Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊከአዋጅ ውጪ በመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ሠራተኞችን ወደ ውጭ ለመውሰድ ውይይት መደረጉ ተገቢ...

ከአዋጅ ውጪ በመግባቢያ ሰነድ ስምምነት ሠራተኞችን ወደ ውጭ ለመውሰድ ውይይት መደረጉ ተገቢ አለመሆኑ ተጠቆመ

ቀን:

አገሮች የሁለትዮሽ ስምምነት አድርገው በየፓርላማቸው ስምምነታቸውን ካፀደቁ በኋላ ወደ ውጭ አገሮች የሚሄዱ ሠራተኞች መሄድ እንደሚችሉ ተደንግጎ እያለ፣ አዋጅ ተጥሶ የመግባቢያ ሰነድ (Bilateral Agreement) ብቻ በመፈራረም ሠራተኞች እንዲሄዱ መፍቀድ የዜጎችን ደኅንነት የማያስጠብቅና ሕግንም አለማክበር መሆኑ ተገለጸ፡፡

የኢትዮጵያ የውጭ አገር ሥራ ሥምሪት አዋጅ ቁጥር 923/2008 አንቀጽ(12) ‹‹ሠራተኛን በውጭ አገር ለሥራ ማሰማራት የሚቻለው፣ በኢትዮጵያና በተቀባይ አገር መካከል የሁለትዮሽ (ባይላተራል አግሪመንት) ስምምነት ሲኖር ብቻ ነው፤›› ቢልም፣ የመግባቢያ ሰነድ በመፈራረም ብቻ በተለይ የቤት ሠራተኞች እየተላኩ ነው፡፡

ሪፖርተር ያገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ቀደም ባሉት ወራት አዋጁ ከሚፈቅደው ውጪ፣ የመግባቢያ ሰነድ ብቻ በመፈራረም በተለይ የቤት ሠራተኞች ወደ ጆርዳንና ኳታር እየተላኩ ነው፡፡ ማክሰኞ ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. የተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ መንግሥት ተወካዮች ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር ስለሠራተኞች ለመነጋገር ወደ ኢትዮጵያ ገብተዋል፡፡ ተወካዮቹ ከሠራተኛና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር ሠራተኞችን በሚመለከት መንግሥት ለመንግሥት ስለሚኖረው ግንኙነት፣ የሠራተኞች መነሻ ደመወዝ ስንት መሆን እንዳለበትና ወደ ተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ የሚሄዱ ሠራተኞች ሊኖራቸው ስለሚገባ ችሎታ ውይይት በማድረግ የመግባቢያ ሰነድ እንደሚፈራረሙም ተጠቁሟል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

ከመንግሥት ተወካዮች ጋር ሠራተኞችን የሚቀጥሩ ኩባንያዎች፣ የቤት ሠራተኞችን አቅራቢ ኩባንያዎችና ከፍተኛ ሥልጠና ያላቸውንና መካከለኛ ሥልጠና ያላቸውን ሠራተኞች የሚቀጥሩ ኩባንያዎች ወደ ኢትዮጵያ መግባታቸውም ታውቋል፡፡

ኩባንያዎቹ ከአገር ውስጥ የውጭ አገር ሥራና ሠራተኛ አገናኝ ኤጀንሲዎች ጋር ረቡዕ ነሐሴ 22 ቀን 2011 ዓ.ም. በሸራተን አዲስ ሆቴል ውይይት ያደርጋሉ፡፡ ኩባንያዎቹ የቤት ሠራተኞችን፣ ሾፌሮችን፣ ከፍተኛ ችሎታ ያላቸውንና መካከለኛ ችሎታ ያላቸውን በርካታ ሠራተኞች እንደሚፈልጉም ተነግሯል፡፡

ቀደም ብሎ የቤት ሠራተኞችን ለመውሰድ ስምምነት ላይ የደረሱት ሳዑዲ ዓረቢያ 1,000 ሪያል፣ ጆርዳን 240 ዶላር (መካከለኛ ልምድ ላላቸው) እና 250 ዶላር (ከፍተኛ ልምድ ላላቸው)፣ እንዲሁም ኩዌት ደግሞ 340 ዶላር በመነሻ ደመወዝ ድርድር ከመደረጉ አንፃር፣ ከተባበሩት ዓረብ ኤምሬትስ ጋር የተሻለ መነሻ ደመወዝ ላይ ድርድር ይደረጋል ተብሎ እንደሚጠበቅም ተጠቁሟል፡፡  

ነገር ግን ወደ ኳታርና ሳዑዲ ዓረቢያ ሠራተኞች እንዲሄዱ የተፈቀደ ቢሆንም፣ ባለፉት ስድስትና ሰባት ወራት ውስጥ የሄዱት ሠራተኞች ከ450 እንደማይበልጡ ተገልጿል፡፡ ምክንያቱ ደግሞ ወደ ዓረብ አገሮች ሠራተኞችን የሚልኩ የአገር ውስጥ ኤጀንሲዎች በኢትዮጵያ ከሚገኙ ኤምባሲዎች የመውጫና የመግቢያ ፈቃድ ማግኘት እንደሚችሉ በአዋጅ የተደነገገውን፣ ኤምባሲዎች ተግባራዊ ባለማድረጋቸውና በመከልከላቸው 300 የሚሆኑ ኤጀንሲዎች ተመዝግበው እየተጠባበቁ እንደሆነም ተገልጿል፡፡

ሌላው ችግር ደግሞ በሕገወጥ መንገድ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ገብተው ለረጅም ዓመታት ያገለገሉ ሠራተኞች፣ ወደ አገራቸው በሕጋዊ መንገድ እንደሚመለሱ የተገባላቸው ቃል አለመጠበቁ መሆኑም ተጠቁሟል፡፡ ይህ የሆነው ደግሞ አዋጅ ቁጥር 923/2008 አንድ የቤት ሠራተኛ ወደ ውጭ አገር ለመሄድ ስምንተኛ ክፍል ማጠናቀቅ እንዳለባት ስለተደነገገ ሠራተኞቹ ምንም እንኳን ባህሉን፣ ቋንቋውንና አገሩን በደንብ ቢታወቁም አዋጁ ስለከለከላቸው ሕገወጥ መንገድን በመምረጣቸው ነው፡፡ እንዲሁም ችግሩን ለመፍታት የመንግሥት ቁርጠኝነት በማነሱና ሥራውን በአግባቡ መምራት ባለመቻሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡ መንግሥት በተለይ ቆይተው በተመለሱ ሠራተኞች ላይ አፋጣኝ ምላሽ ካልሰጠ፣ ሕገወጥ ዝውውሩ ሊባባስ ይችላል የሚል ሥጋት መኖሩም ተገልጿል፡፡

ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም. ኢትዮጵያ የገቡት የኤምሬትስ ልዑካን ጳውሎስ ሚሊየም ሜዲካል ኮሌጅን (ከሐኪሞች አንፃር)፣ የቴክኒክ ሥልጠናን በተመለከተ ጀኔራል ዊንጌት ማሠልጠኛ ትምህርት ቤትና ወሰን ግሮሰሪ አካባቢ የሚገኘውን ኢትዮ ቻይና ፖሊ ቴክኒክ ትምህርት ቤት፣ የምግብ ዝግጅትና ቱሪዝም ማሠልጠኛ ሴንተር፣ ቃሊቲ የሾፌሮችና መካኒኮች ማሠልጠኛ ማዕከልንና ሌሎችንም ተቋማት እንደሚጎበኙ ታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...