Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናለዎላይታ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ

ለዎላይታ ሕዝብ የክልልነት ጥያቄ አስቸኳይ ምላሽ እንዲሰጥ ተጠየቀ

ቀን:

የደቡብ ኢትዮጵያ ብሔር ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት የዎላይታ ሕዝብ ላቀረበው ሕገ መንግሥታዊ የክልልነት ጥያቄ በአስቸኳይ ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ እንዲሰጠው፣ የዎላይታ ሕዝብ ዴሞክራሲዊ ግንባር (ዎሕዴግ) ጥያቄ አቀረበ፡፡

ፓርቲው ይህን ጥያቄ ያቀረበው ሰኞ ነሐሴ 27 ቀን 2011 ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ዲአፍሪክ ሆቴል ነው፡፡ ጥያቄውን ያቀረቡት የፓርቲው አመራሮች ደግሞ የፓርቲው ሊቀመንበር አቶ ተክሌ ቦረና፣ ምክትል ሊቀመንበሩ አስራት ኤልያስ (ዶ/ር)፣ እንዲሁም የፓርቲው የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ ፈለቀ ፈንታ ናቸው፡፡

ለደቡብ ክልል ምክር ቤት የዎላይታ ሕዝብ የክልል እንሁን ጥያቄ የቀረበው በታኅሳስ 12 ቀን 2011 ዓ.ም. መሆኑን ያስታወሱት የፓርቲው አመራሮች፣ የክልሉ ምክር ቤት ግን ለጥያቄያቸው ተገቢውን ትኩረትና ምላሽ ካለመስጠቱም በላይ፣ ‹‹ተስተጓጉሎ እንዲቀር እያደረጉ ናቸው፤›› በማለት የክልሉን ምክር ቤት ወቅሰዋል፡፡

የዎላይታ በክልልነት የመደራጀት ጥያቄ ማለት ዎላይታ በህልውናው የመቀጠል ጥያቄ መሆኑን የገለጹት የፓርቲው አመራሮች፣ ይሁን እንጂ የደቡብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች ዴሞክራሲዊ ንቅናቄ (ደኢሕዴን) እና የደቡብ ክልል መንግሥት ጥያቄው ተገቢውን ምላሽ እንዳያገኝ አስተጓጉለውታል ሲልም ገልጸዋል፡፡

‹‹የአንድን ሕዝብ በክልል ደረጃ ለመደራጀት ከጠየቀበት እስከ ማጠናቀቂያ ድረስ ደረጃ በደረጃ፣ ቅደም ተከተልን ጠብቀው መሥራት የሚገባቸው ሥራዎች ምን እንደሆኑ በሕገ መንግሥቱ ተደንግገው በግልጽ ተቀምጠዋል፡፡ ነገር ግን ደኢሕዴን የሕዝብን ጥያቄ ለማበላሸት ሲባል ብቻ ከሕገ መንግሥታዊ አካሄድ ውጪ የሆነውን ሲሠራ ይታያል፤›› በማለት የፓርቲው አመራሮች ቅሬታቸውን አቅርበዋል፡፡

በመሆኑም ለጥያቄው አስቸኳይ ሕገ መንግሥታዊ ምላሽ እንዲሰጥ ለክልሉ መንግሥትና ለደኢሕዴን ጥያቄውን ያቀረቡ ሲሆን፣ በክልል ደረጃ መደራጀትን በማስመልከት ጥናት ተደርጎ ምላሽ ይሰጣል የሚል ሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ ስለሌለ፣ የዎላይታ ሕዝብ ይህንን ሕገ መንግሥታዊ አካሄድን ጥሶ የሚቀርብለትን አሳሳች ሐሳብ እንዳይቀበል በማለት የፓርቲው አመራሮች ለሕዝቡ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም የፓርቲው አመራሮች፣ ‹‹ደኢሕዴን ከሕገ መንግሥታዊ ድንጋጌ ውጪ ጥናት ነው እየተባለ በቀረበው ሐሳብ ላይ ውይይት እንዲደረግ ሕዝቡን ከማስገደድ እንዲቆጠብ፤›› ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

‹‹በደቡብ ክልል የሰው ሕይወት በጠፋባቸውና የንብረት ዘረፋና ውድመት በደረሰባቸው ሥፍራዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጁ ተገቢ ቢሆንም፣ በሌሎች ሰላማዊ አካባቢዎች የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መታወጅ ተገቢነት የለውም፡፡ ስለሆነም በዎላይታና አካባቢ የታወጀው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እንዲነሳ እንጠይቃለን፤›› በማለት አመራሮቹ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...