የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የዎላይታ ሕዝብ ላቀረበው ሕገ መንግሥታዊ የክልልነት ጥያቄ በአስቸኳይ ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ ይስጥ ሲል፣ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ጥያቄ አቀረበ፡፡
ፓርቲው ይህን ጥያቄ ያቀረበው ሰኞ ነሐሴ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ ዲአፍሪክ ሆቴል በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ነው፡፡
የዎላይታ በክልልነት ደረጃ መደራጀት ጥያቄ ማለት ‹‹ዎላይታ በህልውናው የመቀጠል ጥያቄ እንደሆነ›› የገለጹት የፓርቲው ኃላፊዎች፣ ነገር ግን ደኢሕዴንና የደቡብ ክልል መንግሥት ይህ ጥያቄ ተስተጓጉሎ እንዲቀር ለማድረግ እየሠሩ ነው በማለት ከሷል፡፡
ከዚህ በተጨማሪም የፓርቲው ኃላፊዎች በዎላይታና አካባቢው የታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳም ጠይቀዋል፡፡