Tuesday, February 27, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

ክቡር ሚኒስትሩ ቢሯቸው ከአንድ ኢኮኖሚስት ጋር እያወሩ ነው

[ክቡር ሚኒስትሩ የሰው ኃይል አስተዳደሩን ቢሯቸው አስጠሩት]

 • ፈለጉኝ ክቡር ሚኒስትር?
 • ቁጭ በል እስኪ፡፡
 • ምን ልታዘዝ?
 • እስኪ አስተናጋጅ አትምሰል፡፡
 • ምን አጠፋሁ?
 • ትዕዛዜን መስማት ብቻ ሳይሆን መፈጸምም አለብህ፡፡
 • እኮ ምን ልፈጽም?
 • ባለፈው ያዘዝኩህን ነገር ምን አደረግከው?
 • የትኛውን ነገር ክቡር ሚኒስትር?
 • ሥራህን ትተሃል ልበል?
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ያዘዝኩህን ፈጽመህ ሪፖርት እንደማቅረብ የትኛውን ነገር ትለኛለህ?
 • ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እኮ ከምን አደረስከው?
 • ምኑን?
 • እኔ ጠፋሁ?
 • ይቅርታ ሥራ ስለሚበዛብኝ እኮ ነው ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • የምን ሥራ ነው የሚበዛብህ?
 • ሪፎርም ላይ አይደለን እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • እኔም እኮ ያዘዝኩህ ከእሱ ጋር የሚሄድ ሥራ ነው፡፡
 • ምናለ ቢነግሩኝ?
 • የሰዎቹን ቅጥር ነዋ፡፡
 • የምን ቅጥር?
 • በል ከቢሮዬ ውጣልኝ፡፡
 • ይቅርታ ክቡር ሚኒስትር ምን አጠፋሁ?
 • ጭራሽ የምን ቅጥር ትለኛለህ?
 • ግራ አጋብተውኝ ነዋ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ታዲያ እንዳንተ ዓይነቱን ይዘን እንዴት እንዘልቀዋለን?
 • ተው እንጂ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እውነቴን እኮ ነው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር በየዓመቱ ተሻለሚ ሠራተኛ መሆኔን ረሱት?
 • በምንድነው የምትሸለመው?
 • በጠንካራ ሠራተኛነቴ ነዋ፡፡
 • አንተ መሸለም ያለብህ በሌላ ነው፡፡
 • በሌላ በምን?
 • በቀሽምነት፡፡
 • ምን አጠፋሁ?
 • ባለፈው ለውጡን ለማሳለጥ አሁን ያሉትን ባለሙያዎች አባረህ በእኛ ሰዎች ለውጣቸው አላልኩህም?
 • ምን ነካዎት ክቡር ሚኒስትር?
 • ምነው?
 • ተለውጠናል እያልን እኛ እንደ ቀድሞዎቹ እንሁን?
 • ምን?
 • ለነገሩ ዘፈኑም እንደዚያው ነው፡፡
 • እንዴት?
 • አዲስ ንጉሥ እንጂ ለውጥ መቼ መጣ?
 • አንተ ራስህ የለውጡ አደናቃፊ መሆንህን መቼ አጣሁት?
 • እኔማ ለውጡን በጣም ነው የምደግፈው፡፡
 • ታዲያ የእኛ ሰዎችን ለምን አትቀጥራቸውም?
 • ክቡር ሚኒስትር በብቃት እንጂ በፖለቲካ አመለካከት ሰው አንቀጥርም እያልን እኮ ነው፡፡
 • እሱ ፕሮፓጋንዳ ነው፡፡
 • ለማንኛውም እኔ አላደርገውም፡፡
 • ተወው እኔ የማደርገውን አውቃለሁ፡፡
 • ምን ሊያደርጉ?
 • አንተን እቀይርሃለሁ!

[ክቡር ሚኒስትሩ አንድ ስብሰባ ላይ ከጋዜጠኛ ጋር ይገናኛሉ]

