Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትእግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለያዩ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተወጥሯል

እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለያዩ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተወጥሯል

ቀን:

የብሔራዊ ቡድኑ የሆቴል ዕዳ ጥያቄ አስነሳ

በአቶ ኢሳያስ ጅራ የሚመራው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሁለት ዓመት ቆይታው የመጀመርያው የሆነውን ተደራራቢ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ የውድድር መርሐ ግብር ገጥሞታል፡፡ እነዚህም በሴቶች ለጃፓን ቶኮዮ 2020 ኦሊምፒክ ማጣሪያ፣ በዋናው ቡድን ደግሞ ለኳታሩ 2022 የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያና ለአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) እንዲሁም ዕድሜያቸው ከሃያ ዓመት በታች ለምሥራቅና መካከለኛው የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ሴካፋ) ሲሆኑ፣ ዝግጅቶቹ በባሕር ዳርና በአዲስ አበባ ተጀምረዋል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ከዚህ በፊት በአዲስ አበባና በሐዋሳ በቆየባቸው የዝግጅት ምዕራፎች በሚሊዮን የሚቆጠር የሆቴል ዕዳ እንዳለበት፣ አንዳንዶቹም ተቋሙ ለአገልግሎት የተጠቀመበትን ዕዳ እንዲከፍል ካልሆነ ግን ጉዳዩን ወደ ሕግ እንደሚወስዱት ማስጠንቀቂያ የሰጡበት አግባብ መኖሩን ጭምር ከሆቴሎቹ ባለቤቶች አንዳንዶቹ ለሪፖርተር ገልጸዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ቀደም ሲል ከነበሩት የፌዴሬሽኑ አመራሮች ዘመን ጀምሮ ለዝግጅት የተጠቀመባቸው በርካታ የገንዘብ ዕዳ እንዳለበት ሲነገር ቆይቷል፡፡ አመራሮቹ ይህንኑ መነሻ በማድረግ ቀደም ሲል የነበሩትም ሆነ አሁን ያሉት፣ የሌሎችን አገሮች ተሞክሮ በማሳያነት በመውሰድ የብሔራዊ ቡድን ዝግጅት ወጪዎች የሚሸፈኑት በመንግሥት መሆኑን ነው፤ አሁንም የአቶ ኢሳያስ አመራር ይህንኑ ጥያቄ አጠናክሮ የቀጠለበት ስለመሆኑ ጭምር አቶ ኢሳያስ ከጉዳዩ ጋር በተገናኘ ቀደም ሲል ከሪፖርተር ጋር በነበራቸው ቆይታ መግለጻቸው የሚታወስ ነው፡፡ 

እግር ኳስ ፌዴሬሽን በተለያዩ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ ውድድሮች ተወጥሯል

 

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት የተቋሙን ዕዳ በሚመለከት፣ ከሆቴልና መሰል ዕዳዎች በተጨማሪ ክለቦች ከሜዳ ገቢ ማግኘት የሚገባቸው፣ ግን ፌዴሬሽኑ መክፈል ያልቻለው እስከ ስምንት ሚሊዮዮን ብር የሚገመት የገንዘብ ዕዳ እንዳለበት መግለጻቸው ጭምር አይዘነጋም፡፡

በዚህ ሁሉ ተግዳሮት ውስጥ እያለፈ የሚገኘው ብሔራዊ ፌዴሬሽኑ፣ በአሁኑ ወቅት በአኅጉራዊና ዓለም አቀፍ የውድድር መርሐ ግብሮች ተወጥሮ ይገኛል፡፡ ከመርሐ ግብሮቹ መካከል በጃፓን ቶኪዮ ለሚካሄደው ኦሊምፒክ ከፊት ለፊቱ ከካሜሮን አቻው ጋር ነሐሴ 20 ቀን 2011 .. በባሕር ዳር ስታዲየም ጠንካራ ፉክክር የሚጠብቀው የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሊምፒክ ቡድን አንዱ ሲሆን፣ ሁለት ወሳኝ የማጣሪያ ጨዋታዎች ማለትም ለኳታሩ ዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሌሴቶ አቻው ጋር ነሐሴ 28 ቀን እንዲሁም በካሜሮን አስተናጋጅነት 2020 ለሚከናወነው የአፍሪካ አገሮች ዋንጫ (ቻን) ደግሞ ከሩዋንዳ አቻው ጋር መስከረም 11 ቀን 2012 .. በባሕር ዳርና በትግራይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም የሚያደርጋቸው ጨዋታዎች ተጠቃሽ ናቸው፡፡

