ጥሬ ዕቃዎች
- 5 መካከለኛ ጭልፋ (ግማሽ ኪሎ ግራም) ፀድቶ በሎሚ የተለወሰ የተገረደፈ ቲላፒያ
- 2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) የተገረደፈ ቀይ ሽንኩርት
- 1 መካከለኛ ጭልፋ (100 ግራም) የተገረደፈ ባሮ ሽንኩርት
- 4 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ነጭ ሽንኩርት
- 2 የሾርባ ማንኪያ የደቀቀ ዝንጅብል
- 1 የቡና ሲኒ (100 ግራም) ድፍን ምስር
- 4 ቃርያ
- 2 የሻይ ማንኪያ ጨው
- የ1 ሎሚ ጭማቂ (መለወሻ)
አዘገጃጀት
- ምስሩን በደንብ አጥቦ መጣድ፤
- እንዲበስል ውኃ ጨምሮ መተው፤
- ግማሽ ብስል ሲሆን ቀይ ሽንኩርት፣ ባሮ ሽንኩርትና ዝንጅብል መጨመር፤
- ሳይበዛ በመጠኑ ውኃ ጨምሮ እንዲፈላ መተው፤
- ሲፈላ አረፋውን ከላይ እየገፈፉ ማንሳት፤
- ምስሩና ሽንኩርቱ መብሰሉ ሲረጋገጥ ዓሳውን ጨምሮ ማንተክተክ፤
- ነጭ ሽንኩርት መጨመርና እሳቱን ዝቅ አድርጐ አንሰክስኮ ጨው መጨመር፤
- በቂ መረቅ እንዲኖረው አስተካክሎ ድፍኑን ቃርያ ጨምሮ ማውጣት፤
- ለገበታ ሲቀርብ ቃርያውን አውጥቶ ማቅረብ፡፡
- ደብረወርቅ አባተ (ሱሼፍ) “የባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት” (2003)