የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ያደራጀውና በምዕራብ አዲስ አበባ ሰሚት አካባቢ በሚገኘው የሰሚት ኢንዱስትሪ ማዕከል የተገነቡት የዋንዛ ፈርኒሺንግስ ኢንዱስትሪ ና የአዲስ ጋዝና ፕላስቲክስ ፋብሪካ ሕንፃዎች ነሐሴ 2 ቀን 2011 ዓ.ም. ተመርቀዋል፡፡ መራቂዎቹ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ተካ ገብረ ኢየሱስና የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ/ ፕሬዚዳንት አረጋ ይርዳው (ዶ/ር) ናቸው። ፎቶዎቹ የምረቃውን ገጽታ በከፊል ያሳያሉ፡፡