የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ የክለብ ተጫዋቾች የደመወዝ ጣሪያ በወር 50 ሺሕ ብር እንዲሆን ተወሰነ፡፡ ዓርብ ነሐሴ 3 ቀን 2011 ዓ.ም. የስፖርት ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን፣ የክልል ስፖርት ቢሮ ኃላፊዎችና 14 የፕሪሚየር ሊግ ክለቦች አመራሮች በተገኙበት ቢሾፍቱ በተደረገው ጉባዔ ላይ ውሳኔው ተላልፏል፡፡
በውሳኔ ላይ ሁለቱ የአዲስ አበባ ክለቦች ቅዱስ ጊዮርጊስና ኢትዮጵያ ቡና አልተገኙም፡፡