቀችኝ፡፡›› የሚለውን ግጥም በጌዴኦኛ ያቀረበው በፈቃዱ ንጉሤ ዲዳ ነው፡፡ ሌሎች ገጣሚያን በአፋርኛ፣ በጋሞኛ፣ በጌዴኦኛ፣ በጉራጊኛ፣ በኦሮሚኛ፣ በሲዳሚኛ፣ በትግርኛ፣ በወላይታኛ ቋንቋዎች አንድና ከአንድ በላይ ግጥሞች አቅርበዋል፡፡ ከነዚህም መካከል አቶ አል አብደላ ዓሊ Hyobbiyah Hyobbiyah xayloy ayloy (ለኢትዮጵያ ሕዝቦች)፣ አቶ ካፓ ካንሳ ጌኖ Kawotizaytadreta (የነገሥታት አገር)፣ አቶ ተስፋዬ ጎይቴ ወልደማርያም ይናም ቢናም (እኛ)፣ አቶ ጌቱ በቀለ ዳዲ Hin gadisini qeye`a (ቀየህን አትልቀቅ)፣ አቶ ባጢሶ ዮሐንስ ሌንካ Gingilaaticho`ya (ትንሿ ከበሮዬ)፣ አቶ አድማሱ ቱሚቶ ቱንታ Achuhawu ay metoo! (ጥርስ ምን ቸገረው)፣ ያቀረቡት ይጠቀሳል፡፡

ገጣሚያኑን ከየአካባቢው ለማሰባሰብ አዳጋች የነበረ ቢሆንም በየክልሉ ባህል ቱሪዝም ቢሮ እንዲሁም በሰው በሰው ለማግኘት መቻሉን ያወሱት አቶ ዮናስ ከተገኙት ገጣሚያን በየቋንቋቸው መጻሕፍት የጻፉ መኖራቸውን ገልጸዋል፡፡ ለቀጣይነቱም ከባህልና ቱሪዝም፣ ከደራስያን ማኅበር ጋር በጋራ ከተሠራ ቀጣይነት ይኖረዋል ብለዋል፡፡ ‹‹ብሔራዊ የግጥም ፌስቲቫል ለማዘጋጀት ጥሩ የልምድና የባህል ልውውጥ ለማድረግ አብሮነት ያስፈልጋል፤›› በማለትም አመልክተዋል፡፡

በሔለን ተስፋዬና በተመስገን ተጋፋው

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ኢትዮጵያዊ ማን ነው/ናት? ለምክክሩስ መግባባት አለን?

በደምስ ጫንያለው (ዶ/ር) የጽሑፉ መነሻ ዛሬ በአገራችን ውስጥ በተለያዩ አካባቢዎች ግጭቶችና...

ዴሞክራሲ ጫካ ውስጥ አይደገስም

በገነት ዓለሙ የዛሬ ሳምንት ባነሳሁት የኢሰመኮ ሪፖርት መነሻነትና በዚያም ምክንያት...

ኢትዮጵያ በምግብ ራሷን የምትችለው መቼ ነው?

መድረኩ ጠንከር ያሉ የፖሊሲ ጉዳዮች የተነሱበት ነበር፡፡ ስለረሃብ፣ ስለምግብ፣...

ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም በሌላት አገር ዘመናዊ ስታዲየም እየገነቡ ያሉ ክልሎች

አዲሱ የማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ዘመናዊ ስታዲየም ለማስገንባት ከ500 ሚሊዮን...