Saturday, December 3, 2022
ሌሎች ዓምዶች
  - Advertisment -
  - Advertisment -

  ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸውን ቢሯቸው አስጠሩት

  [ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር ወደ ቢሮ እየሄዱ ነው]

  • ያስተዛዝባል ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምኑ ነው የሚያስተዛዝበው?
  • ሁሉ ነገር፡፡
  • ምን ጎደለብህ ደግሞ?
  • መቼ ሞልቶልኝ ያውቃል?
  • አንተ በቃ ሁሌ ማማረር ነው፡፡
  • አትፍረድ ይፈረድብሃል ሲባል አልሰሙም?
  • ምን?
  • ለነገሩ እናንተ ላይ ማን ይፈርዳል?
  • እንዴት?
  • ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ አይደል ተረቱ፡፡
  • ማን ነው ንጉሥ?
  • እርስዎ ነዎታ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ኧረ እኔ ክቡር ሚኒስትር ነኝ፡፡
  • ያው ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን ለማለት ፈልገህ ነው?
  • ለውጡን እኮ ብዙ ተስፋ አድርገንበት ነበር፡፡
  • እንዴት ማለት?
  • በቃ ለውጡ ሁሉን ነገር ይለዋውጥልናል ብለን አስበን ነበር፡፡
  • ለውጥ ከራስ ነው የሚጀምረው፡፡
  • እናንተ መቼ ነው ታዲያ የምትለወጡት?
  • ምን እያልክ ነው?
  • ለነገሩ ረስቼው እንጂ እናንተም ተለውጣችኋል፡፡
  • ተለውጠናል አይደል?
  • ምን እናንተ ብቻ እኛም ተለውጠናል፡፡
  • ወደ ምንድነው የተለወጣችሁት?
  • ከደሃ ወደ ደሃ ደሃ፡፡
  • ምን?
  • ሦስቴ ከመብላት ወደ አንዴ መብላት፡፡
  • እ…
  • ከኮንዶሚኒየም ወደ ጭቃ ቤት ተለውጠናል፡፡
  • ምንድነው የምታወራው?
  • ለውጥ አለ እያልኩዎት ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እያሾፍክብኝ ነው፡፡
  • ምን ላድርግ ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት ማለት?
  • በለውጡ ስንት ተስፋ አድርገን ነበር፡፡
  • ምን ሆነ ታዲያ ለውጡ?
  • ይኸው እኛን ያልሆነ አለዋወጥ ለውጦናል፡፡
  • ምን ማለት ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር አልቻልኩትም፡፡
  • ምኑን?
  • የኑሮ ውድነቱን፡፡
  • እሱማ የሁሉም ችግር ነው፡፡
  • የእኔ ግን ይብሳል ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እ…
  • መሸከም ከምችለው በላይ ሆኖብኛል፡፡
  • አይዞህ በርታ እንጂ፡፡
  • ኑሮ ውድነቱ መቼ በምርቃት ይቻላል?
  • እ…
  • አሁንማ መሮኛል፡፡
  • ኧረ ተው፡፡
  • እንዲያውም በቅርቡ ሥራ እለቃለሁ፡፡
  • ጭራሽ?
  • አዎ ከሾፌርነት የተሻለ የሥራ ዘርፍ አግኝቻለሁ፡፡
  • ምን ልትሆን?
  • ለማኝ!

  [ክቡር ሚኒስትሩ ስብሰባ ላይ ከአንድ ተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጋር ተገናኙ]