ሌላው ደግሞ በመጪው አዲስ ዓመት በመስከረም ወር መባቻ ዕድሜያቸው ከሃያ ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድኖች በኡጋንዳ አስተናጋጅነት እንደሚከናወን የሚጠበቀው የምሥራቅና መካከለኛው አፍሪካ አገሮች (ሴካፋ) ሻምፒዮና ነው፡፡ የፌዴሬሽኑ አዲሱ አመራር የተቋሙን ኃላፊነት ከተረከበ በኋላ እንዲህ እንደ አሁኑ ተደራራቢ አኅጉራዊና ዓለም አቀፍ መድረኮች ሲገጥሙት የመጀመርያው መሆኑ ነው፡፡ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ አምስተኛው ዝግጅት በኤርትራ አስተናጋጅነት በተካሄደውና ዕድሜያቸው 15 ዓመት በታች የሴካፋ ሻምፒዮና ሲሆን፣ ደያበውድድሩ የተሳተፈው የኢትዮጵያ ታዳጊ ቡድን በኡጋንዳና በሩዋንዳ በሰፊ የጎል ልዩነት ከተሸነፈ በኋላ ከሱዳን ጋር ደግሞ በአቻ ውጤት ተለያይቶ በጊዜ ተሰናብቷል።

በሌላ በኩል የዋሊያዎቹ ዋና አሠልጣኝ ኢንስትራክተር አብርሃም መብራቱ ከሦስት ወር በፊት በሞሮኮ ራባት በተሰጠው የኤሊት ኢንስትራክተሮች (የአሠልጣኞች አሠልጣኝ) ሥልጠና ላይ ተሳትፈው የተሰጠውን ሥልጠና በብቃት በማጠናቀቃቸው የአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) የኮንቲኔንታል ኢንስትራክተርነት ማዕረግ ለአሠልጣኝ አብርሃም መስጠቱን አስታውቋል፡፡ 

ካፍ ለኢንስትራክተር አብርሃም የሰጠው ይህ ማዕረግ ለቀጣዮቹ ሁለት ዓመት በሥራ ላይ እንደሚውል፣ ካፍ በማንኛውም ጊዜና ሰዓት ኢንስትራክተሩን ለአኅጉራዊ ሥልጠናዎች ጥሪ ሲያደርግላቸው የተለያዩ ኮርሶችን እንደሚሰጡ፣ ይሁንና ለጥሪው በወቅቱና በሰዓቱ መልስ መስጠት የማይችሉ ከሆነ ግን ዕድሉን ለሌላ ሙያተኛ አሳልፎ የሚሰጥ ስለመሆኑ ጭምር አስታውቋል፡፡ ሆቴልና ተመሳሳይ ወጪዎችን በሚመለከት በካፍ የሚሸፈን ይሆናል ማለቱ ተሰምቷል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

አወዛጋቢው የሕገ መንግሥት ማሻሻያ ጉዳይ

በኢትዮጵያ የሕገ መንግሥት ማሻሻል ጉዳይ ከፍተኛ የፖለቲካ ውዝግብ የሚቀሰቀስበት...

 መፍትሔ  ያላዘለው  የጎዳና  መደብሮችን  ማፍረስ

በአበበ ፍቅር ያለፉት ስድስት ዓመታት በርካቶች በግጭቶችና በመፈናቀሎች በከፍተኛ ሁኔታ...

የተናደው ከቀደምቱ አንዱ የነበረው የአዲስ አበባ ታሪካዊ ሕንፃ

ዳግማዊ አፄ ምኒልክ በ19ኛው ክፍለ ዘመን መገባደጃ መናገሻ ከተማቸውን...

የአከርካሪ አጥንት ሕክምናን ከፍ ያደረገው ‘ካይሮፕራክቲክ’

በአፍሪካ ከጀርባ ሕመም ጋር በተያያዘ በርካታ ሰዎች ለከፍተኛ የአካል...