Monday, May 29, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፊፋና ካፍ ለወልዲያ ስታዲየም ዕውቅና እንዲሰጡ እንቅስቃሴ ተጀመረ

ፊፋና ካፍ ለወልዲያ ስታዲየም ዕውቅና እንዲሰጡ እንቅስቃሴ ተጀመረ

ቀን:

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በሼሕ መሐመድ ሁሴን ዓሊ አልአሙዲ ሙሉ ወጪ የተገነባው የወልዲያ ስታዲየምና የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከል በዓለም አቀፍ እግር ኳስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (ፊፋ) እና በአፍሪካ እግር ኳስ ኮንፌዴሬሽን (ካፍ) ዕውቅና እንዲያገኝ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ታወቀ፡፡ ዓለም አቀፍ ስታንዳርዱን በጠበቀ መልኩ ተገንብቶ አገልግሎት በመስጠት ላይ የሚገኘው የወልዲያ ስታዲየም፣ ከተማዋ ማሟላት የሚገባትን መሠረተ ልማት አላሟላችም በሚል በፊፋም ሆነ በካፍ ዕውቅና እንዳልተሰጣት ይነገራል።

ከግማሽ ቢሊዮን ብር በላይ የፈጀው የወልዲያ ስታዲየም ግንባታው ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ቢሆንም፣ እስካሁን በፊፋም ሆነ በካፍ ዕውቅና ሳያገኝ መቆየቱ ብዙዎችን ሲያነጋግር ቆይቷል፡፡ በኢትዮጵያ በተለይም በባህር ዳር፣ በመቐለና በሐዋሳ ከተሞች የተገነቡት ዘመናዊ ስታዲየሞች ዝቅተኛውን የፊፋና ካፍ ስታንዳርድ አያሟሉም በሚል የአዲስ አበባ ስታዲየምን ጨምሮ ማንናቸውንም ዓለም አቀፋዊና አኅጉራዊ ውድድሮችን እንዳያስተናግዱ ዕገዳ ማስተላለፉ ይታወቃል፡፡

በዚህ የተነሳ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አረጋ ይርዳው (/) ግንባታው ተጠናቆ ከሁለት ዓመት በፊት ለአገልግሎት የበቃው የወልዲያ ስታዲየም እያለ ፊፋና ካፍ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም ስለሌላት ብሔራዊ ቡድኗ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን በተመረጡ የጎረቤት አገር ስታዲየሞች የሚያከናውን እንደሚሆን መግለጹን ተከትሎ ለምን? የሚል ጥያቄ ማንሳታቸው ይታወሳል፡፡

ምክንያቱን አስመልክቶ ኃላፊው፣ በአገር በቀሉ ኩባንያ ሚድሮክ ኢትዮጵያ ቴክኖሎጂ ግሩፕ የተገነባው ዘመናዊ ስታዲየም ከእግር ኳስም ጎን ለጎን የዓለም አቀፍ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (አይኦሲ) እና የዓለም አቀፍ አትሌቲክስ ፌዴሬሽኖች ማኅበር (አይኤኤኤፍ) ስታንዳርድ ያሟላ ሲሆን፣ ስታዲየሙ 25 ሺሕ 155 ተመልካቾችን የማስተናገድ አቅም ሲኖረው፣ በተጨማሪም የሜዳ ቴኒስ፣ የቅርጫት ኳስ፣ የመረብ ኳስ፣ የእጅ ኳስና የውኃ ዋና ስፖርቶች የሚከናወኑባቸው ማዘውተሪያዎችን አሟልቶ የያዘ ስለመሆኑ ጭምር ሲናገሩ ተደምጠዋል፡፡ ለተመልካቾች ደረጃውን የጠበቀ የፀሐይ መከላከያ ጥላ የተገጠመለት መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

ይሁንና አስፈላጊው የማስተዋወቅ ሥራ ያልተሠራለት በመሆኑ፣ ስታዲየሙ በተለይም በአሁኑ ወቅት ዓለም አቀፍ ውድድሮችን እያስተናገደ እንዳልሆነ ያከሉት / አረጋ ብሔራዊ ፌዴሬሽኖች ዕድሉን ለመጠቀም አለመሞከራቸው እንዳሳዘናቸው ተናግረዋል፡፡ በካፍ ቅድመ ሁኔታ በተቀመጠላቸው የባህር ዳርንና የመቐለን ስታዲየሞችን ለጊዜው እንዲጠቀም የተፈቀደለት የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የወልዲያ ስታዲየም ዕውቅና እንዲያገኝ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑ ተሰምቷል፡፡ እንደ ሪፖርተር ምንጮች ከሆነ የብሔራዊ ፌዴሬሽኑ ፕሬዚዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ በካፍ የክለብ ላይሰንሲንግ ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተድላ ዳኛቸውን ያካተተ ቡድን በመያዝ ባለፈው ሐሙስ ነሐሴ 23 ቀን 2011 .. በወልዲያ ከተማ ተገኝተው ጉብኝት አድርገዋል፡፡

አቶ ኢሳያስና ልዑካናቸው በቆይታቸው ስታዲየሙ የሚገኝበትን ወቅታዊ ሁኔታ፣ የወልዲያ ከተማ መሠረተ ልማትና ሌሎች ተያያዥ ጉዳዮችን በቪዲዮ በማስቀረጽ ሙሉ መረጃውን ለካፍ ልከው ዕውቅና ለማሰጠት ዕቅድ ይዘዋል ተብሏል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመስቀል አደባባይ የመግቢያ ክፍያ ለምን?

ወጣቶች፣ ሕፃናትና አረጋውያን ሳይቀሩ መንፈሳቸውን የሚያድሱበት እንዲሁም ሐሳባቸውን በነፃነት...

በሕገ መንግሥቱ የተዋቀረው ‹‹የብሔር ፖለቲካ›› እና ‹‹ሥርዓቱ›› ያስከተለው መዘዝና መፍትሔው

(ክፍል አራት) በዓቢዩ ብርሌ (ጌራ) ባለፈው ጽሑፌ (በክፍል ሦስት) አሁን ያለው...

የኢትዮጵያ ኅብረተሰብና የመንግሥት መሪ ምሥል

በበቀለ ሹሜ በ2015 ዓ.ም. መጋቢት ወር ውስጥ ይመስለኛል በ‹ሸገር ካፌ›...

ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ ያደረገው አዋጅ የፍትሐዊነት ጥያቄ አስነሳ

በቀጣዮቹ ሁለት ዓመታት ስምንት ዩኒቨርሲቲዎችን ራስ ገዝ በማድረግ ተቋማዊና...