  • ሰላም ነው ክቡር ሚኒስትር?
  • እየተዘጋጃችሁ ነው?
  • ለምኑ ክቡር ሚኒስትር?
  • ለምርጫው ነዋ፡፡
  • ምርጫው ይካሄዳል እንዴ?
  • ለምን አይካሄድም?
  • አገራችን እንዲህ ተወጣጥራ እንዴት ምርጫ ይካሄዳል?
  • መቼም ሕገ መንግሥቱ አይጣስም?
  • ክቡር ሚኒስትር ከምንም ነገር በላይ ሕዝብና አገር ነው የሚቀድመው፡፡
  • ለዚያ እኮ ነው ሕገ መንግሥት ያረቀቅነው፡፡
  • እሱን እንኳን ይተውት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዴት?
  • አሁን ሕገ መንግሥቱ ለሕዝብና ለአገር አስባችሁ ነው ወይስ ለራሳችሁ አስባችሁ ነው ያረቀቃችሁት፡፡
  • እኔ እኮ ተቃዋሚዎች ስትባሉ ታስቁኛላችሁ፡፡
  • በምንድነው የምናስቅዎት?
  • በቃ ይኼ ነው የሚባል አጀንዳ እንኳን የላችሁም፡፡
  • እንዳይሳሳቱ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ይኸው ሕገ መንግሥቱ ስላለ አይደል እናንተ እንኳን የምታንቀሳቅሱት፡፡
  • እኛ ሕዝብ ስለሚደግፈን ነው ያለነው፡፡
  • ኪኪኪ…
  • ምንድነው የሚያስቅዎት?
  • ሕዝብ ነው ያልከኝ?
  • አዎ ምነው?
  • አንተና ቤተሰብህ የምትደግፉት ፓርቲ ይዘህ ሕዝብ ስትል አታፍርም?
  • እኔና ቤተሰቤም ብንሆን እኮ የሕዝቡ አካል ነን፡፡
  • በል ሰው እንዳይሰማህ፡፡
  • ምኑን?
  • በእውነት እኛ ከእናንተ ጋር እንዴት ነው የምንወዳደረው?
  • ሙያ በልብ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እኛም ከእናንተ ጋር ተወዳድረን አሸነፍን ስንል ያሳፍራል፡፡
  • ለዚህ እኮ ተጠያቂው እናንተው ናችሁ፡፡
  • እንዴት?
  • የተቃዋሚ ፓርቲዎች እንዲቀጭጩ ያደረጋችሁት ራሳችሁ ናችኋ፡፡
  • ይኼ ለቅሷችሁ መቼ እንደሚያባራ አላውቅም፡፡
  • እናንተ ከሥልጣን ስትወገዱ ነዋ፡፡
  • አሁንስ ያችን ቀበሮ መሰልከኝ፡፡
  • የቷ ቀበሮ?
  • የበሬው እንትን ይወድቃል ብላ የምትከተለዋ፡፡
  • እርሱን እንተያያለን፡፡
  • የት ነው የምንተያየው?
  • በቀጣዩ ምርጫ ነዋ፡፡
  • ስለመኖሩ እየተጠራጠርክ አይደል እንዴ?
  • ካለ ግን አንላቀቅም ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ለማንኛውም ምርጫው ቀርቶባችሁ ብትደራጁ ይሻላል፡፡
  • በምንድነው የምንደራጀው?
  • በአነስተኛና ጥቃቅን!

  [ለክቡር ሚኒስትሩ አንድ ባለሀብት ስልክ ይደውልላቸዋል]

