Thursday, June 1, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናከፍተኛ ኢሰብዓዊ ድርጊት ይፈጸምበት የነበረው ማዕከላዊ ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት ሊደረግ ነው

ከፍተኛ ኢሰብዓዊ ድርጊት ይፈጸምበት የነበረው ማዕከላዊ ለሕዝብ ጉብኝት ክፍት ሊደረግ ነው

ቀን:

ከ40 ዓመታት በላይ በርካታ ዜጎች ባደረጉትም ይሁን አድርገውታል ተብሎ በተጠረጠሩበት ወንጀል ታፍነው ከተያዙ በኋላ፣ ታስረው ቶርች ይደረጉበት፣ ሕይወታቸው እስከሚያልፍ ድረስ ከፍተኛ ኢሰብዓዊ ድርጊት ሲፈጸምበት የነበረው የፌዴራል ወንጀል ምርመራ ማዕከል (ማዕከላዊ) ከጳጉሜን 1 እስከ 4 ቀን 2011 ዓ.ም. ድረስ ሕዝብ እንዲጎበኘው ክፍት ሊደረግ ነው፡፡

የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ ማክሰኞ ነሐሴ 28 ቀን 2011 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው መግለጫው እንዳሳወቀው፣ ከ40 በላይ ዓመታት ዜጎችን ለማሰርና ለማሰቃየት እስከ ሕይወት መጥፋት የደረሰ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ሲፈጸምበት የነበረውን ማዕከላዊ እስር ቤት በመዝጋት የለውጥ ብሥራት በተነገረበት ዕለት በሞት አፋፍ ላይና በሥቃይ ላይ ለነበሩ ብቻ ሳይሆን፣ በፍትሕ ሥርዓቱ አንፀባራቂ ለውጥ የተመዘገበበትና የሥቃይ ዘመን ዳግም ላይመለስ እንዲዘጋና ሙዚየም እንዲሆን መደረጉን አስታውሷል፡፡

ማዕከላዊ የምርመራ ቦታ የሰው ልጆች በሕይወት እያሉ ደምና ዕንባ የሚቀዳበት፣ ኅሊና የሚሰለብበት፣ ሞራል የሚኮላሽበት፣ አካል የሚጎድልበት አሰቃቂ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የሚፈጸምበት ቦታ መሆኑንም ገልጿል፡፡ ተጠርጥረው ማዕከላዊ ይታሰሩ የነበሩ ዜጎች ከማይሽር የሥነ ልቦና ቅጣት እስከ አካል ማጉደል የሚደርስ ሥቃይ ይደርስባቸው እንደነበርም አክሏል፡፡

አንድ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ሥር ውሎ ክስ እስከሚመሠረትበት ድረስ በሕይወት ምዕራፍ ውስጥ ገጥመውት የማያውቁ የሥቃይ ዓይነቶች፣ በሰው ልጅ ላይ ለመፈጸም ሳይሆን ለመስማት የሚከብዱ ኢሰብዓዊና ኢሞራላዊ ቅጣቶች በግፍ ሲፈጸምበት መኖሩንም አስታውሷል፡፡ ‹‹ይህን መሰል ድርጊቶች ዳግም እንዳመለሱ ከመቼውም ጊዜ በላይ ተግቶ መሥራት ይጠይቃል፤›› ብሏል፡፡

‹‹በአገራችንና በፍትሕ ሥርዓቱ ለነፈሰው መልካም የለውጥ አየር አድናቆት እየቸርንና ለለውጡ ቀጣይነት ማነቆ የሆኑ ተግዳሮቶችን እየተነጋገርን የሕግ የበላይነትን በማረጋገጥ፣ የሕዝብና በመንግሥት አመኔታ የተቸረው የፍትሕ ተቋም ለመገንባት የአገራችን ሰላም አስተማማኝና ዘላቂ ለማድረግ፣ የመልካም አስተዳደር ችግሮች እንዲፈቱና የተጀመረው የልማት፣ የሰላም፣ የዴሞክራሲና የመልካም አስተዳደር ሥርዓት ግንባታ እንዲጎለብት ዘርፈ ብዙ የሕግ ማሻሻያ ሥራዎች ተሠርተዋል፤›› ሲል በመግለጫው አመልክቷል፡፡

በአገር አቀፍ ደረጃ ‹‹ለሕግ ተገዥ ነኝ›› በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ባለው የፍትሕ ወር ያ ግፍ ይፈጸምበት የነበረው ‹‹ማዕከላዊ›› እስር ቤት ውስጥ፣ ኤግዚቢሺን ተከፍቶ ለአራት ቀናት በሕዝብ እንዲጎበኝ እንደሚደረግ የዓቃቤ ሕግ መግለጫ ያትታል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በአዲስ አበባ በድምቀት ተከበረ

የአዛርባጃን ኤምባሲ  የአዛርባጃንን ብሄራዊ ቀን በትላንትናው ዕለት አከበረ። ሰኞ...

የመንግሥትና የሃይማኖት ልዩነት መርህ በኢትዮጵያ

እንደ ኢትዮጵያ ባሉ አገሮች የሃይማኖት ተቋማት አዎንታዊ ሚና የጎላ...

ሐበሻ ቢራ ባለፈው በጀት ዓመት 310 ሚሊዮን ብር የተጣራ ትርፍ ማግኘቱን አስታወቀ

የአንድ አክሲዮን ሽያጭ ዋጋ 2,900 ብር እንዲሆን ተወስኗል የሐበሻ ቢራ...