Friday, December 8, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምእንደ አማዞን ያልተጮኸለት የአንጎላና ኮንጎ የደን እሳት

እንደ አማዞን ያልተጮኸለት የአንጎላና ኮንጎ የደን እሳት

ቀን:

ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ብዙውን ትኩረት የሰጡት በብራዚል ለሚገኘው የአማዞን ደን ሰደድ እሳት ቢሆንም፣ በአማዞን የተከሰተው ሰደድ እሳት በአንጎላም ሆነ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከተከሰተው የደን ሰደድ እሳት እንደማይበልጥ የናሳ መረጃ አመልክቷል፡፡

አልጀዚራና ቢቢሲ እንደዘገቡትም፣ በማዕከላዊ አፍሪካ በሚገኙት በሁለቱ አገሮች ደኖች የተከሰተው እሳት በአማዞን ከተከሰተው በሦስት እጥፍ ያየለ ነው፡፡

በቅርቡ በአማዞንም ሆነ በማዕከላዊ አፍሪካ ደኖች ላይ የተነሳው ሰደድ እሳት መጠን ሲታይ ከአንጎላና ከኮንጎ በመቀጠል የብራዚሉ አማዞን በሦስተኛ ደረጃ ሲገኝ ከብራዚል በመለጠቅ የዛምቢያ የደን ሰደድ እሳት አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል፡፡ የብራዚል ጎረቤት ቦሊቪያ ደግሞ ስድስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል፡፡ የፖለቲካ ሚዛኑ ያደላውና የመገናኛ ብዙኃንን የላቀ ዘገባ ያገኘው ግን የአማዞኑ ነው፡፡

ትላንት የተለቀቀውና መረጃው ከመለቀቁ በፊት በነበሩ 48 ሰዓታት ውስጥ የተከሰተውን ሰደድ እሳት አስመልክቶ ሁለት ሳተላይቶችን በመጠቀም የምድር የአየር ንብረት መረጃን የሚለቀው ሞዲስ (ኤምኦዲአይኤስ) እንዳስታወቀው፣ በአንጎላ 6,902፣ በዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ከንጎ 3,395 እንዲሁም በብራዚል 2,127 ሥፍራዎች ላይ የደን እሳቶች ተከስተዋል፡፡

በማዕከላዊ አፍሪካ ደን የተከሰተው ሰደድ እሳት፣ በብራዚል አማዞን ቀይ መቀነስ ሠርቶ እንደሚንቦገቦገው እሳት ሁሉ ከጋቦን አንጎላ ድረስ ቀይ ሰንሰለት ሠርቶ ይታያል ሲል የናሳ ሳተላይት ምስልን ጠቅሶ ፍራንስ 24 ዘግቧል፡፡

እንደ አማዞን ያልተጮኸለት የአንጎላና ኮንጎ የደን እሳት

 

የቡድን ሰባት አገሮች ስብሰባ ሲካሄድ የፈረንሳዩ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ያደረጉትን ትዊት ጠቅሶ አጃንስ ፍራንስ ፕሬስ እንዳሰፈረው፣ በብራዚል አማዞን የተከሰተውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት አባል አገሮቹ የሚያደርጉትን ጥረት ያህል ለመካከለኛው አፍሪካ ለማድረግ ተጀምሯል፡፡ ሆኖም አገራቱን ከትችት አልታደገም፡፡

የቡድን ሰባት አገሮች በአማዞን የተነሳውን ሰደድ እሳት ለማጥፋት ለሚሰማሩ የእሳት አደጋ አውሮፕላኖች ብቻ 20 ሚሊዮን ዶላር ለመስጠት ቃል ቢገቡም፣ የብራዚል ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ኦንዚ ሎሬንዞኒ ብራዚል እገዛውን እንደማትፈልግ ገልጸዋል፡፡ ‹‹እናመሰግናለን፣ ይህ ሀብት ምናልባትም አውሮፓን በደን ለመሸፈን በጣም አስፈላጊ ሊሆን ይችላል›› በማለትም፣ ዕርዳታውን እንደማይፈልጉ አሳውቀዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ማክሮን የማዕከላዊ አፍሪካን ደን ሰደድ እሳት ለመታደግ እንመክርበታለን ቢሉም፣ በዚህ ስፍራ በየዓመቱ ወቅት እየጠበቀ የሚከሰተውን ሰደድ እሳት በአንድ ጊዜ እገዛ ማቆም እንደማይቻል፣ ይልቁንም ከግብርና ሥራ ጋር ተያይዞ የሚከሰት በመሆኑ ዘላቂ መፍትሔ ላይ ማተኮር እንደሚገባ አስተያየት ተሰጥቷል፡፡

በኮንጎ ሸለቆ የሚገኘው ጥቅጥቅ ደን ከአማዞን ቀጥሎ በዓለም ‹‹ሁለተኛው አረንጓዴ ሳምባ›› እየተባለ የሚጠራ ሲሆን፣ ኮንጎን፣ ጋቦንን፣ ካሜሩንንና ማዕከላዊ አፍሪካን አጠቃሎም 3.3 ሚሊዮን ስኩዌር ኪሎ ሜትርም ይሸፍናል፡፡

በርካታ ኤክስፐርቶችም እንደ አማዞን ሁሉ ካርቦንዳይ ኦክሳይድ ለመምጠጥም ሆነ ሊጠፉ የተቃረቡ እንስሳትን ጠብቆ ለማቆየት ቁልፍ ደን ነው ይሉታል፡፡

ፍራንስ 24 እንደሚለው፣ የኮንኮ ደን ቃጠሎ ከአማዞን ሲነጻጸር ዝቅተኛ የመገናኛ ብዙኃን ሽፋን ቢያገኝም፣ ከፍተኛ አደጋ የተጋረጠበት ነው፡፡

የአማዞን ደን የነደደው በድርቅና በአየር ንብረት ለውጥ ምክንያት ሲሆን፣ የማዕከላዊ አፍሪካው ግን በግብርና ቴክኒክ ክህሎት ማጣት ምክንያት ነው፡፡

በአማዞን ዝናብ ገብ ደን ሰደድ እሳት ከተነሳ ሦስት ሳምንታት አስቆጥሯል፡፡ የደኑ እ.ኤ.አ. በ2013 ከተከሰተው ሰደድ እሳት ብዛትም፣ የ2019ኙ ሪከርድ የያዘ ነው፡፡ ብራዚል በአካባቢው በሚከሰት ሰደድ እሳት ምክንያት በተያዘው ወር መጀመርያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ስታውጅ፣ 2019 ከገባም 80 ሺሕ ያህል እሳት የተነሳባቸው ሥፍራዎች መኖራቸውን የአገሪቱ የጥናት ማዕከል መጥቷል፡፡

የአማዞን ደን እርጥበታማ ቢሆንም ለእሳት ተጋላጭነቱ እየጨመረ ነው፡፡ ለዚህም ምክንያቱ ለእርሻ ሥራ መሬት ለማፅዳት ተብሎ የሚለቀቅ እሳት ነው፡፡ የዓለም ሳምባ የሚባለውና ከሦስት ሚሊዮን በላይ የአካባቢው ተወላጆች በሚኖሩበት አማዞን፣ እስካለፈው ሐሙስ ድረስ 2,500 ቦታዎች ላይ እሳት እየነደደ እንደነበር ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...