  • እንዴት ነዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • እንዴት ነህ ወዳጄ?
  • ለውጥማ አለ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • አለ አይደል?
  • ምን ጥያቄ አለው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ምን ላድርግህ?
  • ይኸው በአገራችን በነፃነት እየተንቀሳቀስን ነው፡፡
  • ልክ ነህ፡፡
  • የበፊቱ ሥርዓት እኮ ሥርዓት እንዳይመስልዎት፡፡
  • እንዴት?
  • በቃ በየቀኑ ሰቀቀን ነበር፡፡
  • እንዳንተ ዓይነቱን ነው ማብዛት ያለብን፡፡
  • የጊዜ ጉዳይ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዴት?
  • ያው ፖሊሲያችሁ የመደመደር አይደል?
  • እሱማ ልክ ነው፡፡
  • ስለዚህ ብዜት ትፈጥናለች እንጂ መደመር እኮ መጨመሯ አይቀርም፡፡
  • ምን ላድርግህ አንተ?
  • አያስቡ ከጎናችሁ ነን ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • በጣም ልትደግፉን ይገባል፡፡
  • ስለእሱ ሐሳብ እንዳይገባዎት ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ድጋፋችሁን አጠናክራችሁ መቀጠል አለባችሁ፡፡
  • ይኸው የተጠየቅኩትን ነገር እያደረኩ ነው፡፡
  • ምን ምን አደረክ?
  • ስፍር ቁጥር የሌለው ችግኝ ነው የተከልኩት፡፡
  • እ. . .
  • ደብተርና እስኪርቢቶም ቢሆን ሰጥቻለሁ፡፡
  • ጥሩ ነው፡፡
  • ከዚህ በላይ ግን ማድረግ የምፈልገው ነገር አለ፡፡
  • ምንድነው እሱ?
  • እርስዎ ሁሌ ያሳዝኑኛል፡፡
  • እንዴት?
  • በቃ ለሕዝቡ እንዲህ ሲሯሯጡ ለእርስዎስ ማን ያደርግልዎት ይሆን ብዬ አስባለሁ፡፡
  • እኔማ ከእግዚአብሔር አገኘዋለሁ፡፡
  • ፈቃደኛ ከሆኑማ ከሌላም ያገኙታል፡፡
  • ከሌላ ከማን?
  • ከእኔ ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • እንዴት?
  • በቃ ልጆችዎን ለማስተማር ወስኛለሁ፡፡
  • እ. . .
  • ውጭ አገር ሄደው መማር አለባቸው፡፡
  • እሱማ ጥሩ ነበር ግን. . .
  • ግን ምን?
  • ወጪው አይቻልማ፡፡
  • ስለእሱ ፈጽመው እንዳይጨነቁ፡፡
  • እንዴት?
  • እኔ ሙሉ ወጪውን እችላለሁ፡፡
  • እ. . .
  • ባይሆን ከእርስዎ አንድ ነገር ነው የምፈልገው፡፡
  • ምን?
  • መሬት!

  [ክቡር ሚኒስትሩ አማካሪያቸውን ቢሯቸው አስጠሩት]

  • ፈለጉኝ ክቡር ሚኒስትር?
  • ቁጭ በል እስኪ፡፡
  • ምነው?
  • ምርጫው እየተቃረበ እንደሆነ  ታውቃለህ?
  • በአሪፍ እየተዘጋጀን ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
  • ሕዝቡ ከእኛ ብዙ ነው የሚጠብቀው፡፡
  • እኛም ከሕዝቡ እንደዚያው፡፡
  • እንዴት ማለት?
  • ባለፈው ምርጫ መቶ በመቶ እኮ ነው ያመጣነው፡፡
  • አሁን ይደገማል ብለህ ነው?
  • ክቡር ሚኒስትር ድርብ ድርብርብ ድል ነው የምንጠብቀው፡፡
  • እንደዚያ እንኳን ላይሆን ይችላል፡፡
  • ምን ነካዎት ክቡር ሚኒስትር?
  • ምነው?
  • ወጣቱን ከያዝነው ሌላው ችግር የለውም፡፡
  • እንዴት?
  • ከአገሪቱ ሕዝብ 70 በመቶ ወጣት ነዋ፡፡
  • እሱስ ልክ ነህ፡፡
  • ስለዚህ ለወጣቱ ደግሞ እየረጨነው ነው፡፡
  • ምኑን?
  • ገንዘቡን ነዋ፡፡
  • በጣም ጥሩ፡፡
  • በቃ ወጣቱን ለሥራ በሚል እያመቻቸነው ነው፡፡
  • መቼም ገንዘቡን ስታድሏቸው ቢሮክራሲ አታበዙባቸውም አይደል?
  • ኧረ ተያዥ ራሱ እርስ በርስ ነው የሚሆኑት፡፡
  • በጣም ጥሩ፡፡
  • ስለዚህ ተደራጅተው ለሚመጡት በቀላሉ ነው የምንሰጣቸው፡፡
  • ዋናው ስታደራጇቸው መጠቀም ያለባችሁ መሥፈርት አለ፡፡
  • በምን ይደራጁ?
  • በወንዝ!

   

  በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

  አሜሪካ ሕወሓትን በማሳመንና በመጫን በሰላም ሒደቱ ትልቅ ሚና መጫወቷን የኢትዮጵያ ዋና ተደራዳሪ አስታወቁ

  የተመድና የአውሮፓ ኅብረት አበርክቶ አሉታዊ እንደነበር ጠቁመዋል በመንግሥትና በሕወሓት መካከል...

