Monday, December 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶቹን ማደራጀት መጀመሩን አስታወቀ

ምርጫ ቦርድ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶቹን ማደራጀት መጀመሩን አስታወቀ

ቀን:

የኢትዮጵያ ምርጫ ቦርድ በሚቀጥለው ዓመት ይደረጋል ተብሎ በሚጠበቀው ጠቅላላ ምርጫ ምክንያት የክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቶቹን ማደራጀት፣ በኅዳር 2012 ዓ.ም. ለሚደረገው የሲዳማ ዞን ሕዝበ ውሳኔ ዝግጅት መጀመሩን አስታወቀ፡፡

በዘጠኝ ክልሎችና በሁለት የከተማ አስተዳደሮች ለሚገኙት ጽሕፈት ቤቶች ኃላፊዎቹን ለመመደብ፣ መሥፈርቶችን አዘጋጅቶ የሚያሟሉ ዕጩዎች እንዲያመለክቱ ጥሪ አቅርቧል፡፡

የሲዳማ ዞንን የክልልነት ጥያቄ ይመልሳል የተባለውን ሕዝበ ውሳኔ አስመልክቶ፣ የሥራ ዕድቅና በጀት ማዘጋጀቱን ቦርዱ አስታውቋል፡፡ ለዚህም የተለያዩ ውይይቶችን ከሚመለከታቸው አካላት በቀጣይ እንደሚያደርግ ታውቋል፡፡

የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ወ/ሪት ብርቱካን ሚደቅሳ ነሐሴ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በሰጡት መግለጫ ወቅት ከጋዜጠኞች ለተነሱላቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

በቅርቡ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀውን የምርጫና የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅን፣ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት ስለመቃወሙ ለተነሳው ጥያቄ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡

ፓርቲዎቹ ቅሬታ ማቅረባቸው የሚጠበቅ ነው ያሉት ወ/ሪት ብርቱካን፣ በተለይ ከ100 በላይ ቁጥር ያላቸው ፓርቲዎች ሲኖሩ የሚጠበቅ ነው ብለዋል፡፡

የፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አዋጁ ተፈጻሚ እንዳይሆን ባለፈው ሳምንት መጠየቁ ይታወሳል፡፡

የጋራ ምክር ቤቱ ከሚያቀርባቸው ጥያቄዎች ውስጥ፣ ‹‹ከዚህ ቀደም በውይይት ወቅት ያቀረብናቸው ጥያቄዎች ለምን እንዳልተካተቱ የምንወያይበት አንድ ተጨማሪ መድረክ እንዲፈጠር፣ እኛ በተገኘንበት በጥያቄያችን መሠረት እንደገና አዋጁ እንዲታይ፣ እንዲሁም የአገሪቱ ሕግ በሚፈቅደው መሠረት እንዲሻሻል፤›› መሆናቸውን የጋራ ምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ግርማ በቀለ ለሪፖርተር መናገራቸው ይታወሳል፡፡

‹‹ከፓርቲዎቹ ጋር ወደ ሦስት የሚሆኑ የምክክር መድረኮች ነበሩን፡፡ ይህ በቂ አልነበረም ማለት ይቻላል፡፡፡ ነገር ግን ሕጉን አላየሁትም ማለት ውሸት ነው፤›› ሲሉ ወ/ሪት ብርቱካን መልሰዋል፡፡

የቦርድ ሰብሳቢዋ ለተፈናቀሉ ዜጎች በተለየ የምርጫ ጣቢያዎች እንደሚዘጋጁ አክለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

በዓለም አቀፍ ደረጃ ሕይወታቸውን በኤድስ ምክንያት ላጡ ሰዎች 35ኛ ዓመት መታሰቢያ

ያለፍንበትን እያስታወስን በቁርጠኝነት ወደፊት እንጓዝ - በኧርቪን ጄ ማሲንጋ (አምባሳደር) በየዓመቱ...

እዚያ ድሮን… እዚህ ድሮን…

በዳንኤል ካሳሁን (ዶ/ር) ተዓምራዊው የማዕበል ቅልበሳ “በሕግ ማስከበር” ዘመቻው “በቃ የተበተነ...

ለፈርጀ ብዙ የማንነት ንቃተ ህሊናችን የሚጠቅሙ ጥቂት ፍሬ ነገሮች

በበቀለ ሹሜ ከጨቅላነት ጅምሮ ያለ የእያንዳንዳችን የሰብዕና አገነባብ ከቤተሰብ እስከ...