2 ኩላሊት
1 እንቁላል
1 የሾርባ ማንኪያ ውኃ
1 ብርጭቆ የተፈረፈረ ደረቅ ዳቦ
1 የቡና ስኒ ቅቤ
½ ኩባያ ዘይት
ጨው ቁንዶ በርበሬ
አሠራር
- ኩላሊቱን ለአንድ ሰዓት ያህል ጨው በገባበት ውኃ መዘፍዘፍ፡፡
- ኩላሊቱን መላጥና አራት ቦታ መክፈል፡፡
- እንቁላሉን ከአንድ የሾርባ ማንኪያ ውኃ ጋር መምታት፡፡
- ኩላሊቱን የተመታው እንቁላል ውስጥ መጨመር፡፡
- የተፈረፈረውን ዳቦ መውቀጥ፣ ወይም መፍጨትና መንፋት፡፡
- ኩላሊቱን የዳቦው ዱቄት ላይ ማንከባለል፡፡
- ዘይትና ቁንዶ በርበሬ መጥበሻ ላይ ጨምሮ መጣድና የተሰናዳውን ኩላሊት መጥበስ፡፡
- አጋም ሲመስል ማውጣት፡፡
- ጽጌ ዑቁባሚኣኬል ‹‹የእናት ጓዳ›› (1984)