 • ሰላም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ሰላም፡፡
 • አላወቁኝም?
 • ማን ነህ?
 • ጋዜጠኛ ነኝ፡፡
 • አላወቅኩህም፡፡
 • ይገርማል?
 • ምኑ ነው የሚገርመው?
 • እኔን አለማወቅዎት ነዋ፡፡
 • ከመቶ ሚሊዮን ሕዝብ ውስጥ አንተን እንዴት ላውቅህ እችላለሁ?
 • ያው ጋዜጠኛ ነኝ ብዬ ነዋ፡፡
 • ስማ አሁን እኮ ድፍን የአገሪቱ ሕዝብ ጋዜጠኛ ሆኗል፡፡
 • እ. . .
 • ማንም እየተነሳ አይደል እንዴ በየሶሻል ሚዲያው እንደ ጋዜጠኛ የሚጽፈው፡፡
 • እሱስ ልክ ነዎት፡፡
 • ይኸው ይኼን የተከበረ ሙያ ለማርከስ ሁሉም በየፊናው ያልገባውን ይጽፋል፡፡
 • እኔም እሱን የምታገል ጋዜጠኛ ነኝ፡፡
 • እንዴት ነው የምትታተገለው?
 • እውነት በመናገር ነዋ፡፡
 • አልገባኝም?
 • ማለቴ አሁን ሁሉም በየፌስቡኩ ውሸት እኮ ነው የሚጽፈው፡፡
 • እሱ አይደል እንዴ አገር እያፈረሰ ያለው፡፡
 • ስለዚህ ክቡር ሚኒስትር እኔም የበኩሌን ለመወጣት በየፌስቡኩ የሚጻፉ ውሸቶችን ለሕዝቡ አጋልጣለሁ፡፡
 • ምን አልከኝ?
 • ውሸት አጋላጭ ጋዜጠኛ ነኝ፡፡
 • ዋናው ውሸት አሠራጮች እናንተ አይደላችሁ እንዴ?
 • ክቡር ሚኒስትር እኔ ሁሌም እውነት ነው የማወራው፡፡
 • እሱን እንኳን ተወው፡፡
 • እንዴት?
 • ስማ ለሕዝቡ እውነት የሆነ ነገር ለመንግሥት ውሸት፣ ለሕዝቡ ውሸት የሆነ ነገር ደግሞ ለመንግሥት እውነት ነው፡፡
 • እ. . .
 • ለማንኛውም አንተ ለሕዝቡ እውነት ከምትናገር፣ የመንግሥትን ውሸት ብታወራ ይሻልሃል፡፡
 • ኧረ እኔ ውሸት አላወራም፡፡
 • ነገርኩህ እኮ ውሸት አንፃራዊ ነው፡፡
 • እንዴት?
 • ለማንኛውም እንቀጥርሃለን፡፡
 • በምን ክቡር ሚኒስትር?
 • ለሕዝብ እውነት ከምታሠራጭ፣ ለእኛ እንድታሠራጭልን ነዋ፡፡
 • ምንድነው የማሠራጭላችሁ?
 • ውሸት!

[ክቡር ሚኒስትሩ ቢሯቸው ከአንድ ኢኮኖሚስት ጋር እያወሩ ነው]

 • አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ለምኑ?
 • ሊያናግሩኝ ፈቃደኛ ስለሆኑ ነዋ፡፡
 • ምን ማለትህ ነው?
 • ምነው ክቡር ሚኒስትር?
 • እዚህ ቢሮ ያለሁት ሕዝቤን ላገለግል እኮ ነው፡፡
 • በጣም ደስ ይላል፡፡
 • በተለይ ደግሞ እንደ አንተ ዓይነቱን ምሁር ማግኘት ለራሴም ይጠቅመኛል፡፡
 • አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ምን ልርዳህ ታዲያ?
 • እኔም አመጣጤ ስለአገራችን ጉዳይ እንድናወራ ነው፡፡
 • በምን ጉዳይ?
 • በፕራይቬታይዜሽን ጉዳይ፡፡
 • ይኼው የምሁራን ጥያቄ ሊመለስ ነው፡፡
 • እንዴት ክቡር ሚኒስትር?
 • የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወደ ግል ሊዘዋወሩ ነዋ፡፡
 • ይኼን ማን ነው የምሁራን ጥያቄ ያደረገው?
 • ሁሌም መንግሥት ከንግዱ ይውጣ ትላላችሁ አይደል እንዴ?
 • አሁንስ ቢሆን መቼ ሙሉ ለሙሉ ትሸጡታላችሁ?
 • ያው ቀስ በቀስ ሙሉ ለሙሉ መሸጣችን አይቀርም፡፡
 • ለማንኛውም ክቡር ሚኒስትር የልማት ድርጅቶቹ የመሸጥ ጥያቄ የሁሉም ምሁራን አይደለም፡፡
 • እንዴት?
 • ዛሬ አመጣጤ ድርጅቶቹ እንዳይሸጡ ለመምከር ነው፡፡
 • ለምንድነው የማይሸጡት?
 • ክቡር ሚኒስትር የአገሪቱን ኢኮኖሚ መቀመቅ ሊከተው ይችላል፡፡
 • እ. . .
 • የድርጅቶቹ መሸጥ በኢኮኖሚው ላይ ምንም ፋይዳ አያመጣም፡፡
 • የውጭ ምንዛሪ እናገኝባቸዋለን እኮ፡፡
 • ጊዜያዊ መፍትሔ ዘላቂ መፍትሔ አያመጣም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • አልገባኝም?
 • ክቡር ሚኒስትር የምትታለብ ላም ሸጦ ሰው እንዴት ወተት መግዛት ያስባል?
 • እ. . .
 • የድርጅቶቹ መሸጥ ጭራሽ ኢኮኖሚው ላይ ጫና ይፈጥራል፡፡
 • ይኸው እነ ዓለም ባንክ እንድንሸጣቸው እያበረታቱን እኮ ነው፡፡
 • የእነሱ መርህ እኮ በሰው ቁስል እንጨት ስደድበት ነው፡፡
 • ምን?
 • ክቡር ሚኒስትር ነገሩ በእርጋታ ቢታሰብበት ይሻላል፡፡
 • ስማ ድርጅቶቹ ቢሸጡ እኮ አንተን ጨምሮ ሁላችንም እንጠቀማለን፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር ከራሳችን በላይ ስለአገሪቱ ማሰብ አለብን፡፡
 • እ. . .
 • አገሪቱ ሳትኖር እኛ መኖር አንችልም፡፡
 • ስነግርህ አገሪቱም ትቀየራለች፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር በኋላ የማንወጣው አዘቅት ውስጥ እንዳንገባ?
 • በቃ ይሸጣሉ አልኩህ እኮ፡፡
 • እኔ ደግሞ ይታሰብበት እያልኩ ነው፡፡
 • ምንም አይታሰብበትም፡፡
 • ለምን?
 • አገሪቱ ትቀየራለች፡፡
 • ድርጅቶቹ ከተሸጡ አገሪቱ ሳትሆን የምትቀየረው ሌላ ነው፡፡
 • ማን ነው የሚቀየረው?
 • እርስዎ!

