Friday, July 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

. . .ላሸንዳይ ወሻደይ

ትኩስ ፅሁፎች

በደም ግባቷ አዳኝ ÷ በፍቅሯ ገዳይ
ጀግና የሚቀናት ÷ ከየዐውዱ ላይ፤
የቆቦዋ ቆንጆ ÷ በምንስ ጉዳይ!
ሶለሏ አስተርእዮ ÷ ይታይ ከመ ፀሓይ?
ውበት ከደም ግባት ÷ ሞያም ከምግባር
ተሰናስለው አብረው ÷ በሥነ ባህርይ
የወሎዋ ቆንጆ ÷ ታምር በተለይ፤
ከኹሉም በላይ።
ታምር ()ችም ሀገር ÷ መልከ ጥፉ ያሏት፤
ውስጧ ሳይታይ።
የሻዳይ ዓለም ÷ ያሸንድዬ ኑሮ
የሶለልም አምሮ ÷ ቢታይ ዘንድሮ፤
ከፊት የጋረደው ÷ ተራራው ተንዶ፣
ገደሉ ተሞልቶ፤
የለያየው ጡቡ ÷ ግድግዳው ተዋግዶ፣
ተመጋግዶ ነዶ፤
ዐመዱ ብቻ አለ ÷ ደጁን አጨቅይቶ
ቤቱን አበላሽቶ።
ክረምቱ ሳይወጣ፤
ከሻደይ ቦልቃ ÷ ባሸንድዬ ደምቃ
ደማምቃምትወጣው ÷ ያቺ ውብ ጨረቃ
እንደው ምን ተጋርዳ? እምን ሥርስ ወድቃ፤
ጥሩዋ ገጽታ ÷ ትቀር ጨፈጋጋ።
ያቢይ ዓዲ ምድሪ ÷ አሸንዳዬ መዓሬ
በጣምምምታምሪ
እንደ ወይን ወበለስ ÷ ግና አትሞሸሪ፤
በጋን ላትኖሪ።
ክረምቱ ተፈጥሮሽ ÷ ከወንዝ ያልገበረሽ
እወንዝ ያልተከለሽ፤
ያላቈጠቈጥሽ ÷ ያላዘረዘርሽ
አንቺም እንዳገርሽ፤
ያለ አገር ፍቅር ÷ ዘር ሐረግም የለሽ፤
ወንዝ አፍራ አይደለሽ።
ግናይሽ ብቻሽን ÷ ድንገት ብቅ ብለሽ፤
ውዴታው በዝቶልሽ።
በክረምቱ መውጫ ÷ በጠራው ሰማይ
ጉብ ብላስ ባያት ÷ የመስከረም ጣይ
ኧረ እንዴት ያላንቺ? ÷ ካላንቺ! ሻዳይ።
ከሌሊቱ ቍር ÷ ካመሻሹም ብርድ
ኹሉን ገላ ኣማጩ ÷ አንገብጋቢው ውርጭ፤
ሶለል ያላንቺማ! አንቺ የሌለሽበት
መች ያስወጣስ ደጅ?
ለለምለሙ ጎንሽ ÷ ተቸምችሞለት
ለምለም እንግጫ፣
በወገብሽ ታስራ ÷ ቅናትሽ ለብቻ፤
የእኔም ቀኔ ውጫ! ውጫ! ተዳርቻሽ።
ካለሙ ዳርቻ ÷ የወጣች ዓለም
ይኸው ቀን ወጥቶላት ÷ እንዳልቀረች የትም፤
ያም ሩቅ ዘመን ÷ ያኹኑም ዕሩቅ፤
ተወዲያ ነዪና ÷ ባለንናሸብርቅ።
ለክብረ በዓልሽ ÷ እንግጫው ተለቅሞ
ወገብሽም ዙሪያ ÷ ጎኑ ተሸልሞ
እርሱው ተገልድሞ፣
ተንዠርግጎ ሲታይ ÷ እንደ ሊማሊሞ፤
ከለመለመው መስክ ÷ ስንቱ አቈብቍቦ
ስንቱ ዞሮ አንጃብቦ፣
እሥርሽ ይታያል ÷ ልዩ ትኩረት ስቦ
ካደረግሽው አልቦ፡፡

  • ኃይለ ልዑል ካሣ
    ነሓሴ ፳፪/፳፻፲፩ ..
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች