ኦዳ ኢንተግሬትድ ትራንስፖርት አክሲዮን ማኅበር ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ወጪ የተደረገባቸው ኢንቨስትመንቶችን ቅዳሜ ጳጉሜን 2 ቀን 2011 ዓ.ም. አስመረቀ፡፡ ማኅበሩ ለሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎት የሚያሰማራቸውን ሃምሳ ዘመናዊ ቮልቮ አውቶቡሶችን ወደ አገር ውስጥ ከማስገባቱም በተጨማሪ፣ ሁለት ዘመናዊ የነዳጅ ማደያና ዴፖ በገላንና በአዲስ አበባ ዳርቻ አካባቢ በማስገንባት በነዳጅና የነዳጅ ውጤቶች ማከፋፈል ለመሰማራት መዘጋጀቱን አስታውቋል፡፡ አክሲዮን ማኅበሩ ከሁለት ዓመት በፊት በአሥር ሺሕ ባለአክሲዮኖች፣ በአራት መቶ ሚሊዮን ብር የተፈቀደ ካፒታል የተቋቋመ ዘርፍ ብዙ ኩባንያ እንደሆነ ተገልጿል፡፡ በምሥሉ ላይ የሚታዩት የትራንስፖርት አገልግሎት ለመስጠት የተዘጋጁት በቅርቡ አገር ውስጥ የገቡት ዘመናዊ ቮልቮ አውቶብሶች ናቸው፡፡