[ክቡር ሚኒስትሩ ከአንድ የተቃዋሚ ፓርቲ መሪ ጋር ተገናኝተው እያወሩ ነው]

 • ምን እያሰባችሁ ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ስለምኑ?
 • ስለምርጫው፡፡
 • ይራዘምላችሁ እንዴ?
 • ኧረ እኛ አልወጣንም፡፡
 • ታዲያ ለምን ጠየቅከኝ?
 • በአገሪቱ ሰላምና ደኅንነት መስፈን አልቻለማ፡፡
 • ለውጥ ላይ መሆናችንን አትርሳ፡፡
 • ብንሆንስ?
 • እናንተም እኮ አገር ቤት ገብታችሁ እንዲህ በነፃነት እንድትንቀሳቀሱ ያደረጋችሁ ይኼ ለውጥ ነው፡፡
 • አሁን እኮ ለውጡ ወደ ነውጥ እየተለወጠ ነው፡፡
 • ምን እናድርግ እኛ?
 • ሥራችሁን ሥሩ፡፡
 • ማለት?
 • ሰላምና ደኅንነት ማስከበር እኮ የመንግሥት ኃላፊነት ነው፡፡
 • እ. . .
 • እንደዚያ ካልሆነ ግን ምርጫውን ማድረግ አይቻልም፡፡
 • ስለዚህ ይራዘማ?
 • እሱ ጥሩ አይደለም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ለምን እናንተ አትጠይቁም?
 • ምን ብለን?
 • ምርጫው ይራዘም ብላችሁ፡፡
 • ጥያቄው በእኛ አያምርም፡፡
 • ብትጠይቁ ይሻላል፡፡
 • ለመሆኑ ክቡር ሚኒስትር እናንተ ምርጫው ለምን እንዲራዘም ፈለጋችሁ?
 • የአገሪቱ ሰላምና ደኅንነት አስተማማኝ እንዲሆን ነዋ፡፡
 • አልመሰለኝም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • እንዴት?
 • እናንተ እንዲራዘም የፈለጋችሁት ሌላ ነገር ለማራዘም ፈልጋችሁ ነው፡፡
 • ምን ለማራዘም?
 • ሥልጣናችሁን!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...

ሕወሓት በትግራይ ጦርነት ወቅት በፌዴራል መንግሥት ተይዘው ከነበሩት አባላቱ መካከል ሁለቱን አሰናበተ

በሕወሓት አባላት ላይ የዓቃቤ ሕግ ምስክር የነበሩት ወ/ሮ ኬሪያ...

የኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ለመፈጸም የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችለውን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...

[ክቡር ሚኒስትሩ  የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላትን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እያዞሩ እያስጎበኙ ከአንድ ዲያስፖራ ጋር እየተወያዩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር የዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ከተማዋን ጎብኝቼ ነበር። እውነት? አዎ። ታዲያ ልዩነቱን እንዴት አዩት? በጣም ይደንቃል። ሌላ ከተማ እኮ ነው የመሰለችው። አይደል? አዎ። እንዴት ነው...