Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርት‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› በሞሮኮ ራባት

‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› በሞሮኮ ራባት

ቀን:

በሰሜን አፍሪካዊቷ ሞሮኮ በተለያዩ ከተሞች ለሁለት ሳምንት ያህል ሲከናወን የሰነበተው 12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች ባለፈው ዓርብ ነሐሴ 24 ቀን 2011 .. ፍጻሜውን አግኝቷል፡፡ በአትሌቲክሱ ባላት ጥንካሬ ብዙዎች ‹‹የሯጮች ምድር›› ሲሉ የሚጠሯት ኢትዮጵያ በመስኩ ዛሬም መሸነፍን የሚጠየፉ የልባም ወጣቶች በረከት ባለቤት መሆኗ ዕውን ሆኗል፡፡ ‹‹አረንጓው ጎርፍ›› ገድል በሞሮኮ ራባት ተደግሟል፡፡

በፈርኦኖቹ ግብጻውያን የበላይነት በተጠናቀቀው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች 53 የአኅጉሪቱ አገሮች ተሳትፈዋል፡፡ በአትሌቲክሱ 42 ወንዶችና 40 ሴቶች በድምሩ 82 አትሌቶችን ያሳተፈችው ኢትዮጵያ 10,000 እና 21 ኪሎ ሜትር ግማሽ ማራቶን ሴቶች ያስመዘገበችው ውጤት ቀደምቱን በተለይም ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› በሚል ዓለም የተደመመባቸውን ጀግኖች ያስታወሰ ውጤት አስመዝግባለች፡፡

ኢትዮጵያ በአትሌቲክሱ ከአበበ ቢቂላ የባዶ እግር ገድል ጀምሮ ማሞ ወልዴ፣ ምሩጽ ይፍጠር፣ ኃይሌና ደራርቱ እያለ በትውልድ ቅብብሎሽ ዛሬም ታሪክ መሥራቱን ቀጥላበታለች፡፡ ልክ እንደ ቀደሙ ሁሉ ወደ ሞሮኮ ያቀናው የአትሌቲክስ ቡድኗ፣ ኢትዮጵያውያን በአንድ ልብና በአንድ ሰንደቅ በአፍሪካውያን ወንድሞቻቸው ፊት አይበገሬነታቸው እንዲጎላ አድርጓል፡፡

ሐሙስ ነሐሴ 23 እና ዓርብ ነሐሴ 24 ቀን 2011 .. በተደረገው በሴቶች አሥር ሺሕ እና 21 ኪሎ ሜትር ግማሽ ማራቶን፣ ከኢትዮጵያውያኑ እንስቶች ውጪ ተፎካካሪ የሌለ እስኪመስል የሜዳሊያው ፉክክር እርስ በርስ ሆኖ ታይቷል፡፡ በሴቶች 10,000 ሜትር የርቀቱ አሸናፊና የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤቷ ፀሐይ ገመቹ ነበረች፣ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የወሰደባት ጊዜ 3156.92 ሆኗል፡፡ ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን ያጠናቀቁት ደግሞ ዘይነባ ይመር 3157.95 እና ደራ ዲዳ 3168.75 ሆኖ ተመዝግቧል፡፡ በወንዶች መካከል በተደረገው 10,000 ሜትር የሩጫ ውድድር ኢትዮጵያ በብርሃኑ ወንድሙ አማካይነት የወርቅ ሜዳሊያ ባለቤት መሆኗ የረዥም ርቀትና የኢትዮጵያውያን ቁርኝት ማረጋገጫ መሆኑ በግልፅ ታይቷል፡፡

