Wednesday, December 6, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበሐዋሳ ከተማ ጥቃት ተሳትፈዋል የተባሉ 68 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ እየተጣራ ነው

በሐዋሳ ከተማ ጥቃት ተሳትፈዋል የተባሉ 68 ተጠርጣሪዎች ጉዳይ እየተጣራ ነው

ቀን:

ምርጫ ቦርድ የሲዳማን ሕዝበ ውሳኔ ለማካሄድ ከ75 ሚሊዮን ብር በላይ ያስፈልገዋል

ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በደቡብ ክልል በሐዋሳ ከተማ ተፈጽሞ በነበረ ጥቃት ተሳታፊ ናቸው የተባሉ 68 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለው ማጣራት እየተደረገ መሆኑን፣ የከተማው ኮማንድ ፖስት ኃላፊ ኮሎኔል ተክለ ብርሃን ገብረ መድን ገለጹ፡፡

በደረሰው ጥቃት የሦስት ሰዎች ሕይወት ማለፉንና በቤቶችና ንብረት ላይ መጠነኛ ጉዳት መድረሱን የገለጹት ኮሎኔሉ፣ በቁጥጥር ሥር የዋሉት ተጠርጣሪዎች በወቅቱ ግርግር ሲፈጥሩ የተገኙ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ በቁጥጥር ሥር የዋሉትን ተጠርጣሪዎችን ጉዳይም በክልሉ ፍርድ ቤተ እየታየ እንደሆነም ጨምረው ገልጸዋል፡፡

ጥቃቱ በተከሰተ በማግሥቱ የክልሉ መንግሥት ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን፣ ጥያቄው በቀረበ በሰባት ቀን ውስጥ ከተማዋ በኮማንድ ፖስቱ ጥበቃ ሥር እንደዋለችና በአሁኑ ጊዜ በአስተማማኝ ሰላም ላይ እንደምትገኝ ኃላፊው አስረድተዋል፡፡ ከተማዋ ወደ ነበረችበት ሁኔታ እንድትመለስ የነዋሪዎች ድጋፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንደነበረው፣ ተጠርጣሪዎችን በማጋለጥ ረገድም የጎላ ተሳትፎ እንደነበራቸው፣ ከኮማንድ ፖስቱ ጎን ለጎንም ጥበቃ እንደሚወጡ አስታውቀዋል፡፡

‹‹በየክፍለ ከተማውና በየቀበሌው ኮማንድ ፖስት ተዋቅሯል፡፡ ዓላማውም የከተማውን ሰላም ማረጋገጥ ነው፡፡ ይኼንን ለማድረግም ለክልሉ የፀጥታ አካል እንደ አጋዥ ሆኖ ነው ኮማንድ ፖስቱ የሚሠራው፤›› ያሉት ኃላፊው ከነዋሪዎችና ከሌሎች ባለድርሻዎች ጋር ተባብሮ መሥራት በመቻሉ ዓላማውን ከሞላ ጎደል ማሳካት መቻሉን አብራርተዋል፡፡ ‹‹ኮማንድ ፖስቱ ቢኖርም ባይኖርም ከተማዋ በአስተማማኝ ሰላም ውስጥ ትገኛለች፡፡ ኮማንድ ፖስቱ ዛሬ ይውጣ ቢባል ይወጣል፤›› ብለዋል፡፡

እንደ ኮሎኔል ተክለ ብርሃን ገለጻ፣ በሐዋሳ ዙሪያ በሚገኙ ገጠራማ አካባቢዎችም ተመሳሳይ ሰላም ሰፍኗል፡፡ በቤትና በንብረት ላይ የደረሱ አደጋዎችንም እርስ በርስ በመተባበር የመተካት ሥራ እየተከናወነ ነው፡፡

የሐዋሳ ከተማ የፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት መምርያ ምክትል ከንቲባ አቶ ገለታ ገረመው፣ ሐምሌ 11 ቀን 2011 ዓ.ም. በከተማዋ ያጋጠመው ችግር የከተማዋን ነዋሪዎች እንደማይወክል ሐሙስ ነሐሴ 23 ቀን 2011 ዓ.ም. በጽሕፈት ቤታቸው በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል፡፡ የጥቃቱ ሰለባ የሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች  እንዲካሱ ለማመቻቸትም እየተሠራ ነው ብለዋል፡፡ የወደመ ንብረት ይተካል፣ የጠፋ ንብረትም እንዲመለስ ይደረጋል ሲሉ ተደምጠዋል፡፡

ከሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ጋር ተያይዞ በከተማዋ ነዋሪዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት በሰዎች ሕይወትና ንብረት ላይ ጥፋት ከማስከተሉ ባሻገር የቱሪዝም ፍሰቱ በከፍተኛ መጠን እንዲቀንስ ማድረጉ ተገልጿል፡፡ ‹‹በሕገ መንግሥቱ መሠረት የቀረበው የሲዳማ የክልልነት ጥያቄ ተገቢውን መልስ በወቅቱ ባለማግኘቱ የተፈጠረ ችግር ነው፤›› ሲሉ ምክልት ከንቲባው አስረድተዋል፡፡

ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የሲዳማ ዞን ሕዝበ ውሳኔ የሚደረግበትን ቀን ይፋ አድርጓል፡፡ ቦርዱ ሐሙስ ነሐሴ 23 ቀን ባወጣው መግለጫ መሠረት ኅዳር 3 ቀን 2012 ዓ.ም. የሕዝበ ውሳኔ መስጫ ቀን ይሆናል፡፡ ቦርዱ ለደቡብ ክልል ምክር ቤት በላከውና ለሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ባሳወቀው መሠረት፣ ሕዝበ ውሳኔውን ለማከናወን የሚረዱ ባለ አምስት ነጥብ ውሳኔዎች የሥራ መዘርዝሮችንና አስፈላጊውን በጀት አስታውቋል፡፡ ሕዝበ ውሳኔውን ለማስፈጸም 75,615,015 ብር በጀት የክልሉ ምክር ቤት ወደ ምርጫ ቦርድ አካውንት ማስተላለፍ እንዳለበት አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ታዋቂው የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አይቴል የስትራቴጂ ለውጥ አካል የሆነውን አዲስ አርማ እና መለዮ ይፋ አደረገ።

በአለማችን ታዋቂ ከሆኑት የኤሌክትሮኒክስ ብራንዶች መካከል አንዱ የሆነው እና...

የጠቅላላ ጉባኤ ስብሰባ ጥሪ ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ

ለሸገር አነስተኛ የፋይናንስ ተቋም አ.ማ ባለአክሲዮኖች በሙሉ የሸገር አነስተኛ የፋይናንስ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ጸሐፊ፣ የሌላ ሚኒስትር ጸሐፊ ከሆነችው የቅርብ ወዳጇ ጋር በስልክ እየተጨዋወቱ ነው]

አንቺ ግን ምን ሆነሽ ነው? ጠፋሁ አይደል? ጠፋሁ ብቻ?! ምን ላድርግ ብለሽ...

በሱዳን ላይ ያጠላው የመከፋፈል ዕጣና ቀጣናዊ ተፅዕኖው

የሱዳን ጦርነት ስምንተኛ ወሩን እያገባደደ ይገኛል፡፡ ጄኔራል አብዱልፈታህ አልቡርሃን...