  የአየር መንገድ ተጓዦች በሻንጣ የሚያስገቡትን የልብስና የጫማ ብዛት የሚገድብ ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ

  ከቀረጥ ነፃ ይገቡ የነበሩ ዕቃዎች 87 በመቶ እንዲቀንሱ ተደርጓል መንገደኞች...

  አዲስ አበባና ኦሮሚያ ወሰን ለማካለል ተስማሙ

  ኮዬ ፈጬ፣ ቱሉዲምቱ፣ ጀሞ ቁጥር 2 ወደ ኦሮሚያ ለቡ፣ ፉሪና...

  በቤንዚንና ነጭ ናፍጣ ላይ ጭማሪ ተደረገ

  ከዛሬ መስከረም 18 ቀን 2015 ዓም እኩለ ሌሊት ጀምሮ...
  - Advertisment -

  ትኩስ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር!...

  የጉራጌ ዞን ጥያቄና የክላስተር አደረጃጀት የገጠመው ተቃውሞ

  መንግሥት የደቡብ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል አካል የነበሩ ዞኖችንና...

  አዋሽ ባንክ ካፒታሉን ወደ 55 ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ያስገደደው ምክንያት ምንድን ነው?

  ባለፈው ቅዳሜ ጠቅላላ ጉባዔውን ያካሄደው አዋሽ ባንክ የ43 ቢሊዮን...

  አቢሲኒያ ባንክ ካለፈው ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው ትርፍ በማግኘት አዲስ ታሪክ አስመዘገበ

  አቢሲኒያ ባንክ ከቀደሚ የሒሳብ ዓመት የ127 በመቶ ብልጫ ያለው...

  የጉድለታችን ብዛቱ!

  ከፒያሳ ወደ ሜክሲኮ ልንጓዝ ነው። ጎዳናውን ትውስታ እየናጠው ሁለትና...
  spot_img

  ተዛማጅ ፅሁፎች

  [በተቋሙ ሠራተኞች የተወከሉ አንድ ባልደረባ ሚኒስትሩን ለማነጋገር ቀጠሮ ይዘው ወደ ቢሯቸው ገቡ]

  ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም ሰላም ... ተቀመጥ! አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር! ቀድሜ ቀጠሮ እንዲያዝልኝ ስጠይቅ እንደገለጽኩት በተቋሙ ሠራተኛ ተወክዬ ነው የመጣሁት። እንዴ? አንተ የእኛ ተቋም ባልደረባ አይደለህም...

  [የተቃዋሚ ፓርቲው ትይዩ ሚኒስትር ክቡር ሚኒስትሩ ጋ ደውለው መንግሥት በሙሰኞች ላይ ለመውሰድ ስላሰበው የሕግ ዕርምጃ ሐሳብ እየተለዋወጡ ነው]

  ሄሎ… ማን ልበል? ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ጤና ይስጥልኝ… ማን ልበል? የእርስዎ ትይዩ ነኝ፡፡  አቤት? ያው ፓርቲዬን ወክዬ የፍትሕ ሚኒስትሩ ትይዩ ነኝ ማለቴ ነው፡፡ ኦ... ገባኝ… ገባኝ...  ትንሽ ግራ አገባሁዎት አይደል? ትይዩ...

   [ክቡር ሚኒስትሩ እራት እየበሉ መንግሥትን በሚተቹ ጋዜጠኞች ላይ እየተወሰደ ያለውን ዕርምጃ የተመለከተ መረጃ እየቀረበላቸው ነው]

  ለጋዜጠኞቹ መንግሥትን እንዲተቹ መረጃ የሚሰጧቸው ታሪካዊ ጠላቶቻችን ናቸው፡፡ እነሱ አይደሉም፡፡ እና የትኞቹ ናቸው? እዚሁ ከተማችን የሚገኙ ምዕራባውያን ናቸው። እንዴት ነው መረጃውን የሚያቀብሏቸው? እራት እያበሉ ነው። ምን? አዎ፣ እራት ግብዣ ይጠሯቸውና መተቸት...