12ኛው የመላ አፍሪካ ጨዋታዎች 13 የስፖርት ዓይነቶች የቀረበችው ኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያው አንድ ብላ የጀመረችው አዲስ አበባን ጨምሮ በኢትዮጵያ በሁሉም ከተሞች በታዳጊ ወጣቶች በስፋት እየተዘወተረ በሚገኘው ወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት መሆኑ ልብ ይሏል፡፡ ታሪኩ ግርማ 63 ኪሎ ግራም የወርቅ፣ እንስት ፀባኦት ጎሳየና ሰለሞን ቱፋ 53 እና 54 ኪሎ ግራም የነሐስ ሜዳሊያዎች መመዝገባቸው ይታወሳል፡፡ 

ምናልባትም በዚህ ስፖርት የተገኘው የወርቅ የነሐስ ሜዳሊያዎች፣ ኢትዮጵያውያን እግር ኳስን ጨምሮ በሌሎችም ስፖርቶች ተጠያቂነትና ግልጽነት እንዲሁም እንደየ ስፖርቶቹ ባህሪይ ግልፅ የሆነ የአሠራር ሥርዓት መዘረጋት ቢቻል ውጤታማ መሆን እንደሚቻል ማረጋገጫ ስለመሆኑ ጭምር የሚናገሩ ሙያተኞች አልጠፉም፡፡ ሌላውና ‹‹አረንጓዴው ጎርፍ›› መገለጫ ሆኖ የተመዘገበው በሴቶች 21 ኪሎ ሜትር የግማሽ ማራቶን ሩጫ ነው፡፡ በውድድሩ አሸናፊ በመሆን የወርቅ ሜዳሊያውን ከፍ ያደረገችው ያለምዘርፍ የኋላወርቅ ስትሆን፣ ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን ተከታትለው በመግባት የብርና የነሐስ ሜዳሊያ ያስመዘገቡት ደጊቱ አዝመራውና መሠረት በለጠ ናቸው፡፡ 

ኢትዮጵያውያን እንስቶች በደመቁበት የዘንድሮ መላ አፍሪካ ጨዋታዎች 800 ሜትር ሒሩት መሸሻ ወርቅ፣ 3,000 ሜትር መሰናክል መቅደስ አበበና ወይንሸት አንሳ የወርቅና የነሐስ፣ 5000 ሜትር ሐዊ ፈይሳና ዓለሚቱ ታሪኩ የብርና የነሐስ ሜዳሊያዎች ሲያስመዘገቡ፣ በወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ጌታነህ ወሌ አማካይነት ቀደም ሲል የተመዘገቡት የብር ሜዳሊያ ውጤቶች ናቸው፡፡
ዓርብ ምሽት በተደረገው የወንዶች 5000 ሜትር ፍጻሜ ኬንያውያኑ ተከታትለው በመግባት ወርቅ ብርና ነሐሱን አጥልቀዋል። ኢትዮጵያውያኑ አቤ ጋሻሁን ጥላሁን
4ኛ፣ አንተን አየሁ ዳኛቸው ይስማ 6 እና ገመቹ ዲዳ ድሪባ
10 ሆነው አጠናቀዋል። በሴቶች 1500 ሜትር ኬንያ ወርቅና ብርን ስታገኝ ኢትዮጵያ በዓይናለም እሸቱ አማካይነት ነሐስን አጥልቃለች።

ይህ ዘገባ እስከ ተጠናቀረበት ዓርብ ምሽት ድረስ ኢትዮጵያ በስድስት የወርቅ፣ በአምስት የብርና በ11 የነሐስ ሜዳሊያ ከአፍሪካ ዘጠነኛ ስትሆን በአትሌቲክስ ደግሞ አምስት የወርቅና አምስት የብር፣ ዘጠኝ የነሐስ ሜዳሊያዎች በማግኘት ሁለተኛ ሆናለች፡፡ ኢትዮጵያ ተጨማሪ የወርቅ ሜዳሊያ የምታስመዘግብበት የአምስት ሺሕ ሜትር የወንዶች ውድድር ይጠበቅ ነበር፡፡ ውድድሩን ግብፅ በበላይነት ያጠናቀቀችው 93 ወርቅ፣ 94 ብር፣ 67 ነሐስ በድምሩ 254 በማግኘት ነው።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...