Thursday, July 25, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልዩኔስኮ ባለ ስድስት መጠሪያውን የነሐሴ በዓል የሚመለከተው ከሁለት ዓመት በኋላ ነው

ዩኔስኮ ባለ ስድስት መጠሪያውን የነሐሴ በዓል የሚመለከተው ከሁለት ዓመት በኋላ ነው

ቀን:

በሰሜን ኢትዮጵያ በተለያዩ ማኅበረሰቦች ዘንድ በነሐሴ ወር አጋማሽ በልጃገረዶችና በሴቶች የሚከበረው በዓል ከፍልሰታ ለማርያም ክብር ጋር የተያያዘ እንደሆነ ይወሳል፡፡

ይህ በትግራይ አሸንዳ፣ ዓይን ዋሪ፣ ማርያ፤ በሰቆጣ ሻደይ፣ በላስታ ላሊበላ፣ በደቡብ ጎንደር አሸንድዬ፣ በቆቦ ሶለል በሚባል የሚጠራው ክብረ በዓል ሴቶች በባህላዊ አልባሳትና ጌጣ ጌጦች ተውበውና አደባባይ ወጥተው የሚያከብሩት በዓል ነው፡፡

ነሐሴ 16 ቀን ከሚከበረው የፍልሰታ ማርያም በዓል ጋር ተያይዞ ከዋዜማው እስከ ማግስቱ በገጠርና በከተማ እየተከበረ ይገኛል፡፡ ከሕፃን እስከ አዋቂ የአሸንዳ ቅጠልን አሸርጠው አደባባይ በመውጣትና በየቤቱ በመዞር እየጨፈሩና እያዜሙ ያከብሩታል፡፡

የፀጉር አሠራራቸው በትግራይ ከአልባሶ እስከ ግልብጭ፣ ከጋመ እስከ ድርብ፤ በሰቆጣና በላሊበላ ጋሜ፣ ቁንጮ፣ ግልብጭ፣ ሳዱላና ቅርድድ ተሠርተው ይታዩበታል፡፡ ጌጣ ጌጣቸውም ልዩ ልዩ ዓይነት ሕንቆ፣ አልቦ፣ ድሪ፣ ድኮት፣ ጉትቻ፣ ማርዳ መስቀል ሲሆን፣ አለባበሳቸውም በመልጉም (ባለጥልፍ ቀሚስ)፣ ሹፎን፣ ጀርሲና በመሳሰሉት ይሆናል፡፡

ዘንድሮ እንደወትሮው ሁሉ ክብረ በዓሉ በመቐለ፣ በሰቆጣ፣ በላሊበላ፣ በአክሱም፣ በደብረ ታቦርና በባሕር ዳር ከተሞች እንዲሁም በአዲስ አበባም በየማኅበረሰቡ በልዩ ልዩ ዝግጅት እንደሚከበር አዘጋጆቹ አስታውቀዋል፡፡ በተለይ በመቐለ እና በሰቆጣ ክብረ በዓሉን አስመልክቶ ዐውደ ጥናት እንደሚካሄድ ታውቋል፡፡

የዩኔስኮ ምዝገባ

ባህልን የሚመለከተው የመንግሥታቱ ድርጅት ዩኔስኮ በየአገሩ ከሚገኙ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶች መካከል በየዓመቱ የሰው ልጅ ወካይ በሚል በዓለም ቅርስነት ይመዘግባል፡፡ ኢትዮጵያ እስካሁን ሦስት የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶችን የመስቀል፣ የፊቼ ጫምባላላ በዓላትና የገዳ ሥርዓት በዩኔስኮ ተመዝግቦላታል፡፡ ከዓመታት በፊት ሰነዱ የተላከው የጥምቀት ክብረ በዓል በመጪው ኅዳር 2012 ዓ.ም. በሚካሄደው 14ኛ ስብሰባ ውሳኔ ይሰጥበታል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ዩኔስኮ የማይዳሰሱ ባህላዊ ቅርሶችን ለአንድ አገር የሚመዘግበው ቢያንስ በየሁለት ዓመት ልዩነት ውስጥ ነው፡፡ በዓለም አቀፉ ተቋም ድረ ገጽ እንደተመለከተው የ2019 ፋይሎች ውስጥ ለውሳኔ ከቀረቡት 54 ፋይሎች አንዱ ጥምቀት ሲሆን፣ በ2020 ፋይሎች ውስጥ ለኅዳር 2013 ዓ.ም. ለውሳኔ ከሚታዩት 42 ፋይሎች ውስጥ ኢትዮጵያ የለችበትም፡፡ በይደር (Backlog) ፋይል (2020) ውስጥ ያለተጨማሪ ሰነዶች ርዕሳቸው ከተዘረዘሩት ውስጥ ግን እነ አሸንዳ አሉበት፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

“ከሁለት ሳምንት በፊት ወደ ኤርትራ የማደርገውን በረራ እንዳሳድግ ተጠይቄ ነበር” የኢትዮጵያ አየር መንገድ

ኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ የሚያደርገውን በረራ እንዲያሳድግ የሚጠይቅ...
00:06:46

የኤርትራ አቪዬሽን ባለሥልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራዎችን ማገዱን አስታወቀ

የኢትዮጵያ ሲቪል አቪዬሽን ባለሥልጣን ጉዳዩን እያጣራሁ ነው ብሏል በኤርትራ ትራንስፖርትና...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተቋሙ የሠራተኞች ማኅበር አመራር ጋር እየተወያዩ ነው]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? ሰላም! በአስቸኳይ እንደፈለጉኝ መልዕክት ደርሶኝ ነው የመጣሁት። አዎ።...

የሱዳን ጦርነትና የኢትዮጵያ ሥጋት

የሱዳን ጦርነት ከጀመረ አንድ ዓመት ከአራት ወራት አስቆጠረ፡፡ ጦርነቱ...