Friday, December 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ኪንና ባህልፈተና የበዛበት የአውታር መተግበሪያ

ፈተና የበዛበት የአውታር መተግበሪያ

ቀን:

በሔለን ተስፋዬ

ጥቅምት 29 ቀን 2009 ዓ.ም. የአውታር መተግበሪያ (Application) በሸራተን ሆቴል ለሕዝብ ይፋ የሆነበት ጊዜ ነው፡፡ ይሁን እንጂ መተግበሪያው ወደ ሥራ ሳይገባ ሦስት ዓመታት ቆይቷል፡፡

መተግበሪያው ብዙ ጥቅሞች ከማስገኘቱም አኳያ ለሙዚቀኞች፣ ለአቀናባሪዎችና ለግጥም ዜማ ደራሲያን ከቅጂ (copy) አደጋ ይታደጋል ተብሎ ታምኖም ነበር፡፡

መተግበሪያው ለብዙ የሙዚቃ ባለሙያዎችም ተስፋ የሰጠ እንደነበርም የሚታወስ ነው፡፡ በተለይ ደግሞ በአሁን ወቅት በስፋት ከተለመዱ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ጋር ተመሳሳይነት ስላለው በኢንዱስትሪው ላይ የጎላ ተፅዕኖ እንደሚኖረውም ተጠብቆ ነበር፡፡

መተግበሪያው አንድ አልበም በ15 ብር፣  ነጠላ ዜማ ከሆነ ደግሞ በአራት ብር ከሃምሳ ሳንቲም እንዲሸጥበትም ተደርጎ ነበር የተሠራው፡፡

በአንድሮይድ ስልኮች ላይ የሚሠራው አውታር ከስልክ ቀሪ ሒሳብ ላይ የሚቆረጥ የክፍያ ሥርዓት ተበጅቶለታል፡፡

በአውታር መተግበራያ ውስጥ ገብተው ሙዚቃን ከሸመቱ በቀጥታ ተጠቃሚ የሚሆኑት ድምፃዊው፣ አቀናባሪው፣ የዜማና የግጥም ደራሲው ሳውንድ ሪከርድ ፕሮውዲሰሩ ናቸው፡፡ በአጠቃላይ አምስት አካላት የሚገኘውን ገቢ እኩል ይከፋፈላሉ፡፡

ሙዚቃን ለማድመጥ ከሲዲ ማጫወቻ ጋር መታገልን የቀረፈው የአውታር መተግበሪያ፣ ከዚህ ቀደም በሙዚቃ ኢንዱስትሪ ውስጥ የነበረውን ዙሪያ ጥምጥም የመገበያያ ሥርዓት በዚህ መልኩ በቀልጣፋ አሠራር የሚቀያየር መሆኑም ተነግሮለታል፡፡

ኦንላይን መገበያያ መተግበሪያዎችን መጠቀም ከጊዜም፣ ከገንዘብም አኳያ ጥሩ የሚባልበት ደረጃ ላይ ደርሷል የሚለው የሙዚቃ አቀናባሪውና ከአውታር መሥራቾቹ የሆነው ኤልያስ መልካ ነው፡፡ የሙዚቃ አልበሞችን ከአሳታሚዎች በሚገዛበት ገንዘብ ቢያንስ ሦስት አልበሞችን ከአውታር መግዛት እንደሚቻል ይገልጻል፡፡

አጠቃቀሙን በተመለከተ እያንዳንዱ ተጠቃሚ ልክ ፌስቡክ አካውንት እንደሚከፍት ሁሉ የአውታር መተግበሪያ ኦን ላይን በመግባት በማውረድ አካውንት በመክፈት መገልገል ይቻላል፡፡

የአውታር መሥራቹ እንደተናገረው፣ መተግበሪያው እንዳሰቡት ቀላል ባለመሆኑ እስካሁን በአግባቡ ተግባራዊ ማድረግ አለመቻሉን ገልጾ፣ መተግበሪያው ቀስ በቀስ ወደ መስተካከል ደረጃ ለማድረስ ጥረት ላይ ነን ብሏል፡፡

አውታር እየተንገዳገደ ይነሳል የሚል ተስፋ አለን ያለው አቶ ኤልያስ፣ በዚህ መተግበሪያ እስካሁን በሺሕዎች የሚቆጠሩ ደንበኞችን ማፍራት መቻሉን አስረድቷል፡፡

የአውታር መተግበሪያ ይፋ የተደረገ ሰሞን የተወሰኑ ደንበኞች አገልግሎቱ እስከተቋረጠበት ጊዜ ድረስ መገልገል ችለው ነበር፡፡ ‹‹ከአንዳንድ ደንበኞች መተግበሪያውን አንድ ጊዜ ብቻ ሞክረው ብር ሲቆረጥባቸው ድጋሚ መክፈት ስለሚፈሩ ብሩ የተበላ ይመስላቸዋል፤›› የሚለው ኤልያስ፣ ደግመው ቢሞክሩም አንድ ጊዜ ብር ከቆረጠባቸው ደግሞ ሌላ ገንዘብ እንደማይወስድ አስረድቷል፡፡

‹‹ከመተግበሪያው ካለመናበብ ምክንያት ለመሥራቹና ለደንበኞች ትንሽ ግራ የሚያጋባ ሁኔታ ተፈጥሯል ያለው መሥራቹ፣ በቅርብ ጊዜ ውስጥ ይኼን ችግር ለመቅረፍ ቡድን ተዋቅሮ ወደ ሥራ መግባቱን አመልክቷል፡፡

‹‹አውታር በዚህ ሦስት ዓመታት ውስጥ የድሮ ሙዚቃዎችን በማሰባሰብ፣ ወደ መተግበሪያው ለማስገባት፣ ከዚያም ወደ ዲጂታል ለመቀየር፣ መተግበሪያውን ለማዳበርና ለማሳደግ  እየሠራን ነው፤›› ብሏል፡፡

መተግበሪያው የሚሠራው ለጊዜው በአንድሮይድ ስልኮች ሲሆን፣ በቀጣይ በሌሎች የስልክ ዓይነቶች ተግባራዊ እንደሚሆንም ታውቋል፡፡

አንዳንድ ጊዜ ሰዎች መተግበሪያው አስቸገረኝ ይላሉ፣ አንዳንዴ ደግሞ ለጓደኛዬ ልልክ ብዬ አስቸገረኝ የሚሉ አልታጡም የሚለው መሥራቹ፣ እንደማንኛውም መተግበሪያ በየጊዜው መሻሻል (አፕዴት) መደረግ አለበት ይላል፡፡ ከአውታር መተግበሪያ የተሸመቱ ሙዚቃዎች ማዳመጥ የሚችለው ገዥው ብቻ እንጂ ሙዚቃን ከአንዱ ወደ ሌላው በመላላክ እንደማይቻል ይናገራል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመቃወም ነፃነት ውዝግብ በኢትዮጵያ

ስሟ እንዳይገለጽ የጠየቀችው በአዲስ አበባ ከተማ በተለምዶ የሾላ አካባቢ...

የሲሚንቶን እጥረትና ችግር ታሪክ ለማድረግ የተጀመረው አጓጊ ጥረት

በኢትዮጵያ በገበያ ውስጥ ለዓመታት ከፍተኛ ተግዳሮት በመሆን ከሚጠቀሱ ምርቶች...

የብሔር ፖለቲካው ጡዘት የእርስ በርስ ግጭት እንዳያባብስ ጥንቃቄ ይደረግ

በያሲን ባህሩ በሪፖርተር የኅዳር 9 ቀን 2016 ዓ.ም. ዕትም “እኔ...